>

አሜሪካንን እያሳደዳት ካለው ጣረ ሞት ተጠንቀቁ! [ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም]

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

የትራምፕ ጣረ ሞት አሜሪካንን በማሳደድ ላይ ይገኛል፡፡

ሁለት እምነተ ቢስ ፖሊሶች ሁለት አፍሪካ አሜሪካዊ ዜጎችን ከገደሉ እና አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰው አምስት የዳላስ ፖሊስ ኃላፊዎችን ከገደለ እና ሌሎች ሰባት ሰላማዊ ሰዎችን ካቆሰለ ከቀናት በኋላ ዶናልድ ትራምፕ እራሱን የሕግ እና የስርዓት እጩ አድርጎ በመጥራት ይህንን አሰቃቂ ድርጊት ፖለቲካዊ እንደምታ ያለው ለማድረግ ሞክሯል፡፡ ትራምፕ እንዲህ በማለት አውጇል፡

“ሕግ እና ስርዓትን በከፍተኛ ደረጃ ማስከበር አለብን፣ ወይም ደግሞ ሀገር የሌለን መሆናችንን መቶ በመቶ እናቆማለን፡፡ ሀገር የሌለን መሆናችንን እናቆማለን፡፡ የሕግ እና ስርዓት እጩ እኔው እራሴ ነኝ፡፡ “

ትራምፕ ሂላሪ ክሊንተንን “ደካማ፣ ውጤትየለሽ እና አቅመቢስ ስትሆን በቅርቡ በኤሜል ያደረገችው የቅሌት ድርጊት ደግሞ እራሷን ብቻ ሳይሆን መላውን የሀገሪቱን ህዝብ የሚያስደነግጥ ጉዳይ ነበር፡፡ ሴትዮዋ እልም ያለች ቀጣፊ ውሸታም ናት ወይም ደግሞ ሙሉ በሙሉ ምንም ዓይነት ብቃት የሌላት ደካማ ፍጡር ናት፡፡ ከሁለት አንዱን ናት፡፡ ይኸ ነገር በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ እኔ በግሌ ይህች ሴት ሁለቱንም ናት“ ነበር ያለው፡፡

“ሕግ እና ስርዓት” የሚለውን የአነጋገር ፈሊጥ ሴናተር ባሪ ጎልድዋተር እ.ኤአ. በ1964 የእጩነት ጥቆማቸው ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ እንዲህ ከሚለው ንግግራቸው ጀምሮ ስሰማው ቆይቻለሁ፡ “እኛ ሬፐብሊካውያን ሕግ እና ስርዓትን ለማስከበር ኃላፊነቱን በዘለቄታዊ መንገድ መወጣት የሚችል መንግስት እንዲኖረን እንፈልጋለን፡፡“

ሪቻርድ ኒክሰን እ.ኤ.አ በ1968 ባደረጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ንግግር ይህንን ሀረግ እንዲህ በማለት ገልጸውት ነበር፡

“አንድ ሀገር ከፍተኛ የሆነው የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ስርዓት ባልተጠበቀ መልኩ ተለውጦ በሕግ አልበኝነት ስርዓት በምትጠቃበት ጊዜ፣ አንድ ሀገር ለዘመናት ሰፍኖ የቆየው የእኩልነት ዕድል ባልተጠበቀ ሁኔታ በአንድ ጊዜ በኃይል በዘረኝነት ድርጊት በሚተካበት ጊዜ እና የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ወደ ውጭ ሀገር ወይም ደግሞ በሀገር ውስጥ ወደማንኛውም ከተማ ያለምንም ፍርሀት እና የጥላቻ ተቃውሞ በሰላም ለመጓዝ የማይችል ከሆነ – ይህ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ አዲስ አመራር የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው… በዚህም መሰረት ሕግ እና ስርዓት እያሉ ለሚናገሩት ይህ አባባል የዘረኝነት መገለጫ ሀረግ ነው፣ እናም ለዚህ አባባል እንዲህ የሚል ምላሽ እነሆ፡ የእኛ ዓላማ ለእያንዳንዱ አሜሪካዊ ፍትህን ማጎናጸፍ ነው፡፡ በአሜሪካ ውስጥ ሕግ የምናስከብር ከሆነ ፍትህን ለማስከበር የሚያስችሉ ሕጎች ያስፈልጉናል“ ነበር ያሉት፡፡

ኒክሰን ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ይህ ሀረግ በሲቪል መብቶች ጥበቃ ወትዋቾች፣ የዱሮውን ኋላቀር ልማድ በማይቀበሉ ሰዎች፣ በተማሪዎች እና በጸረ ጦርነት ወትዋቾች ላይ ፖሊስ የኃይል እርምጃ ጀምሮ ነበር፡፡

እንደዚሁም ሁሉ ሮናልድ ሬጋን እ.ኤ.አ በ1964 ባደረጉት ንግግር ላይ ሕግ እና ስርዓት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በማድረግ ተናግው ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1981 ሬጋን ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ሕግ ማለት ጠንካራ ወግ አጥባቂ ዳኞችን መሾም እና ስርዓት ደግሞ በርካታ እስር ቤቶችን እንደ አሸን መፈልፈል ሆነ፡፡ የእስር ቤቶች ብዛት እ.ኤ.አ በ1980 ከነበሩበት ከ500,000 እ.ኤ.አ በ1994 ወደ 1.5 ሚሊዮን ከፍ በማለት በሶስት እጥፍ ጨመረ፡፡

ትራምፕ ስለሕግ እና ስርዓት ሲናገር በእርግጠኝነት ምን ለማለት ፈልጎ ነው?

ትራምፕ “አሜሪካንን ታላቅ እናድርጋት“ ሲል በእርግጠኝነት ምን ለማለት ፈልጎ ነው?

እስከ አሁን ድረስ አሜሪካ ታላቅ እንዳትሆን ኃላፊነት የነበረው እና አሁን አሜሪካንን እንደገና ታላቅ ለማድረግ የሚፈልገው ማን ነው? ሕግ እና ስራዓትንስ የማያከብሩ እነማን ናቸው?

ትራምፕ በክረምቱ ወቅት በርካታ የዘር ግጭቶች እንደሚኖሩ በመግለጽ እንዲህ በማለት በተከታታይ ተናግሮ ነበር፡ “በፖሊሶቻችን እና በሕግ አስከባሪዎች ላይ በሙሉ ያለንን ጥላቻ ለማቆም እና ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ጊዜው አሁን ነው…ማለቴ በበርካታ ከተሞች ታላቅ እና በጣም ታላቅ በሆነ ችግር ላይ ናችሁ፡፡ እናም ይኸ ችግር በዚህ ክረምት ወቅት የመጨረሻው ይሆናል ብዬ አስባለሁ“ ነበር ያለው፡፡

አምስት ፖሊሶች ከተገደሉ እና ሰባት ሌሎች ዜጎች ደግሞ ከቆሰሉ በኋላ ትራምፕ ሕግ እና ስርዓት የሚለውን ሀረግ የመጠቀሙን ጉዳይ አሳሳቢ ይሆንብኛል፡፡

ይህ ጉዳይ አሳሳቢ ይሆንብኛል ምክንያቱም ያ ሀረግ አፍሪካ አሜሪካዊ ወንጀለኞች ስለሆኑ በፖሊስ ኃይል መጨፍለቅ አለባቸው በማለት ሁልጊዜ ስም በማጥፋት እና ጥላሸት በመቀባት ተግባር ላይ የሚውል ሀረግ ስለሆነ ነው፡፡

ሆኖም ግን የትራምፕን የህግ እና ስርዓት ሀረግ ገለጻ እንደ ሌሎች በዘር፣ በጎሳ እና በኃይማኖት ጉዳዮች ላይ መሰረት አድርጎ እንደሚሰጠው ቆጥቋጭ መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡

ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ ሙስሊሞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ክልከላ እንደሚጥል ቃል ገብቷል፡፡

ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆኖ ከተመረጠ ሴት ደፋሪዎች እና ኃይለኛ ወንጀለኞች አድርጎ የሚቆጥራቸው እና እኔ ደግሞ ጥቂቶች ጨዋ ሰላማዊ የሆኑ ሰዎች አድርጌ የምቆጥራቸው  ሜክሲኮናውያን ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታላቅ የአጥር ግንብ እንደሚገነባ ቃል ገብቷል፡፡

ከአንድ ሳምንት ትንሽ ቀደም ብሎ ትራምፕ ሂላሪ ክሊንተንን በመሳደብ፣ በማዋረድ እና ሁሉንም የኃይማኖት ቡድን በመናቅ አሳንሶ ስም የማጠልሸት ተግባርን ዒላማ ያደረገ ዘለፋ አካሂዷል፡፡

በሚቀጥለው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ የሬፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆኖ በይፋ ይሰየማል፡፡

የትራምፓውያን ጣረ ሞት አሜሪካንን ያሳድዳል!

ከ84 ዓመታት በፊት ትራምፓውያን ሀከንክሬውዝ/ስዋስቲካ (የናዚ ቡድን) በማለት በሌላ ስም በጀርመን ሀገር ስልጣንን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ ሀከንክሬውዝ የአራያኖችን የበላይነት ያረጋገጠ ነበር፡፡

አብረሀም ሊንከን በጌትስበርግ ንግግራቸው እንዲህ በማለት አውጀው ነበር፣ “ከ87 ዓመታት በፊት ቀደምት አባቶቻችን በዚህች ምድር ላይ ነጻነትን የምታጎናጽፍ እና ሁሉም ሰዎች እኩል ሆነው ተፈጥረዋል ለሚል መርህ እራሷን ያስገዛች አዲስ ሀገር ተፈጥራለች፡፡” ባሮች ነጻ ሆነዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2016 አዲሱ ፋሽስዝም/neo-fascism የዘር መርዙን በሚረጭ፣ የውጭ ዜጎችን በሚጠላ፣ የጾታ አድልኦን በሚፈጽም፣ ሴቶችን በሚጠላ፣ የማስፈራራት ሽብርን በሚነዛ፣ የዘር ህዋስ ተመልሶ ይመጣል በማለት የበላይነቱን በሚለፍፍ በአይሁዶች ላይ የዘረኝነት አድልኦን በሚፈጽም እኩይ ምግባራት በመዘፈቅ በአሜሪካ ውስጥ መጥፎ ገጽታውን በማሳየት እና መንታ ምላሱን በማውለብለብ ላይ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ ታህሳስ 2015 ባወጣሁት ትችቴ “የአሪያኖች መነሳሳት! እና የትራምፕ የአራያን መንግስት የማቋቋም ወይም የትራምፕ- አሪያን የዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን ታላቅ የማድረግ የተማጽእኖ ንግግር“ በሚል ርዕስ የተሰማኝን ታላቅ ሀዘን ገልጨ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከሰባት ወራት በኋላ በዚህ ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ የሬፐብሊካን ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆኖ መመረጥ ፍርሀቴን እና ስጋቴን የበለጠ አስፈሪ አድርጎታል፡፡

ትራምፕ በሬፐብሊካን ፓርቲ ውስጥ የትኛውን ሬፐብሊካን እንደሚወክል አላማወቄን አምኛለሁ፡፡

ትራምፕ ለመወከል እየጮኸለት ያለው የሬፐብሊካን ፓርቲ የአቤ ሊንከንን ፓርቲ ከሆነ ፓርቲውን የመሰረተው እና ከፍተኛ እገዛ ያደርግለት የነበረው ከመቃብር ውስጥ ሆኖ ይገለባበጣል ለማለት ብቻ ነው የምችለው፡፡ (ሊንከን የሬፐብሊካን ፓርቲ የመጀመሪያው እንደሆነው ሁሉ ትራምፕ ደግሞ በተጻራሪ መልኩ የፓርቲው ፍጻሜ የመጨረሻው ሊሆን ይችላልን?)

ትራምፕ ለመወከል እየጮኸለት ያለው የሬፐብሊካን ፓርቲ የወግ አጥባቂዎች ፓርቲ ከሆነ ትራምፕ የዚያ ዓይነት ለመሆን አይችልም ምክንያቱም ለወግ አጥባቂነት እና ለወግ አጥባቂነት እሴቶች ሙሉ በሙሉ ንቀት አለው፡፡ ትራምፕ ለምሁራን የማይስማማ እና በተራው ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ፖለቲካን በማራመድ እራሱን ብቻ በመወከል የነጭ የሰራተኛ መደቦችን በመያዝ እና ሬፐብሊካንን በማሳዘን የኋይት ሀውስን ቤተመንግስት የመቆጣጠር ዓላማን ሰንቆ ነው በመንቀሳቀስ ላይ ያለው፡፡

በርካታ ጠንካራ ሬፐብሊካኖች በትራምፕ ጸረ ሬፐብሊካን ፓርቲ አቋም ላይ እተሰላቹ እና ተቀባይነት የለውም እያሉ መጥተዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2012 የሬፐብሊካን ዕጩ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሚት ሮምነይ አሁን በቅርቡ የትራምፕ ፕሬዚዳንት መሆን ማለት የዘረኝነት መስፋፋት እና የታጋሽነት እጦት የተንሰራፋበት እንደዚሁም ደግሞ የሴቶች ጥላቻን የሚያራምድ – እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአሜሪካ ስብዕና ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የሚያስከትሉ ናቸው በማለት ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ጸረ ታጋሽነቱን ለመግለጽ ሂላሪ ክሊንተንን ባለስድሰት ቀስት የትሪያንግል ምስል በሆነ በ100 ዶላር ቢል ቦርድ ላይ “እስከ አሁን ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ሙሰኛ“ የሚል ጽሁፍ በማጻፍ የስም ማጥልሸቱን ተግባር ቀጥሎበት ይገኛል፡፡

ትራምፕ በሂላሪ ክሊንተን ላይ እያሳየ ያለው የጸረ ታጋሽነት እይታ ከናዚ የሕዝብ መረጃ እና ፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር የበለጠ ነው፡፡

በአጠቃላይ እጅግ በጣም የወረደ እና አሳፋሪ ነገር ነው፡፡

በናዚ ጀርመን የአይሁድ ህዝቦች የጁዳይዝም እምነት ተከታዮች ለመሆናቸው እና ከሰው በታች የሆነ ስብዕና እንዳላቸው መገለጫ እንዲሆን መለያ ምልክት የሚሆነውን ልብስ እንዲለብሱ ይገደዱ ነበር

ናዚዎች በአይሁዶች ላይ ቀስ በቀስ ባህላቸውን እና የፖለቲካ እይታቸውን የሚቀይር በጣም አስቸጋሪ እና መጥፎ ውሸት በመዋሸት እኩይ ምግባራትን ይፈጽሙ ነበር፡፡ አይሁዶች የጀርመንን (አራያን) ህዝቦች ደም የሚመጡ፣ ባህላቸውን የሚበክሉ፣ ኢኮኖሚያቸውን በበላይነት የሚቆጣጠሩ እና ህዝቡን የሚበዘብዙ እና የሚቆጣጠሩ  ተደርገው እንደ ውጭ ዝርያ ይታዩ ነበር፡፡

ናዚዎች ፖስተሮችን፣ ጋዜጦችን፣ ፊልሞችን እና የሬዲዮ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ስም እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን በመላ አውሮፓ የሚገኙ የአይሁዶች ከተሞች በሙሉ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና ከዚህ በፊት በአስከፊ የድህነት መረብ ውስጥ ተተብትበው የመገኘታቸው ሁኔታ ነበር፡፡

ወዲያዉኑ ናዚዎች እነዚህ ያልሰለጠኑ ዘላኖች፣ የጆህቫ ምስክሮች እና ሌሎች የአካል እና የአእምሮ ብቃት የሌላቸው በአራያን አባቶች መሬት ላይ መኖር የለባቸውም በማለት ስም ዝርዝራቸውን እየለቀሙ መኖር የለባቸውም የሚለውን ውሳኔ አጸደቁ፡፡

እ.ኤ.አ መስከረም 1935 ናዚዎች በጀርመን ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ሙሉ የፖለቲካ መብት ያላቸው እና ምንም ዓይነት የፖለቲካ መብት የሌላቸው ዜጎች በማለት መመደብ ጀመሩ፡፡

በናዚዝም እና በትራምፓውያን መካከል ሁለት ልዩነቶች ብቻ አሉ፡፡

ናዚዎች የእራሳችን ግዛት ነው በማለት በምስራቅ አውሮፓ እና ከዚያም በላይ ጦርነት በማወጅ የጀርመንን ህዝብ የሞራል እና አካላዊ ደህንነት ማስጠበቅ የሚል ፕሮፓጋንዳን በሰፊው በማሰራጨት ግዛታቸውን የማስፋፋት አስፈላጊነትን ያካተተ ነበር፡፡

የናዚ ትልቁ መሪ ዕቅድ የሌሎችን ዘር ህዝቦች በማጋዝ፣ በመግደል እና የፖላንድ፣ የዩክሬይን፣ የሩሲያን እና የስላቪክ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በባርነት በመያዝ ለአራያን ጀርመኖች ዝርያ የተለየ ቦታ ማዘጋጀት ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካውያንን ቀደምቶች ሀገር ከሜክሲኮ እና ከሌሎች በዓለም ላይ ካሉ ህዝቦች በመጠበቅ የክልከላ ግንብ መገንባት ነው፡፡

ትራምፕ የሜክሲኮን፣ የላቲን አሜሪካንን፣ የአፍሪካን እና የኢሲያን ዜጎች በማጋዝ፣ በማባረር፣ በማሰር ወይም ደግሞ ከሀገር ውስጥ በማስወጣት እና ማንኛውንም አስፈላጊ የሆነ ነገር ሁሉ በመጠቀም የትራምፕ አራያን ዘር ምርጥ በማለት ለብቻ ለማስቀመጥ ይፈልጋልን?!

ትራምፕ ኩራትን በተላበሰ መልኩ እንዲህ በማለት አወጀ፡ “ታላቅ ግንብ እገነባለሁ – እናም ምንም ቢሆን ከእኔ የተሻለ ግንብ አይገነባም፣ እመኑኝ – እናም በጣም ውድ በሆነ መልኩ እገነባዋለሁ፡፡ ከእኛ በስደቡብ በኩል በሚገኘው ግዛታችን ትልቅ በጣም ትልቅ የሆነ ግንብ እገነባለሁ፣ እናም ሜክሲኮናውያን ለእዚያ ግንብ ክፍያ እንዲከፍሉ አደርጋለሁ፡፡ የተናገርኳቸውን ቃላት ልብ ብላችሁ ያዙ“ ነበር ያለው፡፡

በትራምፓውያን እና በናዚዎች መካከል ባለው ሁለተኛው ልዩነት ምንም ዓይነት ሀሳብ የለኝም፡፡

እ.ኤ.አ በ1920ዎቹ አካባቢ ናዚዝም እያቆጠቆጠ በነበረበት ጊዜ ሂትለርን ያገኙት አሜሪካውያን ጋዜጠኞች እንዲህ ብለው ነበር፣ “ይህ ሰው ህገ ወጥ ባህሪ ያለው ፍጡር ነው፡፡ እራሱን የሚያሞኝ ሰው ነው፡፡ ሂትለር በስልጣን ላይ የወጣ መሆኑን እየተመለከቱም ቢሆን በርካታዎቹ በዚህ እምነታቸው ቀጥለውበት እንደነበር እና ሌሎች ጀርመናውያን የፖለቲካ ሰዎች ሊቆጣጠሩት ይገባል፡፡ ብዙዎቹ የጀርመን ፖለቲከኞች እራሳቸው አምነዋቸዋል“ ነበር ያሉት፡፡

አንድ ዓመት ከመሙላቱ በፊት የፖለቲካ ሰዎች ለዋናው መሪ ዕቅዳቸው በርካታ ድምጽ ሰጭዎችን እንዲያሰባስበለት የሬፐብሊካን ፓርቲ መጥፎ ስነምግባር ያለውን ትራምፕን ተጠቅሞበታል ብለዋል፡፡ ትራምፕ የሁሉም የንቀት ቀልዶች እምብርት ነው፣ እርሱን እንደ እውነተኛ አድርጎ ለመውሰድ ይቻላል፣ እንደዚሁም እንደ ስነምግባር የለሽ አደንቋሪ ሰው አድርጎ መቁጠር፡፡ አዎ አደገኛ ምግባረ ብልሹ ሰው ነው፡፡ ቢላዋ የያዘ ስነምግባር የለሽ ሰው ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዕለቱ መጨረሻ ያው ምግባረ ብልሹ ፍጡር ነው፡፡

የተናቀው እና ቂል ነው የተባለው ሰው በአሁኑ ጊዜ የአሜሪካንን የፕሬዚዳንትነት ቦታ አደገኛ በሆነ መልኩ በመመልከት ላይ ይገኛል፡፡

ጥያቄ ሆኖ መቅረብ ያለበት ስነምግባር የለሹ ማን ነው የሚለው አይደለም፣ ሆኖም ግን ስነምግባር የለሹን የሚንቅ ቂል ማን ነው የሚለው ነው፡፡

ከታሪክ የማይማሩ ያንኑ ተመሳሳይ ስህተት ይደግሙታል ይባላል፡፡ ቤኒቶ ሙሶሎኒ እና አዶልፍ ሂትለር በምርጫዎች ወደ ስልጣን መጡ፡፡ የአሜሪካንን ዴሞክራሲ በሻምፒዮንነት የሚመሩ ከሁሉም ህጸጾቹ ጋር እንዳለ ሆኖ የሚቀጥለውን ፕሬዚዳንት ለመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በመጠቀም ጥብቅ የሆነ ትምህርት መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

ናዚዎች ጀርመንን ታላቅ እና ቀዳሚ ሀገር እናደርጋታለን የሚል ፕሮፓጋንዳ በህዝቦች መካከል በመንዛት እንዲሁም ጀርመንን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከደረሰባት ውርደት ለመካስ የሚል ፕሮፓጋንዳ ሲያሰራጩ ነበር፡፡ በአንደኛው የዓለም ጦርነት በኢኮኖሚ እና በስነልቦና የደቀቀውን እና የተሸነፈውን ህዝብ እንዲቀበላቸው እና የእኩይ ምግባሮቻቸው ተከታይ እንዲሆን ተማጽነዋል፡፡

የትራምፕ የፕሮፓጋንዳ ቡድን እና አሜሪካንን ታላቅ እናደርጋታለን የሚል ህልም እንዲሁም አሜሪካንን የዓለም ኃያል እናደርጋታለን የሚለው በዓለም ላይ እየተበዘበዙ ያሉ፣ ደስተኛ ያልሆኑ እና ቀጣ ያለባቸውን ህዝቦች እንዲሁም የተገለሉትን እና በውስጥ እና በውጭ ኃይሎች እንዲደኸዩ የተደረጉትን እያታለሉ የሸፍጥ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ደጋፊዎቻቸው ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

አሜሪካንን ሀገራቸው አድርገው በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ትራምፓውያን በአገኙት የድል አድራጊነት መንፈስ ትምህርት ሊወሰድ አይችልምን?

በአሜሪካ በስደት የሚኖሩ ዜጎች ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞችን አባርራለሁ በማለት እኔ ዶናልድ ትራምፕ ቃል እገባለሁ … ካለ በኋላ ምን ያስባሉ…?

በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ትራምፕ በዩኤስ አሜሪካ እና በሜክሲኮ መካከል የሚገነባውን የክልከላ የአጥር ግንብ መገንባት ይጀምራል፡፡ በሜክሲኮ እና በሜክሲኮናውያን ላይ ያለውን አቋም ግልጽ አድርጓል፡፡ ትራምፕ አባዛኞቹ ሴት ደፋሪዎች እና ወንጀለኞች ሲሆኑ ጥቂት የሚሆኑት ደግሞ ደህና የሆኑ ጨዋ ሰዎች ናቸው ብሏል፡፡

በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ትራምፕ የሙስሊም ማህበረሰቦች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እና ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት የሚያስችል ትዕዛዝ ያስተላልፋል፡፡

በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ትራምፕ ከቻይና ጋር የነበሩትን የንግድ ስምምነቶች ቀዳዶ በመጣል የንግድ ጦርነቱን ይጀምራል፡፡

በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ትራምፕ የኦባማን ዝቅተኛ ወጭ የጤና ድንጋጌን ሙሉ በሙሉ መጥፎ ነው በማለት ይሽረዋል፡፡

በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ውስጥ ትራምፕ ሕግ እና ስርዓትን በህዝቦች ላይ ይጭናል፡፡

ግን ትራምፕን ጨምሮ ይህ ለመሆኑ እና ላለመሆኑ ማን ያውቃል?

ትራምፕ እንዲህ ብሎ ነበር፣ ፕሬዚዳንት በምሆንበት ጊዜ ለየት ያልኩ ሰው ነው የምሆነው፡፡ ምንጊዜም አይታችሁት የማታውቁ ትክክለኛ የፖለቲካ ሰው መሆን እችላለሁ፡፡

ይኸ ማለት የማይተገብረውን የሚናገር እና የሚናገረውን የማይተገብር ማለት ነውን?

ዶናልድ ትራምፕ ደስተኛ ያልሆኑትን የነጭ ድምጽ ሰጭ አሜሪካውያንን ፍርሀት እና አጉል እምነት በመጠቀም ድምጽ ማሰባሰብ እችላለሁ ብሎ ያምናልን? ሁሉም ነጮች የዘረኝነት ማጨቂያ ጎተራዎች እንደሆኑ እና በእነዚህ ዘረኛ በሚላቸው አማካይነት እ.ኤ.አ ህዳር 8/2016 ከፍተኛ የንቅናቄ ስራ ተሰርቶ ለኋይት ሀውስ የወርቅ ዋንጫ እንደሚያበቁት አድርጎ ያምናል፡፡

የትራምፕ ዋና ስልቱ  የጥቂት ነጭ ድምጽ ሰጭዎችን ንዴት መጠቀም እና በዚህም መሰረት በብዛት ሆነው በጅምላ በመውጣት ባለፉት ሁለት ዙር ዓመታት በዴሞክራቶች ተይዞ የቆየውን የፕሬዚዳንታዊ ቦታ በማሸነፍ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የህዝብ ሽግሽግ ለውጥ በማምጣት ለእርሱ ድምጽ ይሰጡኛል የሚል ስሌት ነው በማራመድ ላይ ያለው፡፡ ይህንንም ዓላማውን እውን ለማድረግ በሙስሊሙ ህዝብ እና ባልተመዘገቡ ስደተኞች ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ በማካሄድ እና ዘረኝነትን በማራመድ ይሳካልኛል ብሎ ያስባል፡፡

የሬፐብሊካን መስራቾች እየተባሉ የሚጠሩት ምግባረ ብልሹ የሆነው እና ብልህነት የጎደለው ዶናልድ ትራምፕ የፓርቲውን ጥቆማ አግኝቶ እያዩ በንቀት እያዩ ወደ ፕሬዚዳንትነት መሰላሉ በመውጣት ላይ መሆኑን እየተመለከቱ ዝም በማለታቸው እንዲህ የሚል ትምህርት መውሰድ ይኖርባቸዋል፡ “ምግባረ ብልሹነት በምግባረ ብልሹነት ላይ ሲጨመር ከፍተኛ አደጋን ያስከትላል፡፡“

ስደተኛ አሜሪካውያን ምግባረ ብልሹውን ትራምፕን እየናቁ ዝም በማለታቸው ወደፊት በእራሳቸው ላይ ምግባረ ብልሹነት ተግባራትን ይሰራባቸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ መልካም ወንዶች እና ሴቶች ሀገራቸውን የሚታደጉበት ጊዜ ነው፡፡

ድምጽ ለመስጠት አሁኑኑ ይመዝገቡ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሀምሌ 11 ቀን 2008 ዓ.ም

Filed in: Amharic