>
5:13 pm - Monday April 20, 1699

ሰውዲ አረቢያ በገንዘብ እጦት ችግር ክፉኛ ልትመታ ነው ተባለ [ታምሩ ገዳ]

Tamiru Gedas article 27-10-2015ነገሩ ቀልድ እና ሟርት ይመሰላል፣ ነገር ግን እውነት ነው ።ለብዙዎች እርጥባን እና ምጽዋት በመቸር እንደ ጣኦት የምተመለከው ስውዲ አረቢያ እንደ አለማቀፍፉ የገንዘብ ማእከል (አይ ኤም ኤፍ) ሰሞነኛ ማሰጠንቀቂያ ከሆነ (ይህቺው የአለማችን ቁጥር አንድ የተፈጥሮ ነዳጅ አመራች እና ሻጭ አገር) በቀጣዮቹ ጥቂት አመታት ውስጥ ክፉኛ የገንዘብ እጦት ችግር ሊገጥማት አንደሚችል አስጠንቅቋል።

የአሜሪካው ኬብል ኔውስ ኔት ዎርክ(CNN ) በሰኞ ጥቅምት 25 2015 ዘገባው እንደ ገለጸው ከሆነ በአሁኑ ወቅት በአለም ገበያ ላይ ያለው የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአማካኝ በበርሚል $50( ሃምሳ ዶላር) ሆኖ ከዘለቀ የዋጋ ማሽቆልቆሉ በ አምራቾቹ ላይ የ 360 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ሰለሚፈጠር ዋንኛ ነዳጅ አቅራቢያዋ እና ነዳጅም ስትንፋሷ የሆነው ሰውዲ አረቢያን ጨምሮ በቀጣዩ 5 ወይም ከዚያ ባነሰ አመት ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ እጦት የገጥማቸዋል ሲል አለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አስጠንቅቋል።ሪፖርቱ ጎረቤት ኦማን እና ባህሪንም ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸው ተንብዮዋል።ከ አመት በፊት በበርሚል$ 100( አንድ መቶ ዶላር) የነበረው ነዳጅ ዘይት በቅርቡ እሰከ $45 ዶላር መወረዱ እና ሰወዲ አረቢያ የመሳሰሉት አገሮች ከመጠባበቂያ ፉንዳቸው እስከ መቆንጠር ተገደዋል ተበሏል።”ነዳጅ ሻጮች አገሮች ገቢያቸውን እና ወጪያቸወን ማሰተካከል የጠበቅባቸዋል” ሲል IMF ምክሩን ለእነ ስውዲ አረቢያ ሰጥቷል።

የእነ ስውዲ አረቢያ የኢኮኖሚ መንገዳገድ የመጣው በአካባቢው በተቀሰቀሰው የእርሰ በርስ ጦርነት እና የገበያው መናጋት በተፈጠረ ማግስት መሆኑ ሁኔታውን አባብሶታል ተብሏል።ስወዲ አረቢያ ከችግሯ ለማገገም ነዳጅ በበርሜል በያንስ $106 መሸጥ የግድ ይላታል ያለው ሪፖርቱ ስውዲ አረቢያ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቦንድ በመሽጥ ችግሯን ለመቅረፍ ጥረት ብታደርግም በጎረቤት የመን የሚገኙ የሺያት አማጺያኖችን ለመዋጋት በሚል ሽፋን እና ደንበሯን ለማሰከበር ስትል እኤአ 2014 ብቻ የመከላከያ ባጀቷን ወደ 80.8 ቢሊዮን ዶላር(17% ጭማሪ አና በ አለማችን 4ኛዋ ለመከላከያ ወጪ አድራጊ አገር አደርጓታል። አሜሪካ 610 ቢሊዮን ፣ቻይና 216 ቢሊዮን ዶላር ፣ሩሲያ 81 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ከ 1 እስከ 3 ይከታተላሉ) የመደበች፣ በ 2011 አካባቢውን ያመሰቃቀለው የአረብ ስፕሪንግ (የአረብ አብዮት)ከደጃፏ ጎራ አንዳይል ጥረት የምታደረገው ሪያድ የዜጎቿን ቁጣ ለማብረድ ስትል የማሕባራዊ (social) እና የመከላክያ ወጪዋን በቀላሉ የምትቀነስ አይመስልም ተብሏል
የሰውዲ ነገር ሲነሳ ከሁለት አመት በፊት ኑሮን ለማሸነፍ እና አንጀራ ፍለጋ ወደ ግዛቷ የገቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምስኪን አትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኛ እህቶቻችን እና የጉልበት ሰራተኞች ወንድሞቻችንን ጨረቄን እና ማቄን ሳይሉ እጅግ ኢ-ሰብ እዊነት በተሞላው መንገድ ከግዛቷ ጠራርጋ ማባረሯን በርካታ አትዮጵያዊያኖችን ማሳዘኑ እና ማስቆጣቱ አይዘነጋም። ያንንም መጥፎ አጋጣሚ ብዙዎች “ብ ሔራዊ ውርደት” ሲሉት ተደምጠዋል።
Tamiru Gedas article 27-10-2105-1ማን ያውቃል የዛሬ 50 እና 60 አመትታት የግመሎች እና የፍየሎች መፈንጪያ የነበረችው ያቺ ከበረሃው ከረሰ ምድር ውስጥ በሚቀዳ የነዳጅ ሃብቷ ብቻ የአለም ጡነቸኞችን ሳይቀር የመታሰገዳቸው ስውዲ አረቢያ የነበረው እንዳልነበረ ሆኖ ኪሳራው ሲበረታባት እና ደግነታችንን ከቅደመ አያቶቿ ሰለመታውቅ ወደ ሃበሽ ምድር(ኢትዮጵያ) ለመሸሸግ ዜጎቿን ትልክ ይሆናል፣ሰደቱ ወደ አረቡ አለሙ መሆኑ ቀርቶ ወደሰው ልጆች መፍለቂያ (ኢትዮጵያ) የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም ። ኋለኞች ፊተኞች ፊተኞች ኋለኞች ይሆናሉ የሚባለው ስለዚህ አይደል?።

Filed in: Amharic