>
11:25 am - Monday November 29, 2021

የዲሲ ፍ/ቤት [ አርአያ ተስፋማሪያም]

Money
በቅ/ማርያም ቤ/ክ ቦርድ አመራር አባላትና አስተዳዳሪዎች (ቄስና ዳይቆናት) የተፈጠረው አለመግባባት በትላንትናው እለት በፍ/ቤት ውሳኔ አግኝቷል። ሽኩቻውን በሁለት ጐራ ከፍለው በዋናነት ሲፋለሙ የሰነበቱት ዶ/ር አማረና ዶ/ር አክሊሉ ናቸው። ከ23 በላይ ሰዎችን አላግባብ አባረዋል የተባሉትና በሃይል ቤ/ክስቲያኑን ተቆጣጠሩ የተባሉት ዶ/ር አማረ ለአንድ ወር ቦርዱን እንዲመሩና ከዛ በኋላ አዲስ የቦርድ አመራር ተመርጦ እንዲዋቀር በውሳኔው ተመልክቷል። ትላንት ምሽት ሁለቱም ቡድኖች «ተፈረደልን» ሲሉ ደጋፊዎቻቸውን ሲሸነግሉ ታይተዋል። ቀልደኛ ወዳጄ «የባድመ ውሳኔ» ብሎታል።..ሶስት አባላት (ዶ/ር የሚመሩት) በቅርቡ ሶስት መቶ ሺህ ዶላር አውጥተው ከባንክ መውሰዳቸው በሰነድ ማስረጃ ሲታወቅ 1 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ « ሌላ ቦታ ተቀምጧል» መባሉና “ይህ ቦታ የት ነው?”..ተብሎ ቢጠየቅም በቂ ምላሽ እንዳልተገኘ ተነግሯል። ..ባጭሩ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር መዘረፉ ሲጠቆም ጉዳዩ በፍ/ቤትና በፌዴራል መንግስት እንደሚታይ ተጠቁሟል። ..እስካለፈው እሁድ ድረስ በቅ/ማርያም ቤ/ክ ሲፈፀሙ የነበሩ ድርጊቶች አንገት ያስደፋሉ። አንዱ ዶ/ር ሲናገሩ ሌላኛው ዶ/ር ማይክ በመቀማት «ምናባህ ታውቃለህ» እያሉ በህዝብ ፊት ይዘልፉ ነበር። ከ1 ሺህ ህዝብ በቤ/ክ ውስጥ እያለ መብራት ማጥፋት ምን ይባላል?..እነዛ በርካታ ህፃናት ቢጎዱና ቢሞቱስ?..ባለፈው እሁድ ሴኩሪቲ በሶስት በር በማቆም ለመቁረብ የመጡ ህፃናት – ወላጆችን አትገቡም «የእነከሌ ደጋፊዎች ናችሁ» ማለት አያሳፍርም?….ከ7 ሚሊዮን በላይ ወገን ተርቧል፤ ገንዘቡ ለነዚህ ወገኖች ምግብ መግዣ ይዋል።

Filed in: Amharic