>

ጦርነትን የሸሹ የመኖች ወደ ጅቡቲ ሲኮበልሉ ፣10 ሺህ ኢትዮጵያኖች ወደ የመን ይጎርፋሉ [ታምሩ ገዳ]

“ታጣቂዎች አራት ኢትዮጵያዊያኖችን ገንዘብ አምጡ ብለው አይኔ እያየ ገድለዋቸዋል” የሰደተኛው ትውስታ

Tamiru Geda 13052016-1በሰውዲ አረቢያ መራሹ ጦር የአየር ላይ ድብደባ እና በአርሰ በርስ ጦረነት እየፈራረሰች ያለቸው ጎረቤት የመን ዜጎቿ ነፍሳቸውን ለመታደግ ሲሉ ወደ ጅቡቱ ሲሰደዱ በተቃራኒው ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያኖች በአገራቸው እየደረሰባቸው ያለው የሰብ አዊ መብት ረገጣን በመሸሸሸ እና ለተሻለ ኑሮ ሲሉ እጅግ አሰከፊውን እና አሰቸጋሪዉን የበረሃ እና የባህር ላይ ጉዞ በማድረግ ወደ ሰላም አልባዋ የመን እየጎረፉ አንደሚገኙ ታውቋል።

በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ የሚያተኩረው የመንግስታቱ የመረጃ መረብ(IRIN) ማክሰኞ ግንቦት 10 /2016አኤ አ ባወጣው ዘገባ ባለፈው አመት(2015 ) ወደ የመን ከጎረፉት 90ሺህ ሰደተኞች ውስጥ 90% ያህሉ(ከመቶው ዘጠናው እጆች) ከኢትዮጵያ የተሰደዱ ሲሆን የተቀሩት ብቻ ከ ጎረቤት ሶማሊያ የመጡ ናቸው ብሏል። የኢትዮጵያዊያኑ ሰደት ዛሬም ያለማቋረጡን የገለጸው ዘገባው ባለፈው መጋቢት ወር ብቻ በ 10ሺህ የሚቆጠሩ ከኦሮሚያ ክልል የወጡ ወጣት ኢትዮጵያዊያኖች በአገራቸው ውስጥ ከደረሰባቸው በደል እና መገለል አኳያ ወደ ሰውዲ አሪቢያ እና የባሕረ ሰላጤው አገሮች ስራ ፍለጋ ለመጓዝ ሲሉ ወደ ሰላም አልባዋ የመን መሰደድን መርጠዋል ፣ ከእነዚህ መካከል ከ 65 በላይ የባሕር ላይ አውሬዎች ሲሳይ ሆነዋል።

በሶማሊ ላንድ እና በጅቡቲ በኩል ወደ የመን ከተሰደዱት ኢትዮጵያዊያኖች መካከል ከ አሊቲና/ትግራይ የተሰደደው የ 31 አመቱ ከማል ፈረጃ አንዱ ሲሆን ሰኣታት የፈጀብትን የባህር ጉዞውን አጠቃሎ ከየመን ዳርቻ ሲደረሱ የተቀበሏቸው ደላላዎች/ህገወጥ አሸጋጋሪዎች ሳይሆኑ የየመን ታጣቂዎች እንደነበሩ አወስቶ በወቅቱም ሰለደረሰባቸው ግፍ እና በደል ሲዘረዝር “ ከአንዲት ጠባብ ቤት ውስጥ ለሳምንታት አሰረውን ከአገር ቤት/ከ ኢትዮጵያ ገንዘብ እንዲላክልን ለዘመዶቻችን ስልክ እንድንደውል አሰግደዱን። ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ አራት ወገኖቻቸንን አይናችን እያየ ገደሏቸው “ሲል ሕይወቱን ብቻ ማትረፍ የቻለው ከማል አሰቀያሚው የሰደት ጠባሳውን ለኢሪን ዘጋቢ ተናግሯል።ባለቤቱን እና ልጁን ኢትዮጵያ ውስጥ ጥሎ ለተሻለ ኑሮ ወደ የመን የተሰደደው ከማል በአሁኑ ወቅት የየመኑ ጦርነት ጋብ እስኪል ድረስ የመን ወስጥ የጫት እርሻ ውስጥ በቀን ስራ በማገልገል ሰለ ስውዲ አረቢያ ጉዞው ኣና ህልሙ እየወጠነ ይገኛል።

በብዙ ሰደተኞች ዘንድ የተሻለች አገር ሆና የምትታየው ስውዲ አረቢያ በየመን ውስጥ በሚካሂደው ጦርነት ውስጥ እጆቿን በማሰገባቷ እና የየመን ሸማቂዎቹ/ሁቲዎች በበኩላቸው በጋራ ደንበሮች ላይ የፈተሻ ኪላዎችን በመቆርቆራቸው ሳቢያ የአትዮጵያዊያኖቹ ሰደተኞችም ከየመን ወደ ስውዲ አረቢያ የመሻገር እጣ ፈንታቸው የተመናመነ ሆኗል ተብሏል። ሰደተኞችን ይረዳ የነበረው የአለማቀፉ ከሰደት ተመላሶች ድርጅት (IOM) ባለፈው አመት ጥቃት ደርሶበት አምስት ኢትዮጵያዊያኖች መሞታቸውን ተከተሎ አገልግሎቱን ያቋረጠ ቢሆንም ካለፈው አመት ጀምሮ ከ 3ሺህ በላይ ሰደተኞችን ከየመን እስር ቤቶች ሰብሰቦ ወደ አገራቸው ወደ ኢትዮጵያ በፈቃደኝነት ያጓጓዘው ይሀው ድርጅት/IOM/መካከል የስውዲ አረቢያ ጉዞውን እውን ለማድረግ ከ ኦሮሚያ አካባቢ ከብቶቹን በመሽጥ ወደ የመን የተሰደደው የ 25 አመቱ አሊ አህመድ ኢብራሂም አንዱ ሲሆን አሊ ሰለ ወደፊቱ ተሰፋው ምን እንደሚያስብ ለኢሪን ዘጋቢ ሲናገር” በእውነቱ በአሁኑ ወቅት ምንም የማሰበው ነገር የለም ፣በኢትዮጵያ ውስጥ ተሰፋውም ጨልሞብኛል፣ ምናልባት የመን አንጻራዊ ሰላሟ ስታገኝ ዳግም ወደ የመን እሰደድ ይሆናል”ብሏል።

Tmairu Geda 13052016የዛሬ ስደስት ወራት ከአማራ ክልል ተነስቶ የቀይ ባህርን በማቋረጥ ወደ የመን የተሰደደው የ 40 አመቱ ኢብራሂም አሊ የሱፍ በበኩሉ የየመኑ ሰደቱ እንዳልተመቸው ፣ ስውዲ አረቢያም ብሯን እንደዘጋችበት ፣በሰነኣ/የመን የሚገኘውም የአኢትዮጵያ ኢምባሲም ጀርባውን እንዳዞረበት አምረሮ ይናገራል። በስተመጭረሻም”መሄጃው ጠፈቶን ወጥመድ ውስጥ እንገኛለን “ሲል ምሬቱን እና ሰጋቱን የገልጻል።

እኛም ብንሆን እነዚህ አገራቸውን ፣ ቤት ንብረታቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ጥለው እና ውድ እና መተኪያ የሌለው ነፍፍሳቸውን ሸጠው ለምይሳካው የሰድት ኑሮ የተዳረጉ እነዚህ በሺዎች የሚቆጠሩ ምስኪን ወገኖቻቸንን በትቻለን መጠን ልንድርሰላቸው እንደሚገባ ሊዘነጋ አይገባም ።

Filed in: Amharic