>
9:14 am - Saturday February 4, 2023

ፕ/ት ሙጋቤ እግዚአብሔር ኬኒያኖችን በመፈጠሩ አማረሩት [ታምሩ ገዳ]

Mugabeየወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ዋና ጸሃፊ እና የዙምባብዊው ፕ/ት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ እግዜአብሔር የኢትዮጵያ የቅርብ ወዳጅ እና ጎረቤት አገር የሆነችው የኬኒያን እብዛኛው ሕዝቧን በመፍጠሩ በፈጣሪ ላይ ያላቸውን ቅሬታቸውን አሰሙ፡
በሳለፍነው እሁድ በመዲናይቱ ሃራሬ በተካሔደ አንደ የቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በክብር እንግደነት የተገኙት የ 91 አመቱ ጉምቱ የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ዋና ጸሃፊ ፕ/ት ሙጋቤ “እግዜአብሔር በአለማችን ላይ እጅግ የረቀቁ ፣ የሞተ ሰው ሳይቀር የሚገፍፍፉ ሌቦች የሆኑት ኬኔያዎችን መፍጠር አለነበረበትም።” ሲሉ በጎረቤት ኬነያ ሕዝብ ላይ የቃላት ጦርነት አሰምተዋል።
ሙጋቤ ትችታቸውን ሲያራዘሙ “እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ሰዎች(ኬኔያዎች) አንዳንዴ ነገረ ስራቸው ያሸማቅቀኛል፣አንዳንድ ጊዜ ሰመለከታቸው ሰርቆት በደም ሰራቸው ወስጥ የተዋሃደ የመሰለኛል፣ ግማሹ የአገሬው ህዝብ ሰርቆትን ነው የተካነው ፣እነዚህ ስዎች (ከኔያዎች ) ወደ ትምህርት ቤት ሔደው ሊማሩ እና ሊያነቡ ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን እነርሱ በሰርቆት ነው የተካኑት ።እነደውም እንዳንድ ጊዜ ኬኔያ ውስጥ በባችለር ዲግሪ የሚያሰመርቅ የሌብነት ተቋም እና የሌብነት ኮርስ ያለ ይመሰለኛል።ኬነያዎች ሰራ ሲያገኙ አያማረሩም ምክንያቱም አንዴ እግራቸው እና አንገታቸው ከገባ የተገኘውን ገንዘብ ጠራርገው እንደሚወሰዱት ያውቃሉ ፣ቤታሰሩ እንኳን ነጻነታቸውን ወዲያውኑ እንደሚያሰመልሱ እርግጠኞች ናቸው ።ሌላው ቀርቶ ዳኛው እንኳን የሌቦቹን ያህል ጉልበት የለውም(በገንዘብ ያንበረክኩታል) ።” ያሉት ፕ/ት ሙጋቤ የዙምባብዊ ዜጎች በአጋጣሚ ወደ ኬንያ ጎራ ካሉ እራሳቸውን ከኬኒያዎች እንዲጠብቁ መክር መሰጠታቸወን( ዘ ሰፔክታተርሰ )ተሰኘው ድህረ ገጽ በህዳር 4 2015 አኤአ ዘግቦታል።”ዙምባቤዎች ታማኞች እና አገራችውን የሚያፈቅሩ ናቸው፣ አደራ የኬንያዊያኖች የሰርቆት በሽታ እንዳይተላፈባችሁ ጠንቀቅ በሉ።” በማለት ሙጋቤ ተናግረዋል ተብሏል።
ፕ/ት ሙጋቤ አልፎ አልፎ በሚናገሯቸው ነግግሮች የሚዲያ ተኩረት ከሚሰቡ ጥቂት የአለማችን መሪዎች ተረታ የሚካተቱ ሲሆን በአንደ ወቅት የቀደሞው የደቡብ አፍሪካው ፕ/ት ኔልሰን ማንዴላን ” ለቐኝ ገዢዎች ከመጠን በላይ ጻድቅ የሆኑ መሪ ናቸው “በማለት ወርፈዋቸው ነበር። በሌላ ጊዜም ጃማይካኖችንም እንዲሁ “ ወንዶቻቸው በጋንጃ/ሱረት እና በጭፈራ ያበዱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻቸው በሴቶች ብቻ የተጨናነቁ ናቸው። አብካችሁ እንደ ጃማይካኖች አትሁኑ ።”ሲሉ ለአገራቸ ህዝብ መናገራቸው ተደምጧል።
ፕ/ት ሙጋቤ በዚህ ብቻ አላበቁም ከዚህ ቀደም የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር ቶኔ ብልየርን “በ አገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትግቡ በተረፈ ገሃነም/ሴኦል መገባት ትችላላችሁ”ብለዋቸዋል። የ ሃያሏ አገር አሜሪካ ፕ/ት ባራክ ኦባማ በቅርቡ በ 50 ግዛቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን/ግበረሰዶማዊነትን በመፍቀዳቸው የተቆጡት የካቶሊክ እምነት ተከታዩ ፣አዛወንቱ ፡የነጻነት አርበኛው እና የዙምባብዊ መሪ ሙጋቤ”ወደ ነጩ የዋይት ሃውስ ቤተመንግስታቸው ተጉዤ ኦባማ እኔን እንዲያገቡኝ ተንበርክኬ አጠይቃለሁ።” ሲሉ ማሾፋቸውን በርካታ የምእራባዊያን የዜና አውትሮች በጊዜው ለዜናቸው ማጣፈጫነት ተጠቅመውበታል።
ታዲያ ሰሞነናውን የሙጋቤን አነጋገር ያዳመጡ ኬኒያዊያኖች እና ዙምባቤዎች የተለያዩ የደጋፍ እና የነቀፊታ አሰተያየቶችን በመሰጠት ላይ ሲሆኑ ከእነርሱም መካከል “ ሙጋቤ የራሳቸወን ቤት ሳይጸዱ /ኢኮኖሚያቸውን ሳይጠግኑ ሰለሌላ ቤት ምን አዘባረቃቸው? ፣ ሙጋቤ ታላቅ ሰው ናቸው ፣ የሙጋቤ አነጋገር በ አንድ ጎሳ የበላይነት ለምትናጠው ለኢትዮጵያ፣ በአምባገነኖች ለሚረገጡት ለ አነ ኡጋንዳ እና ለጅቡቲ፣ በሃይማኖት ለተተበተቡት ለታንዛኒያዎች ወዘተ (የምስራቅ አፍሪካ አገሮች) ጥሩ መልእክት ነው ያሉት አልጠፉም።
በነገራችን ላይ በጎረቤቶቻችን በኬኔዎች ላይ የሰላ ትችት በመሰጠት ደረጃ ሙጋቤ የመጀመሪያው አይደሉም የአሜሪካው እጩ ፕ/ት ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ሰለኬንያ ሲናገሩ “ በኬንያ ውስጥ ሁሉም ሰው ሌባ ነው።ሰለዚህ በመጪው 2016 የአሜሪካ ፕ/ት ሆኘ ከተመረጥኩ ሁሉንም ኬነያዎችን ከምደረ አሜሪካ ጠራሪጌ አሰወጣልሁ።” ሲሉ ከወዲሁ ዝተዋል ሲል ጀኔያን ዳይሊይ ፖስት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ አሰነብቧል።
እነዚህ መሪዎች በኬንያዎች ላይ ይህን መሰሉን መሪር ትችት ለምን ለማሰማት አንደፈለጉ ለጊዜው አልታወቅም፣ ይሁን እንጄ እንደ ናይጄሪያዎች በአለም ቁጭ የበሉዎች(አጭበርባሪዎች) የለም የሚሉ ወገኖች ጥቂት አይደሉም ። የኢትዮጵያ ባለሰልጣናት ሰሞኑን ወደ ናይጄሪያ ተጉዘው ሰለ ጸረ ሌብነት ልምድ እና ትምህርት መቅሰማቸውን የአገሪው ጋዜጣ ቫንጋርድ ሰሞኑን ዘግቧል። ችግሩ ተገባራዊነቱ ላይ እንጂ በትምህርት እና በሰልጠና ሰም እየተባለ ኮሪያ ፣ቻይና ህንድ ማለዢያ ያለረገጠ ባለሰልጣን የለም። የእኛን ሪክ ርድንም የሚደረሰብን አገር እና ባለሰልጣናት ያለ አይመሰልም። ይህንንም ጉዳይ ክቡር ጠ/ሚ/ር ሓይለማሪያም ደሳለኝ ሰሞኑን በተሌቭዥን መሰኮት ብቅ ብለው አረጋግጠውልናል።

Filed in: Amharic