>

ሰማያዊ ግንቦት 9 መስቀል አደባባይ ሕዝባዊ የአደባባይ ስብሰባ ጠራ

•አስተዳደሩ ሳይፈርም የተቀበለውን ደብዳቤ ግልባጭ የተጻፈለት ምርጫ ቦርድ ፈርሞ ተቀብሏል

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

Semayawi party ginbot 9 demonstrationሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 16/2007 ዓ.ም የሚደረገውን 5ኛው ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ መወሰኑን ለከተማ አስተዳደሩ ከጻፈው ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፓርቲው ህዝባዊ ስብሰባውን ለማድረግ ያሳወቀው ቦታ መስቀል አደባባይ ሲሆን፣ ስብሰባው የሚቆየውም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡00 ድረስ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህንኑ የአደባባይ ስብሰባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲያውቀው ሰማያዊ ፓርቲ ደብዳቤ የጻፈ ሲሆን፣ ደብዳቤውን አስተዳደሩ ደብዳቤው ላይ ሳይፈርም መቀበሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሆኖም ግን ደብዳቤውን የተቀበሉት የስራ ኃላፊ ለሚመለከተው አካል ፈርመው መምራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ግልባጭ የተጻፈለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የተላከለትን ደብዳቤ ፈርሞ መቀበሉን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

Filed in: Amharic