>

ስንት ትውልድ እስኪጠፋ እንጠብቅ? [ፍርዱ ዘገዬ]

ዳዊት በመዝሙሩ – “አቤቱ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወዳንተ ይድረስ፣ በመከራየም ቀን ፊትህን ከኔ አታዙር” ሲል ፈጣሪውን ተማጽኗል፡፡ እኛስ? ከልበ ድንጋዮቹ ወንድሞቻችን ግፍና በደል የሚታደገንን ሙሤ እንዲልክልን እንደዳዊት እየጮኽን ነው ወይንስ እንደኖኅና እንደሎጥ የቅጣት ዘመናት በአሥረሽ ምቺው የኃጢኣት ባሕር ከተዘፈቁት ጋር አብረን ፈጣሪን ረስተናል?

እግዚአብሔር የኖኅ ዘመን ሰዎችን በውኃ ቀጣ፡፡ ኋላ ላይ ግን ለፍጡራኑ አዘነ፡፡ በዚያ መልክ ዓለምን ዳግም በውኃ ንፍር እንደማይቀጣም ቃል ገባ፡፡ እግዚአብሔር በሎጥ ዘመን ሶዶምንና ገሞራን በድኝ የእሳት ዝናብ ቀጣ፡፡ ሁለተኛውም ከመጀመሪያው ባሰ፡፡ የሰው ልጅ ግን ከሁለቱም አልተማረም፡፡ እናም በጥፋቱ ቀጠለ – እስካሁኒቷ ወያኔያዊት ዘመነ ፍዳ ወፃማ ቅጽበት ድረስ፡፡ ፈጣሪም የቅጣት ዓይነቶችን በመጠንም በዓይነትም በደረጃም እየለዋወጠ ፍጡራኑን – በአባይ ፀሐይ ትዕቢታዊ አገላለጽ “ልክ ማስገባቱን” እንደቀጠለ እስካሁን አለ፡፡ ግን ማን ልክ ገባ? ማንም! ሰውና ፈጣሪ ያልተገባ ፉክክር ውስጥ ገብተውና እልህ ተጋብተው በተለይ በአሁኑ ዘመን የለዬለት የጨበጣ ውጊያ ውስጥ የገቡ ይመስላል፡፡

ሦስተኛ ዓይነት መለኮታዊ ቅጣት በኢትዮጵያ በግልጽ ከታወጀ እነሆ 25 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ከውኃና ከእሳት ቀጥሎ ወደዚህች ዓለም የመጣው የቅጣት ዓይነት በሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ ለሙከራ ያህል በሚመስል አኳኋን ተግባራዊ የሆነ ሲሆን እሱም ትውልድን በትምህርትና በዕውቀት ማደደብና በቋንቋና በጎሣ መከፋፈል ነው፡፡ ይህ በተከታታይ ትውልዶች ላይ የተቃጣ ገሃነማዊ ቅጣት ከቀደሙት የውኃና የእሳት ቅጣቶች በበለጠ የሚያቃጥልና የሚፋጅ ነው፡፡ ሰዎች እንደቀላል ሊመለከቱት ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ቅጣቱ ጥይት ሳያባክን ትውልድን ማምከን የሚችል ከኒዩክሌር ቦምብ የበለጠ እጅግ አውዳሚና በቀላሉ ማንሠራራትም የማይቻልበት ነው፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ሂልተን አንድ የመጻሕፍት ምረቃ መርሐ ግብር ነበር፡፡ እዚያ ስብሰባ ውስጥ የነበረ አንድ ወዳጄ በአስቸኳይ እንደሚፈልገኝ ነገረኝና ምን ሆኖ ወይም ምን አጋጥሞት ይሆን ብዬ ተጣድፌ ላገኘው ሞከርኩ፡፡ ቀኑ ብሔራዊ የነፃነት ክብረ በዓል የሚከበርበት እንደመሆኑ ሥራ የለኝምና አንድ ቦታ ተገናኝተን ማርፈጃውን ስለታዘበው ነገር በቁጭት እየተንገበገበ ቀጣዩን ነገር አጫወተኝ፡፡

በሰባት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጁ የልጆችና ሕጻናት መጻሕፍት ሜጋ የመጻሕፍት አሣታሚና በቅርብ እንደተመሠረተ የተነገረለት ስፖትላይት የተባለ ድርጅት በጥምረት ዛሬ ጧት አስመረቁ፡፡ በዚህ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ በርካታ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎችና ጋዜጠኞች እንዲሁም በንባብ ዙሪያ የሚሠሩ መጻሕፍት አሣታሚዎችና አከፋፋዮች ተጋብዘው ብዙዎቹ ተገኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሚሠራው ታዋቂው የፎክሎርና የሥነ ጽሑፍ ምሁር ዶክተር ፈቃደ ትዛዙም (አዘዘ?) ተገኝቶ ንባብን በሚመለከት ከሕይወት ተሞክሮው በጥቂቱ የተጨለፈ አጠር ያለ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ ታዋቂ ደራሲያንና የመድረክ ሰዎችም ተጋባዥ ነበሩ፡፡ በጣም ደስ የሚል ነበር፡፡…

ወዳጄ ይህን ሲነግረኝ ቀዝቀዝ አልኩ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ብሎ በጥድፊያ እኔን መፈለጉ አላሳመነኝምና በአስቸኳይ ለምን ሊያገኘኝ እንደፈለገ ጠየቅሁት፡፡ ጓደኛዬ ንዴት እንጂ ንግግር ብዙም አይሆንለትም፡፡ ከፍ ሲል የነገረኝን በእርጋታ ከነገረኝ በኋላ በንዴት እየተንጨረጨረ እኔንም የሚያናድዱ ብዙ ቁም ነገሮችን ዘከዘከልኝ፡፡ የመጣጥፌ መሠረትም ይህ የነገረኝ ነገር ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ከወዳጄ ተሰናበቱ – ከኔ ጋር ጥቂት እንቆይ፡፡

ከጓኛዬ እንደተገነዘብኩት ዐማርኛን ጨምሮ ሰባት የልጆች የንባብ መጻሕፍት ተዘጋጅተው ለምረቃ በቅተዋል፡፡ ይህ በራሱ እሰዬው የሚያስብል ትልቅ መልካም ነገር ነው፡፡ ይሁንና የመጻሕፍቱ ይዘትና ቅርጽ እንዲሁም የመጻፊያ ሆሄያት ምርጫ ብዙ ማነጋገሩ አልቀረም፡፡ በሥፍራው ግን ይህን ነገር ማንም ደፍሮ እንዳላነሳ ወዳጄ ነግሮኛል፡፡

እንዲህ ያለ ነገር ውስጥ መግባት ጣጣው ብዙ መሆኑን ሁሉም ሳይረዳ አልቀረም፡፡ በዚህ ወያኔ በገነነበትና ያሻውን በሚያደርግበት አደገኛ ወቅት ሰዎች ትክክለኛ መስሎ የሚሰማቸውን ነገር በግልጽ ከመናገር ይልቅ (“ሽብርተኛ” ሆኖ ዘብጥያ ላለመውረድ ሲባል) አድምጡና ተመልከቱ የተባሉትን ብቻ አድምጠውና ተመልክተው ወደየመጡበት መሄድ የተለመደ ሆኗል – ጎመን በጤና፡፡

ከዐማርኛና ከትግርኛ በስተቀር በኦሮምኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ፣ በሃዲይኛና በሶማሊኛ የተዘጋጁት መጻሕፍት የተጠቀሙት ሆሄያት የላቲኑን ነው፤ ያሳየኝ ብሮሸርም ይህን ይጠቁማል፡፡ ይህ ነገር በርግጥ የየቋንቋዎቹ ተናጋሪ ኅብረተሰብ ምርጫ ቢሆን ችግር ባልነበረው፤ ምርጫው የወያኔ መሆኑን ለመረዳት ደግሞ እነዚህን መሰል መጻሕፍትና በራሳቸው ቋንቋ የራሳቸውን ቋንቋ ተምረው ሲያበቁ መጨረሻ ላይ የሚሰጧቸውን የፈተና ወረቀቶች ከፈተናው አዳራሽ እንደወጡ በመቀዳደድ አካባቢውን ጨረቃ በጨረቃ ማስመሰላቸው አንዱ ምሥክር ነው፤ እንዲያውም “ ልጆቻችን በአንድ የአካባቢ ቋንቋ ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ የሚያደርጉት የትም ሄደው ሥራ እንዳይዙና እዚሁ እንደኛው ገበሬ ሆነው እንዲቀሩ ነው” በሚል የየአካባቢው ሕዝብ እንደሚጮህ የታወቀ ነው – ሰሚ የለም እንጂ፡፡ በመሠረቱ አንድ ዜጋ የራሱን አንድ እና ለሁሉም የሚያገለግል ደግሞ አንድ በድምሩ ቢያንስ ሁለት ቋንቋዎችን ቢለምድ ሕዝብና ሀገር ይበልጥ ይጠቀማሉ እንጂ ጉዳት የለውም፡፡ ዜጎች በአንድ ክልል ተኮድኩደው ከአድማስ ወዲያ ሕይወት መኖሩን እንዳያውቁ ሆን ተብሎ በወያኔ የሚሸረበው ተንኮል ወያኔ አወራርዶ ሊጨርሰው የማይችል የታሪክ ዕዳ ተሸካሚ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሣያል፡፡ ሁሉም ሕዝብ የነዚህን እባቦች ተንኮል በእኩል ደረጃ በሚረዳበት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን በጣም አደገኛ ሁኔታ ከአሁኑ ሲያስቡት አስጨናቂ ነው፡፡ የሕዝብ መገናኛ ድልድዩ ሁሉ ፈራርሷል፤ ሃይማኖት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣የጋራ ማኅበራዊ ሥነ ልቦና… የመሳሰሉት ዕሤቶች የሕዝብ መገናኛ ድልድዮች ናቸው፡፡ ወያኔዎች እንዚህን ማስተሳሰሪያ ገመዶች በጣጥሰው አንዱ ከሌላው እንዳይገናኝና በምትኩ ሁሉም ፉዞ ሆኖ የነሱ አሽከርና ባሪያ እንዲሆን በከፍተኛ ደረጃ እየሠሩበት ነው – አብዛኛው ሕዝብም የተኛ ይመስላል፡፡ ችግሩ ታዲያ የተኛ የነቃ እንደሆነ ነው፤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ መንቃቱም የማይቀር ነውና፡፡

አንድ ማሳሰቢያ ልስጥ፡፡ እኔ በዘሬ ኢትዮጵያዊ ነኝ – ይህን ስል ግን ወያኔና የወያኔን ፍልስፍና የሚከተል ማንኛውም ወገን “ይህ ሰው ዐማራ ነው” ብሎ እንደሚፈርጀኝ እገምታለሁ፡፡ የማነሳው ጉዳይ ግን ከኔ ማንነትና ምንነት በዘለለ ትልቅ ሀገራዊ ውድመት የሚያስከትል መሆኑን ሁሉም ልብ ሊል ይገባዋል፡፡ እናም እኔ አሁን የምለው ከተቻለ ሀገሪቱን ከመፈራረስ የምናድንበትን መንገድ በጋራ እንፈልግ፣ አለበለዚያ ግን ማንም ተጠቃሚ የማይሆንባት ጥቂት ጮሌዎች ብቻ በሀብትና በሥልጣን ሊያውም ለተወሰነ አጭር ጊዜ ተምነሽንሸውባት በቅርብ ለይቶላት የምትጠፋ ሀገር ውስጥ እየኖርን እንደሆነ እንገንዘብ እያልኩ ነው፡፡ ዐማራን ለማዳን ወይ ስለዐማርኛ ተጨንቄ ወይ ወያኔ በ“ካህናትና ጳጳሣት” ካድሬዎቹ ድራሹን ስላጠፋው ሃይማኖት ተጠብቤ… እንዳይመስላችሁ፡፡ እንዲያውም በዐማራ ምክንያት ወያኔና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያንና ቀሪውን ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጋውን ሕዝብ ከሚያጠፉ በ20 ሚሊዮን ገደማ የሚገመተው ከወያኔ ጭፍጨፋና ዕልቂት የተረፈው የዐማራ ሕዝብ በሌላ ሀገር ውስጥ ባዶ ቦታ ተፈልጎለት እዚያ ሄዶ ቢሠፍር የምመርጥ ሰው ነኝ – ለእሥራኤላውያን ታስቦ እንደነበረው፡፡ እስኪ ሌሎቻችሁ እንኳን ራሳችሁን አድኑ፤ ሁሉም ተያይዞ ሞኝ አይሁን፤ የዚህን ዐውሬ የትግሬዎች ቡድን አንደርባዊ ድግምቱንና ትብታቡን አፍርሱበትና ራሳችሁን ነፃ አውጡ፡፡ ለመሆኑ ማን ነው ከወያኔ የጥፋትና የውድመት አዙሪት ነፃ የሆነ? የትኛው ጎሣ ወይም አካባቢ ነው ከወያኔ ቀረቤታና በወያኔ ችሮታ የተጠቀመ? ኦሮሞ? ሶማሌ.? አፋር? ጋምቤላ? ቤንሻንጉል? ከድንጋያማ የተራቆተ መሬት የመጡ ቀጫጭንና ከሲታ ወንድሞቻችን ዛሬ እኛን እርስ በርስ እያባሉ እንደጉማሬ በልተው እንደዝኆን ሲወፍሩ ባይናችን በብረቱ እየተመለከትን የምንገኝ አንዳንድ ቂሎች በጋራ ጠላቶች መሠሪ የፈጠራ ወሬ እየተነዳን አሁንም የፈረደበት ዐማራ ላይ እንረባረባለን፤ የሞተን ፈረስ መጋለብ – የደረቀን ወንዝ መሻገር የጀግንነት መገለጫ አይሆንም፡፡ ትኋንን በጠበንጃ፣ ቁንጫን ደግሞ በርግጫ መግደልም የሚያስፎክር ጀብድ አይደለም፡፡ እውነትን ከሀሰት አበጥሮ በመለየት ሁነኛ ዘመድን ማወቅ አንዱ የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ እንደቦይ ውኃ በነዱት መነዳትና እንደክርስቶስ ዘመን “ስቅሎ ሰቅሎ” ብሎ በንጹሕ ዜጎች ላይ “ሆ!” እያሉ መዝመትም በትንሹ ቂልነት ነው፡፡ ጠላትንና ወዳጅን አለመለየት ለከፋ ችግር ይዳርጋል፡፡

ዐማሮችን መጥላትና ማጥፋትም ይቻላል፤ ቀላልም ነው፡፡ እንግሊዞችን መጥላትና – ቢያንስ በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ – ማጥፋትም ይቻላል፤ ይህም ቀላል ነው፡፡ ዐማርኛንና እንግሊዝኛን ግን ማጥፋት ይቅርና ለማጥፋት ማሰብ በራሱ ዕብደትና ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍልም ነው – ኢትዮጵያን በሚመለከት እየታዘብነው እንዳለነው ይህ ዓይነቱ የወፈፌ ሥራ የትውልድን መቃተት ያስከትላል፡፡

ዐማርኛን ማጥፋት ዐማሮችን እንደማጥፋት ቀላል ቢሆን ኖሮ እስካሁን ትግርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኖ ነበር፡፡ ወያኔዎች ግን የለየላቸው ደንቆሮና ልበ-ሥውራን በመሆናቸው ይህ ታሪካዊ ኹነት እንኳን ሊገባቸው አልቻለም፡፡ የነሱን ልጆች ሸገር ላይ ለምን ዐማርኛና በዐማርኛ ያስተምራሉ? ለምን ወደ ቻይና፣ እንግሊዝና አሜሪካ እየላኩ ለሥልጣኔ ቅርብ ያደርጓቸዋል? ለሌላውስ ድንቁርናን ለምን ይፈርዱበታል?

ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታስ በትግራይ ክልል ለምን ዐማርኛ ይነገራል? ገዢዎቸ ራሳቸው ለምን ዐማርኛን ይለምዳሉ? አሃ! ተረዱታ! ጀምጀምንና ጃንጀሮን – ኮንሶና ሙርሲን፣ አሪና በርታን  ለማስገበር፣ ሲዳማንና ወላይታን እንደልብ ለማዘዝ፣ ጠምባሮንና ደራሳን ለማሽቆጥቆጥ፣ አኝዋክንና ኑዌርን ለመቦጥቦጥ፣ ቦንጋንና ቤንቺ ማጂን ለመርገጥ፣ ሃዲያንና ሐረሪን ለመንዳት፣ ኦሮሞንና ሶማሌን ለመግዛት፣… ከዐማርኛ የበለጠ መሣሪያ እንደማያገኙ ዐወቋ! ግን ግን የቋንቋው ጥቅም ገብቷቸው ሲያበቃ ለተናጋሪዎቹ ያላቸው ንቀትና ጥላቻ አላፈናፍን ብሏቸው ይሄውና ይህን ቋንቋ ለማጥፋት – የሚበሉበትን ወጪት ሰባብሮ ለመጣል – ያቺ ሞኝ ሴት በተረቱ አደረገች ተብላ እንደምትታማበቱ ያለ አስቂኝ ግን አጓጉል ነገር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ሞኟ ሴት ግን ምን አደረገች በል? እሷማ ባሏን የጎዳች መሰላትና ሰውነቷን በጋሬጣ ዘነጣጠለችዋ፡፡ ጅል ሴትና ደንቆሮ ወያኔ አይግጠማችሁ፡፡

ዐማርኛ የሙጃ ሣር ነው፡፡ ዐማርኛ ሰንሰልና ሸምበቆ ነው፡፡ ዐማርኛ ባማርኛ አንፋር ወይም ነጭሎ ብለን የምንጠራው የተክል ዓይነት ነው፡፡ የትም ቢሄድ አካባቢውን በቀላሉ ይለምዳል፤ ሞኛሞኝ ቢጤ ነው፡፡ ዐማሮች የሚባሉ ወገኖቻችን እንደዐማርኛ ገርና ለማዳ ስለመሆናቸው አታስወሹኝ እምብዛም አላውቅም፡፡ ዐማርኛ ግን ቀደም ሲል በተፈጠረለት ታሪካዊ አጋጣሚ የተነሣ በመላው ኢትዮጵያ ተሠራጭቶ ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ከጥንት ጀምሮ እየደከመ ይገኛል፡፡ ትርፉ ድካም ብቻ ሆኖ መቅረቱ ግን ያሣዝናል፡፡ ለዚህ ልፋቱ – ለዚህ ከ80 በላይ ለሚገመቱ ጎሣና ነገዶች የጋራ የመግባቢያ መሣሪያ ሆኖ ማገልገሉ ባለቤቶቹን ሊያስወድስና ሊያሸልም ሲገባ በተገላቢጦሽ ሽልማታቸው ውግዘትና ጥይት መሆኑ ምን ዓይነት የታሪክ ምፀት እንደገጠመን ጠቋሚ ነው፡፡ ወያኔ በጨለማ ውስጥ የሚኖር የድንጋይ ዳቦ ዘመን ፍጡር ሆኖ እንጂ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ንጉሥ – ለሀፄ ዮሓንስ ጮሙሮ –  ትግሬም ይሁን ኦሮሞ ወይ ዐማራና ቅልቅል ሁሉም የተጠቀሙት ዐማርኛን ነው – ዐማርኛ ኮከቡ ሰምሮለት ላገዛዝ ሳያመች የሚቀር አይመስለኝም – ለተናጋሪዎቹ ጠንቅ ሆነ እንጂ፡፡ ሁሉም ነገሥታትና ገዢዎች ዐማርኛን መጠቀሙ ስላመቻቸውና ስላተረፉበት እንጂ ወደውትም ላይሆን እንደሚችል ቢያንስ በጥርጣሬ ደረጃ መጠርጠር ይቻላል፡፡

የቋንቋ ልደት፣ ዕድገትና ሞት የራሱ አካሄድ አለው – እንደወያኔ በዐዋጅና በጦርነት አንድ ቋንቋ አይወለድም ወይም ተወልዶ እንኳን ቢሆን አያድግምና ለተፈለገው ቁም ነገር አይበቃም፤ ለዚህ ነባራዊ እውነት ዋናው ምሥክር ወያኔዎች ራሳቸው ናቸው፡፡ እንደነሱ ፍላትና ምኞት ቢሆን ኖሮ ትግርኛ የአሁኒቷ ኢትዮጵያ የጋራ ቋንቋ ሆኖ ነበር – ግን እባብ ልቡን ዐይቶ … እንደሚባለው በፈለጉት መሣሪያ ቢወጉት ዐማርኛ አልሞት አላቸው – እንደነሱው አፍር ልሶ ከመቃብሩ ይነሣል፤ እንዲያውም ይባስ ብሎ እየገነነ መጣና በዋሽንግቶን ከተማ ሣይቀር የሥራ ቋንቋ እስከመሆን ደረሰ፡፡ እንጂ እንደነሱ ጥረት – እንደነሱ የባህል ወረራ – እንደነሱ መፍጨርጨር አዳሜ በአሁኑ ሰዓት አብዚሎ ቅብዚሎ እያለች ሁሏም በትግርኛ ትግባባ ነበር – በመሠረቱ ትግርኛ ብሔራዊ ቋንቋ መሆን አለመሆኑ አያሳስበኝም፤ የሚያሳስበኝ የመሆኛውና ያለመሆኛው ሥልት ነው፤ እንጂ እንኳንስ ጠንቅቄ የምናገረው የእናቴ ወገኖች ቋንቋ በአግባቡና በደንቡ ከሆነ የዝንጀሮም “ቋንቋ” ብሔራዊ ቀርቶ የዓለምም ቢሆን በደስታ እቀበላለሁ፡፡

የትግርኛን ቋንቋና የትግራይን ባህል በሌላው ላይ በግዴታ ለመጫን የሚያደርጉት ሙከራ ቀላል አይደለም – ይህ ደግሞ በጣም ያናድድሃል፤ የምትወደው ብትሆን እንኳን እንድትጠላው ሊያደርጉህ ይችላሉ – ፈቃዳችሁ ከሆነ እዚች ላይ አንዲት ፈረንጅኛ አባባል ልጥቀስ መሰለኝ – “A man can take a horse to a river, but twenty cannot make it drink.” አዎ፣ ሙዚቃውን ልትከፍት ትችላለህ – ግን ማን ነው በፍቅር የሚያዳምጥልሀ? እንዴ፣ ከዚህ ከጀመርኩላችሁ ከዘፈን አቅም እንኳን ሚዲያው ሁሉ በዐዋጅ የተገደደ ይመስል ብዙውን ጊዜ ካለትግርኛ ሌላ ዘፈን አይከፍትም – ቲቪውም፣ ኤፍ ኤሙም፣ የባዛርና የንግድ ትርዒት ዝግጅቱም፣ ዕድሩም ሰምበቴውም ምኑም ምናምኑም… ኮበለይና ተበራቢረይ ሲል ነው የምታደምጡት – ይቅርታችሁንና ብዙዎቻችን ደግሞ ማሽቃበጥ ስንወድ! እነዚህን የ simple  psychology ተጠቂ ዶንኪሾታዊ ወንድሞቻችንን በቀላል ነገር የመደሰትና በትንሽ ድል የመኮፈስ ተፈጥሮ የምናውቅ አጎብዳጆች እነሱን ለማስደሰት የምናደርገው አንዳንድ ነገር ለትዝብት ሲዳርገን አስተውላለሁ – ያ ዓይነቱ ራስን ያለመሆን ችግር ደግሞ በጣም ያሳዝነኛል – እነሱ ራሳቸውም ሳይታዘቡን የሚቀሩ አይመስለኝም – ነገ ደግሞ በሌላው ቀን በቅጽበት ሌላ እንደምንሆን ግልጽ ነው፡፡… የትምህርት ቤቶች ሚኒ ሚዲያዎች እንኳን ባቅማቸው ካለበት የተጋባበት ሆነው በዕረፍት ሰዓታቸው የሚለቋቸው ዘፈኖች ብዙዎቹ ትግርኛ ናቸው፡፡ ሰው ደግሞ ጥልት! በኃይል የመጫን አሉታዊ ጎኑ እንግዲህ ይህ ነው፡፡ ወደህ ከሆነ ትጨፍርበታለህ፣ ትፎክትበታለህ ማነው ትፎክርበታለህ፣ ታገባበታለህ፣ ትፈታ…. አይ፣ አይ መፍታትስ ይቅር… ብቻ ከልብህ ትወደውና በሙዚቃው እንደልብህ በፍቅር ትመላለስበታለህ፡፡ ስትገደድ ግን ትጠላዋለህ፡፡ ተገድደህ እንድትቀበል ከሚደረግ ነገር የበለጠ የሚጠላ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ እንኳንስ ትልቁን የማንነትህን መገለጫ ይቅርና ከረሜላም ቢሆን በፈቃድህ እንጂ ተገድደህ ብላ ብትባል እንደኔ ሆዳም ካልሆንክ በስተቀር ያቅርሃል ወይም ቢያንስ ሊያቅርህ ይገባል፡፡

መጠጥ ቤቶች ካለትግርኛ አያዘፍኑም – ለነገሩ እነሱ እንኳ አብዛኛው ደምበኛቸው ትግሬ በመሆኑ ሊሆን ይችላል፤ እርግጠኛ ነኝ – የዚህ ዘመን የሆቴልና የመዝናኛ ሥፍራዎች ደምበኛ ሲታይ በአነስተኛ ግምት ከ60 በመቶ በላይ ትግሬ ነው፡፡ ጎበዝ መደባበቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ እንዲህ የምለው ደግሞ አንዱን በመጥላት ወይም ሌላውን በመውደድ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከዘር ሐረግ አንጻር ዐማራ ቢቀቀል አይሸተኝም፡፡ በተቃራኒው አንድን ትግሬ አንድ ሰው – ምናልባትም ዐማራ – አላግባብ ሲበድለው ባይ ያን ዐማራ እኔ ነኝ ቀድሜ የምፋረደው፡፡ እኔ እንዲህ ነኝ፡፡ ሁሉም እንዲህ ይሁን፡፡ ሰውን በሰውነቱ እንጂ በሰው ሰራሽ ነገሮች ፈርጀን በእንስሳዊ ባሕርይ አንነዳ፡፡ ማን ነው በፈቃደኝነት ዐማራ ወይ ትግሬ የሆነ? እኔ በተወለድኩበት ቤተሰብ ውስጥ እንድወለድ ለእግዜር ያስገባሁት ማመልቻ የት ነው የሚገኘው? ምን ዓይነት የሚጎመዝዝ ቀልድ ነው ይሄ ኦሮሞ፣ ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ሽናሻ… የሚሉት ፈሊጥ? ማን ይሆን ይህን የሰው ግርድና አመሳሶ የሚለይ ቆሻሻ ነገር ወደዚች ምድር ያመጣብን?

እደግመዋለሁ – ዐማሮች በዐማርኛ ተጎዱ እንጂ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ ቋንቋ እንዲያውም ከናካቴው ባይፈጠር ይሻላቸው ነበር፡፡ ለጥፋትና ውድመታቸው፣ ለስደትና መከራቸው ዋና ምክንያት ሆነ እንጂ የጠቀማቸው አንዳችም ነገር የለም – በስማቸው የተጠቀመ የየትኛውም ዘር ሹምባሽና አገረ-ገዢ ሁሉ ጥቁር ጠባሳውን ወደነሱ እያላከከ ጦሱጥምቡሱ ተረፋቸው እንጂ ዐማሮች ባማርኛ አልተጠቀሙም፡፡ ይህ በጣም አሣዛኝ ነገር ነውና ሁላችንም ለዐማሮች እንዘንላቸው፡፡ በዚህ ሩዋንዳዊና አርመናዊ የዕልቂታቸው ዘመን ካለኛ ማን አላቸው?

ቋንቋ በመሠረቱ ከሸሚዝና ከኮት የዘለለ ጥቅምም ሆነ አስፈላጊነት የለውም፡፡ ሁላችንም ከኅሊና መታወር የተነሣ “ያንተ ቋንቋ፣ የኔ ቋንቋ” እንላለን እንጂ የማንም ቋንቋ የሁሉም ነው፤ የሁሉም ቋንቋ ደግሞ የማንም ነው፡፡ ያንተ ሊባል ይችል የነበረው በትውልድ እንደ አንድ ባሕሪያዊ ስጦታ ብታገኘው ነበር – ለምሣሌ በጄኔቲክ ውርስ ከአባትህ ልትወርሰው እንደምትችለው ሸፋፋ አረማመድ ማለቴ ነው፡፡ ቋንቋን ግን ከሚነገርበት አካባቢ ከራቅህ አታገኘውም – ወይም በሕጻንነትህ ወደሌላ ቦታ ብትወሰድ የዚያን አካባቢ ቋንቋ እንጂ የዘመዶችህን ቋንቋ ጆሮህን ቢቆርጡት አትሰማም፤ጭራሹንም ያለ ቋንቋ ቀርተህ እንደሌሎች እንስሳት ጓደኞቻችን ለምሣሌ እንደላም “እምቧ” እያልክ ልትኖርም ትችላለህ – በከብቶች መሀል ከነሱ ጋር ብቻ እንድታድግ ከተደረገ፡፡ ወያኔዎች ግን ይህን እውነት አያውቁም ወይም ሊያውቁ አይፈልጉም፡፡ ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪ (ትግሬ) ሰው ለነሱ እግዚአብሔራቸው ነው – ዘረኝነት የፈጣሪን ቦታ የተካላቸው የአምልኮት ጽላታቸው መሆኑን መርሳት የለብንም፤ ትግሬ ማለት ለነሱ በምንም ነገር የማይደራደሩበት አካላቸው አምሳላቸው ነው – አጠፋ አላጠፋ፣ ንጹሕ ሆነ ወንጀለኛ ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ የጠባብነት ወረርሽኝ የሚያሰቃየው ሰው በዘመናዊ ፈሊጥ ከ”ዕውቀት የፀዳ” በመሆኑ ልክ እንደከብት መሰሉን እየፈለገ እንደከብት ይተሻሻል፤ ሌላውን ደግሞ በጠላትነት ፈርጆ ባገኘው ቀንድ ሁሉ እያሳደደ ይወጋዋል፡፡ ለዚህ ነው ወያኔዎች የነሱን ቋንቋ የማይናገርንና ትግሬ ያልሆነን ሰው ፍዳውን እያሣዩ መፈጠሩን እንዲጠላ የሚያደርት፡፡ የዕውቀት አድማሳቸውም ከአፍ እስከ አፍንጨቸው እንኳን አይደርስም፡፡ ዶክተርና ፕሮፌሰር ተብየዎቹም ቢሆኑ ዕውቀታቸው ያን ያህል ነው – ድግሪውን በግዢ ካላመጡት ያውም፡፡ ትምህርት ደግሞ የውስጥ ዐይንን – እንደሎብሳንግ ራምፓ አባባል ሦስተኛውን ዐይን – ካልከፈተ ዋጋ የለውም፡፡ ያ ሁሉ በትምህርት ያሣለፈው ጊዜ ልፋት ነው፡፡ ብዙ ዓመት ተምሮ መደንቆርን ነው ያተረፈው፡፡ ተማረ የተባለ ሰው በትንሹ ዘረኝነትን መፀየፍ ይኖርበታል፤ በሰው ልጆች እኩልነት ማመን ቀዳሚው የመማር ጥቅም ሊሆን ይገባል – አለዚያ ያ ተማርኩ የሚል ሰው ደደበ እንጂ አልተማረም፡፡ ለነገሩ መማር ማለት መደንቆርም እንደሆነ የሚያምኑ ፈላስፎች አሉ፡፡

ጠባብነትና የግንዛቤ ዕጥረት ደግሞ ጓደኛሞች ናቸው፤ ብዙ ነገርም ያሳጡሃል – ለምሣሌ ማኅበራዊ እንስሳነትህን በማስረሳት የሁሉምነትህን ትተህ የጥቂቶች ወገን ብቻ እንድትሆንና ለጥቂቶች ልብህን ለብዙዎች ግን ጥርስህን እንድትሰጥ ያስገድዱሃል፤ ሃይማኖትህን ያስክዱህና በዘረኝነት ልምሻ ኮድኩደው በከረፋ መሬት ላይ የዘውግ አባላትህን ትፈልግ ዘንድ የእንፉቅቅ ያስኬዱሃል፤ ከሌላ ዘውግ ጓደኛና ወዳጅ ቢኖርህ እሱንም ያስክዱህና በጠባቧ የዘውግ ክፍልህ አውርደው የገማ የገለማ የአጥንትና ደም ጭቃ ውስጥ እንድትንቦራጨቅ ያደርጉሃል፡፡ ዘረኝነትን ምናልባት ከሆነልህ በጸሎትና በጸበል እንጂ በትምህርትና በሕይወት ተሞክሮ በቀላሉ አትገላገለውም፡፡ ቀያጅ ነው፤ ባሪያው ካደረገህ እንደ አደንዛዥ ዕፅ ሱስ፣ እንደሀሽሽና ሱረት ፍዳህን ሳያበላህ አትገላገለውም፡፡ ብቻ ጠባብነትና ዘረኝነት መዘዛቸው ብዙ ነው ወንድሜ፡፡ እግዜር ይጠብቅህ እንጂ በተወርዋሪ ኮከብ የብርሃን ብልጭታ በምትመሰል በዚህች ቅጽበታዊ የምድር ሕይወት ውስጥ የዘረኝነትን ደዌ ጨምሮ የማይታይ አበሳ የለም፡፡

በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ጠፋች ማለት ምን ማለት ነው? ብዙ ሰው ላይገባው ይችላል፡፡

በደምቢ ዶሎ ከተማ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በቢኤ ዲግሪ የተመረቀ አንድ ኦሮምኛ ተናጋሪ ወጣት በዚሁ በወያኔ ዘመን ለሥራ ፍለጋ አዲስ አበባ ይመጣል፡፡ ማስታወቂያ ያነብና እኔ የማውቀው አንድ ትምህርት ቤት ሄዶ ለእንግሊዝኛ አስተማሪነት ያመለክታል፡፡ የመመረቂያ ውጤቱ ኤ በኤ ስለነበር ለቃለ መጠይቅ ከተመረጡት ውስጥ ስሙ ይካተትና በቀጠሮ ይጠራል፡፡ ፈታኞቹ አንድ ፈረንጅና ሁለት ሀበሾች ናቸው፡፡ (የዘመናችንን የውጤት መግለጫ ካርድ ስናይ “ቢ” “ሲ”ና “ዲ” የት ገቡ ብለን መጠየቃችን አይቀርም፤ በተግባር ግን ዜሮ! በተለይ አንዳንድ የግል የትምህርት ተቋማት ተማሪን ለመሳብ ሲሉ …)

ብቻ የሚያሣዝን ነው፡፡ ጠፍተናል፡፡ ወያኔዎች ድራሻችንን አጥፍተውናል፡፡ ሰው ግን አላወቀም ወይም ጥልቅ የሆነ ክፍለ ዘመናዊ እንቅልፍ ውስጥ ነው፡፡ ያ ልጅ ራሱን እንዲያስተዋውቅ ዕድል ይሰጠዋል – በእንግሊዝኛ፡፡ ምንም ነገር መናገር ያቅተዋል፡፡ ፍርሀት እንዳይመስላችሁ – የችሎታ ማጠር ነው፤ ቋንቋውን ከየት ያምጣው? ዲግሪን እንደጠበል መርጨት እኮ በጣም ቀላል ነው – ደርግ የከፍተኛ መኮንንነትን ማዕረግ በ“ከዚህ መልስ ሻምበል፤ ከዚያ ታች ወዲህ ደግሞ ሻለቃ” እያለ በለብ ለብ ሥልጠናና አለልክ በተጋነነ ባዶ ጀብድ ያድል አልነበር? – አሁን የነወዩ ብሶ ቁጭ አለ እንጂ! ከበረሃ ትግል በቀጥታ ወደ ጄኔራልነት)፡፡ መቶ ዩንቨርስቲ መክፈት እኮ እጅግ ቀላል ነው – ለዚያውም በቢከፍቱ ተልባ የሚታወቁ ዩንቨርስቲዎችን ለታይታና ለዕቅድ ማስፈጸሚያ ብሎ መክፈት – ባገር ሀብትም መቀለድ፡፡ … ልጁ በዐማርኛ ራሱን እንዲገልጽ በአስተርጓሚ ይጠየቃል፤ ዐማርኛውስ ከየት መጥቶ? በምን ይግባቡ? ፈረንጁም አፉን ይዞ ከተደመመ በኋላ እንዲህ ተብሎ እንዲነገረው መከረ፤” አየህ፣ አሁን እኛ ብንቀጥርህ የ4ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደመሆናቸው አንተን ያሣቅቁሃል፤ እነሱ ካንተ መቶ በመቶ ይበልጣሉ… ስለዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት የግል የቋንቋ ት/ቤቶች በአንደኛው ተመዝገብና ራስህን አሻሽል፡፡ ማሻሻልህን እርግጠኛ ስትሆን ለመቀጠር አመልክት፡፡ አሁን ግን እናዝናለን አልተገናኘንም…”፡፡

ዛሬ የተመረቁት መጻሕፍት በላቲን ነው የተጻፉት ተብሏል፡፡ በላቲን ሆሄ እንዲጠቀሙ የተሸረበውን ወያኔያዊ የፖለቲካ ሤራ ለጊዜው እንተወውና ወደ ወጪው እንሂድ፡፡ በዐማርኛ ቢጻፍ በ100 ገጽ ያልቅ የነበረ መጽሐፍ በላቲን ሲሆን በትንሹ 300 እንደሚሆን ታውቃላችሁ? ካላወቃችሁ ዕወቁ፡፡

ምሣሌ ማየት እንችላለን፡- “ወላይትኛ” ሊባል ሲችል  Wolayttotto Doonaa ተባለ ተሠልጥኖ ተሙቶ፡፡ ማየት ማመን ነውና ወላይታዎች የሆናችሁ ራሳችሁ ፍረዱት፡፡ 7 ፊደል በ17 ፊደል ተመነዘረ፡፡ እኔ በመሠረቱ አይደለም በላቲን በዐረብኛና በቻይንኛም ቢጻፍ ግድ የለኝም – ቋንቋውን ዱሮውንም አላውቀውምና፡፡ የወያኔ መሠረታዊ እሳቤ ግን ወላይታውንና ሌላውን ዘውግ ከኢትዮጵያዊነት የማስተሳሰሪያ ገመድ ለመነጠል ነው፡፡ እንጂ ወላይትኛ በዐማርኛ መጻፍ አለመጻፉ ያን ያህል አጨቃጫቂ ሆኖ እንዳይመስላችሁ፡፡ ወያኔ ደግሞ ቅራኔና ግጭትን እንደመፍጠር የሚያስደስተው ነገር የለም፡፡

ሌላውና ከዚሁ የሚያያዘው ነገር ጎሣዎች ሁሉ በየራሳቸው ቋንቋ እንዲማሩ ተደርጎ ዐማርኛን ሲቻል እንዲጠሉትና በመላ አቅማቸው እንዲዋጉት ያ ባይቻል ከዐማርኛ ርቀው እንዲያድጉና ከሌላው ዜጋ ጋር በምንም ዓይነት የጋራ ገመድ እንዳይገናኙ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ዕቅድ በሚገባ ተተግብሮ ፍሬ እያፈራላቸው ነው፡፡ አንድ የፌዴራል ተብዬ ሠራተኛ ከአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ ሲወጣ የክልሉን ቋንቋ የሚያውቅ ዐማርኛ ተናጋሪ ይዞ መሄድ አለበት፡፡ ሁሉንም ክልል ፀረ-ዐማርኛና ፀረ-አንድነት አድርገውታል፡፡

አብዛኛው የሥራ ዘርፍ በወያኔዎች በተያዘው አዲስ አበባ ውስጥ በየግንባታው ‹ሳይት› ሥራ ለመቀጠር የሚፈልግ ዜጋ ትግሬ ሆኖ መገኘት ይኖርበታል – በተፈጥሮ ወይም በገዢ – ዲቪ ይገዛል – ትግሬነትም ካወቅህበት ይገዛል፡፡ ትግሬ ካልተሆነ በቀላል መቀጠር የለም (የቅንፍ ጨዋታ፡- አንዲት አሮጊት በአንድ ረጂም ሠልፍ ገብተዋል፡፡ ምግብና ልብስ ለመቀበል ነው ሰዎቹ የተሰለፉት፡፡ ሴትዮዋ ግን ሠልፉ ውስጥ ለመገኘት መሥፈርት መኖሩንም ሆነ የመሥፈርቱን ዓይት አያውቁም፡፡ ተሠላፊዎቹ የኤች አይቪ ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ሴትዮዋ ተራቸው ደረሰና ማስጃቸውን ተጠየቁ፡፡ መሥጢሩን ካለማወቃቸውም በተጨማሪ ምንም ማስረጃ የላቸውም፡፡ ያኔ “አይ ፈጣሪየ፣ ለምንድነው ይህን በሽታ እንኳን ያልሰጠኸኝ?” በማለት በሽታውን ስላልሰጣቸው አማረሩት አሉ – ሆድ መጥፎ ነው፤ ከሰው በታች ያደርጋል- ያዋርዳል፤ እንደምናየው እንኳንስ ትግሬነትን የማይድን በሽታን ያስመኛል፡፡…) ሁሉም እንደውሻ ዘሩን እያነፈነፈ ነው ወዛደርና ኩሊ እንኳን የሚቀጥር፡፡ እናም መንጓለል አለ – አዳሜ የቀባጭ ምሷን እያገኘች ነው፡፡ በዚህ መልክ ሁሏም ዋጋ እየከፈለች ነው፡፡  በቀጣፊዎች ሸር በተፈጠረ ታሪካዊ ስህተት ለተጎዳ ዜጋ መቼም እሰይ አይባልም እንጂ ሁሉም ይህን ችግር መረዳቱ ጥሩ ነው ባንልም ክፉ አይመስለኝም – ትልቅ ዋጋ ከፍለህ የቀሰምከውን ትምህርት በቀላሉ አትረሳውምና፡፡

አዲስ አበባ የምትመጣ የክልል ሰው ፍዳዋን እያየች ነው፡፡ ከትምህርት ትምህርት የላት፤ ከችሎታ ችሎታ የላት፤ ከቋንቋ ቋንቋ የላት… ባዶዋን ትመጣና ዘበኝነትና ግርድና ባቅማቸው በቀላሉ የማይገኙ እየሆኑ ክፉኛ እየተቸገሩ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ቋንቋ ዋና መሣሪያ ነውና፡፡ ዘመናውያኑ ትግሬዎች ቋንቋቸው ከዐማርኛ እምብዝም ስለማይለይና ሥረ-መሠረታቸው አንድ ግንድ በመሆኑ ለመልመድ ብዙም አይቸገሩም፡፡ ከትግራይ ገጠር በመጡ በሁለትና ሦስት ወር ውስጥ ዐማርኛን አቀላጥፈው በመናገር ይሄን የዋህ የመሀል አገር ሰው በአሽከርነትና በግርድና ያንቆራጥጡታል – ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ አይደለም ብረት ይሰብራል፤ በተግባር አየን፡፡

አሁን ምን ይደረግ? እኔ እንጃ፡፡

Filed in: Amharic