>
5:13 pm - Friday April 19, 7507

ጥቂት ስለ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው[በላይ ማናየ]

Negere Ethiopia edtor Getachew-Assefa-300x200በፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ በተመረቀበት ዘርፍ በመንግስታዊ ተቋም ውስጥ ተቀጥሮ በአጥኚነት ከሁለት አመት በላይ አገልግሏል፡፡ ሆኖም ግን የዛሬ አራት አመት በፖለቲካ አመለካከቱ ልዩነት ከመስሪያ ቤቱ አባረውታል፡፡
ጌታቸው ይሰራበት ከነበረው መስሪያ ቤት ሲባረር ተመልሶ ወደ መንግስታዊ መስሪያ ቤት ቅጥር ማመልከትን አልመረጠም፡፡ ይልቁንስ አብዝቶ ወደሚወደው የሚዲያ ስራ አጋደለ እንጂ! በዚህም በቀድሞዎቹ መሰናዘሪያ ጋዜጣ እና ላይፍ መጽሄት (በኋላ ስሟ ተቀይሮ ‹ፍቱን› ተብላለች) በአምደኝነት ሰርቷል፡፡ ከዚያም የዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡
ነገረ ኢትዮጵያ ለ26 እትሞች ያህል ከሄደች በኋላ በጫና ከህትመት መውጣቷን ተከትሎም ጋዜጣዋን በማህበራዊ ድህረ ገጽ እንድትቀጥል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ዛሬ ጠዋት ለእስር እስከተያዘበት ጊዜ ድረስ በጋዜጠኝነት ስራው ላይ ደፋ ቀና ከማለት አልቦዘነም፡፡ በተያዘበት ወቅት እንኳ የፍርድ ቤት ውሎ ለመዘገብ ወደ ስራ እያመራ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ጌታቸው በማህበራዊ ሚዲያም ንቁ ተሳታፊ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ጌች ማዕከላዊ በእስር የሚገኝ ሲሆን የታሰረበትን ምክንያት ግን እስካሁን ለማወቅ አልተቻለም፡፡

Filed in: Amharic