>

ለዞን ዘጠኝ ጦማሪያን መታሰቢያ

  ሰውን አስሮ ይዞ ማስቀረት አይቻል
  በግዞት ቤት አስሮ ከሰውም ቢለያይ
  አካልን ነው እንጂ መች ሀሳብ ሊታሰር
  ሁሉን ይፅፈዋል በአዕምሮው ማህደር
 
  እናም ሰውን ማሰር አይደለም መገደብ
  ካሰበው እንዳይደርስ አይቻልም ማቆም
  ቢሆንም መታሰር እንዲሆን አውቃለው
  መፈታት አይቀርም ቀን አለው ቀን አለው
 
 የሀገርን ችግር መፃፍ ወንጀል ሆኖ
 ሰዎች ይገባሉ በወህኒ ታጉሮ
 እናም ወንጀላቸው ሲጠየቅ በይፋ
 ህገ መንግስት መናድ! አረ ፍትህ ጠፋ
 
  ምንም አይነት ወንጀል ሳይኖር ለአመታት
  ታስረው ይከርማሉ በጨለማ ግዞት
  መገረፉ አይጣል ኤሌትሪኩም አለ
 ባልሰሩት ወንጀል ላይ እመኑ እያለ
 
  ማመን መች ነው ቀላል ሞት እኮ ይሻላል
  ባልሰሩት ወንጀል ላይ ቲያትር ቀላቅሎ
  በእመን አትመን በዱላ አባሮ
  ይቅርታ ጠይቁ ይላል ውሎ አድሮ
 
  ስጋ እንኳን ቢቃጠል ለእውነት ቢከፈል
  አጥንትን አውጥቶ ህመሙ ቢያይል
  እውነት ነው ሚያሸንፍ የማታ የማታ
  ሀሰት ይወድቅና እውነት ነፃ ወጥታ
 
    ዘ-ፀአት ዞን ፱ ጦማሪያን ባሰብኩ ጊዜ
     ኒኮልሰን እስትሪት
    ገጣሚ-ሚካኤል ካሳሁን
Filed in: Amharic