>
8:14 pm - Tuesday January 31, 2023

የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ዝግጅት በሆላንድ - የፈደሬሽኑ እና የሆላንድ ካር ባለቤት የአቶ ታደሰ ተሰማ ፍጥጫ

TADESSE TESEMAክንፉ ኣሰፋ
14ኛው የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ዝግጅት በነገው እለት በደመቀ በሆላንድ ይከፈታል:: ከአውሮፓ፣ ከሰሜን አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ የሚመጡ ከ28 ያላነሱ የእግር ኳስ ቡድኖች እና በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶች ከዛሬ ማክሰኞ ጅምሮ ወደ ሆላንድ በመግባት ላይ ናቸው።
 በኢትዮጵያ የመጀመርያው የስፖርት ጋዜጠኛ እና የአለም-አቀፍ አኦሎምፒክ አማካሪ ሆነው ያሚያገለግሉት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ  በዚህ በዓል የክብር እንግዳ ናቸው።
 የዘንድሮው በዓል ከመጪው እሮብ 26 ጁላይ ጀምሮ እስከ እሁድ 30 ጁላይ ይካሄዳል። ከዚህ ቀደም የዝግጅቱን ሃላፊነት የሚወስዱት የአዘጋጁ ሃገር ክለቦች ነበሩ። ይህንን ዝግጅት ግን ፌዴሬሽኑ ራሱ በማዘጋጀቱ ልዩ ያደርገዋል።
 ዘ ሄግ በሚከናወነው በዚህ የኢትዮጵያውያን መሰባሰብያ በዓል ላይ ልዩ-ልዩ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ። ከእግር ኳስ ጨዋታው ባሻገር ዘመናዊና የባህል ፋሽን ትዕይንት፣ የሙዚቃ እና የተለያዩ ስፖርታዊ መርሃግብሮች ይካሄዳሉ።
 ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው ሆላንድ ካር ባለቤት አቶ ታደሰ ተሰማ የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ጋር ክፉኛ ተፋጥጠዋል። አቶ ታደሰ ተሰማ ይህንን የአውሮፓ ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን ለማፍረስ መነሳታቸውን በአንደበታቸው ተናግረዋል። እቅዳቸውን  ለማሳካት አስቴር አወቀን ጨምሮ በርካታ ዘፋኞችን በግላቸው በማስመጣት የፌዴሬሽኑን ገቢ ለማዳከም ቆርጠው መነሳታቸውን የስፖርቱ አፍቃሪዎች ይናገራሉ።
 አቶ ታደሰ ተሰማ በሆላንድ ካር ስም በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከ100 በላይ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች ላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣  መክሰራቸውን በካንጋሩ ፍርድ ቤት አሳውጀው ወደ ነበሩበት ወደ ሆላንድ ተመልሰዋል። ገንዘባቸው የተበላባቸው ሰዎች በመሰባሰብ  በኢንተርፖል በኩል ግለሰቡ ተይዘው  እንዲቀርቡ ቢጠይቁም ይህ ሊሆን አልቻለም።  ከስርያለሁ ያሉት እኚህ ግለሰብ ሆላንድ ላይ ዘመናዊ ምግብ ቤት በመክፈት ንግዳቸውን እያጧጧፉት ይገኛሉ። አቶ ታደሰ በዚህ አላበቁም።  በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ ዋስትናነት ኢትዮጵያ  እንዲገቡና መግለጫ እንዲሰጡም ተደርገዋል።    በኢንተርፖል እንዲያዙ ጥያቄ የቀረበባቸው እኝህ ሰው፤ በብራስልስ የህወሃት ኤምባሲ ጋር እጅና ጓንት ስለሆኑ ከህግ በላይ ናቸው።  የልብ ልብ ተሰምቷቸውም  በህዝብ ንብረት ይቀልዳሉ። እነ ኤርምያስ አመልጋ  የህዝብ ገንዘብ በመብላት ወንጀል ሲታሰሩ አቶ ታደሰ ግን እንደልባቸው እንዲገቡ እና እንዲወጡ ተደርገዋል። ምክንያቱም በየአመቱ የሟች ጠ/ም መለስን የሙት አመት እያከበሩ ግብር ያበላሉ።
 አቶ ታደሰ ተሰማ በዘንድሮው የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል በዓል ላይ ከአስር በላይ አርቲስቶችን በመጋበዝ የፌደሬሽኑን ገቢ ለማግደል አቅደዋል። ከዚህ አጥፊ ተግባራቸው በፌዴዴሽኑ ቢጠየቁም አሻፈረኝ፡ብለዋል። እንዲያውም ይህንን ፌደሬሽን እንደሚያፈርሱት ነው የተናገሩት።  እኚህ ሰው ምንም እንኳን በዕጃቸው የህዝቡን ገንዘብ የያዙ ቢሆንም ይህንን በድፍረት ለመናገር የቻሉት ከጀርባቸው የተማመኑበት ሃይል ስላለ ነው።
የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን በአውሮፓ ላለፉት 14 አመታት ኢትዮጵያውያንን በማሰባበብ ትልቅ ስራ እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው። አቶ ታደሰ ይህንን ተቋም እንደ ሰሜን አሜሪካው ለሁላት ለመክፈል ከተላኩ ይመስላል።  በአቶ ታደሰ በኩል እየተጠራችሁ ለዚህ እኩይ ተግባር የምትመጡ አርቲስቶች በሙሉ የሰሜን አሜሪካው አይነት ችግር እንዳይድደርስባችሁ ተጠንቀቁ።  በተለይ አንጋፋዋ  አስቴር አወቀ፣ ወደ ሆላንድ ስትገቢ የሚያስመጣሽ ሰው የስራ ግብር መከፈሉን አረጋግጪ።
Filed in: Amharic