>
11:13 pm - Wednesday August 4, 2021

የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ፤ የዛሬው ዳንኤል አበበ ማነው? [የዲያስጶራ ይሁዳዎች ክፍል ፪ (ግርማ እንድሪያስ)]

ባለፈው ብዕሬ ደም ተፍታ ነበር። ደም ያልኩት ብዙ የደሙ፣ የተሰቃዩ ሰዎችን እያወኩኝና የዕውኑን ዓለም ይሁዳዎች መተረክ ስትችል ላይላዩን ብዕሬ ተሽከርክራ ስለነበረ ነው። አጠገባችን ያሉ ይሁዳዎችንመግለጽ ሲቻል፣ የቅዱስ መጽሃፉ ይሁዳ ላይ አተኮረች። አንጀታቸው ቅቤ የጠጣም፣ ቆሽታቸው ያረረም አስተያየታቸውን እንዲልኩ ኢሜሌንአስቀምጨ ነበረ። በርካታ መልዕክቶች ደርሰውኛል። ከረኩት፣ ገፈቱን ከቀመሱት፣ የትየሌለ ጅቦችን ካስተዋሉት አንባቢዎቼ። አመሰግናለሁ።
«ሟች የገዳይን ሃሳብ ቢያውቅ ኖሮ አብሮት አይሄድም ነበር።» ብዙ ሟቾች ከገዳዮቻቸው ጋር ያዘግማሉ። ደስ የሚለው ግን ገዳዮችም አንድ ዕለት ሟቾች መሆናቸው ነው። ለጊዜው ባለንባት ምድር ይሄ ሃቅ ነው።

እንደመግቢያ

ቃኤል ወንድሙን አቤልን ገደለው። ምን አ ድርጎት?…. ይሄን ስተነትን አልገኝም። ይልቅስ አቤል ዜጎቹ በሃገሩ ልጆች የደረሰበትን የገለጸበት ብዕር መግቢያዬ ባደርገው እመርጣለሁ።
«ቀልድ ያለፈበት ጨዋታ ሆኗል። አሁን ዘውጉ ተቀይሯል። ፍጥጥግጥጥ ያለ ዕውናዊ ድርሰትን መመልከት ጀምረናል። ዓይን አያየው የለም። አሁን ደግሞ ገራፊዬን አሳየኝ። በኤሌትሪክ ገመድ ጀርባዬ እስኪቀደድ የገረፈኝን፣ በመጥረጊያ እንጨት ውስጥ እግሬን ያነደደኝን፣ እጄ በካቴና ታስሮ ወለል ላይ ያንከባለለኝን፣ ጨለማ ቤት ውስጥ አስገብቶ ከየት  እንደመጣ በማላውቀው ጅራፍ አሳሬን ያሳየኝን፣ እናቴን ከመቃብር ጠርቼ አንቺ  እናቴ ለምን ጥሩ ሁን ብለሽ አሳደግሽኝ? ብዬ  እንድወቅሳት ያደረገኝን፣ወንድየወንዶች ቁና በካቴና የታሰረን ሰው በእኩለሌሊት ጠርቶ አፉ ውስጥ ጨርቅ ወትፎ የሚደበድብ በዓይኔ በብረቱ አየሁት።» ፌብሪዋሪ 23 ቀን 2016 ። አቤል ዋቤላ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የደረሰበትን መግቢያው ላይ ያሰፈረውን መግቢያዬ አደረኩት።

የሚፈጥረው ስሜት

አቤል የደረሰበትን በብዕሩ ግለት ብቻ የገለጸው አይመስለኝም። ብዕሩ ከገለጸው በላይ ስቃዮችን አ ቤል አሳልፏል። ሌሎችም ወገኖች ዕለት በዕለት የሚደርስባቸው ነው። የአቤልን ብዕር ቡና እየጠጡ ካነበቡ፣ ቡናው  እሬት እሬት ማለቱ አይቀርም።  እየበሉም ከሆነ ያለመጡትን መዋጥ አ ይቻልም።  እህሉ አፍ ላይ ከመንቀዋለል ውጭ። ክፉዎች ግን ስቃይን አ ሳምረው መሳቅ ይችሉበታል። የ ክፉዎች መዝናኛ የሌሎች ስቃይነውና።

ከብዙ ጊዜያት በኋላ ብዕሬ አንድ አንድ  እያለች የዲያስጶራን ይሁዳዎች ለማጋለጥ ወስናለች። ከሰገባዋ ወጥታለች። ዲያስጶራ የጥሩዎችም፣የክፉዎችም መሸሸጊያ (መደበቂያ) በመሆኗ ክፉዎች ቁርበት አንጥፉልኝ…” ሲሉ ታነጣጥራለች። ትተኩሳለች። ቁርበት ሳይሹ አርፈው የተደበቁት ክፉዎችላይ ብዕሬ ኢላማምአላማም የላትም። ምክንያቱም የተደበቁበት ሃገራቶች  እና መንግስታቶች ሃላፊነትና ውሳኔ ነው። ሲያጨበጭቡላቸውም ሆነ፣ ሲቀበሉዋቸው ከማየት ውጭ ምንም ለማለት ህሊናዬም ብዕሬም አትፈቅድም። ነገር ግን ሁለት ዋሻሲይዙ አልፈቅድም። የትላንቱ ሽፍትነታቸው አገርሽቶ ቁርበት አንጥፉልኝየሚሉ ጅቦች ሲሆኑ አልችልም። ሁለት ዋሻ ያልኩት:- አንዱ ያረፉበት ሃገር ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ተወልደው ባደጉበት ሃገር በመናገራቸው፣ በመኖራቸው፣ በማሰባቸው ሰለባ የሆኑ ዜጎች ባቋቋሙት የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ማህበራቶች ውስጥ መወሸቃቸውን ብቻ ሳይሆን ከፊትከፊት መታየታቸው ነው። አንደኛው ዋሻ አያገባኝም የምለው  እጃቸው በደም የጨቀየን ወንጀለኛ ማጋለጥም፣ መፍረድም ያረፉበት ሃገር ጉዳይ ነው።  ይሄንን ስል በጥቁቱም ቢሆን ያረፉባቸው ሃገሮች የሚሰጡትን ውሳኔ አይቻለሁና ነው። የቀይ ሽብሩ ተዋናይ የነበረው  እሸቱ ዓለሙ በኔዘርላንድ  እስር ቤት ውስጥ የሚገኘው በኢትዮጵያውያኖች ወይም በጋዜጠኞች ጥቆማና ክስ አ ይደለም።  እንደዚያ ቢሆን ማሰረጃ ዶት ኮምና”- http://www.masreja.com/ ኦባንግ ሜቶ ብዙ ወንጀለኞችን በፋይልና በመረጃ አ ቅርበው ሲፈረድም ሆነ ሲፈየድ ያየነው የለምና። ለብዕሬ አንድ ማሳያ መስጠቴ አንባቢን ግንዛቤ ለማስጨበጥም ያን ያህልም ምቀኛ ብዕር ከሰገባ ያለማውጣቴን ለማሳየት ነው።

¤ ¤ ¤

ትላንት በስርዓቱ ውስጥ ሰላማዊውን ሰው ቁጭ ብድግ ሲቀጡት፣ አ ቅሉን ሲያሳጡት የነበሩ ሰዎች ይቅርታ!” የምትለዋን ቃል ቢደፍሩት  እንኳንስ ብዕርን የሚያህል ትልቅ ነገር ከሰገባው መጎተት ቀርቶ ባጨበጨብንላቸው ነበር። ግን ያንን መመልከት የሰማይ ያህል ይርቃል። በዚህ ጉዳይ ወይም በይቅርታ ጠያቂነት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳ በኔ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የምሰጣቸው ናቸው። ለህዝቡ የጠየቁት ይቅርታ ካለሁበት ዲያስጶራ አ ማለውኝ ለውጭ ሃገር መጽሔት ለንባብ አ ብቅቼአ ቸዋለሁ። የተመሰጥኩባቸውና የምረካባቸው ውድ ሰው!.

እነሆ አንድ ይሁዳ ላሳያችሁ ነው።
የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ አበባው፤ የዛሬው ዳንኤል አበበ ማነው?

%e1%8a%a8%e1%8a%ab%e1%88%b3%e1%88%81%e1%8a%95-%e1%8a%a0%e1%8b%b5%e1%88%9b%e1%88%b1-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%8b%b3%e1%8a%95-%e1%8a%a4%e1%88%8d-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a0%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8b%a8ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅበሚል ሽፋን ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች በሾኬተብለው ከተፈለፈሉት ድዊዎች ውስጥ አንዱ ነው። አንቱ የተባሉ ሰዎችን ጉዳይ በአቃቢ ህግነት ይመለከትና ይተነትን ነበር። ጉዳዩ በዚሁ ሰው ተይዞላቸው ለሞት ከተዳረጉት የፖለቲካ ሰዎችና ጋዜጠኞች ውስጥ በስም መጥቀሱ አስፈላጊ ይመስለኛል። እስከ ሞታቸው ፍጻሜ ጉዳያቸውን ከያዘው ሰለባዎች ውስጥ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ ከፖለቲከኞች ሲጠቀሱ ተስፋዬ ታደሰ ከጋዜጠኞቹ አ ንዱ ነው። ተስፋዬ ታደሰ የመስታወት መጽሔት አዘጋጅና አሳታሚ ነበር።  ዶክተር ታዬ ወልደሰማያት ተፈራ አስማረ፣ ዳንኤል ክፍሌ፣ መጽሃፈ ሲራክ፣ መላኩ ታደሰ፣ መላኩ ጸጋዬ፣ እስክንድር ነጋ፣ ሲሳይ አጌና እኔ ግርማ እንድሪያስ  ወርቁ አለማየሁ ወዘተ….. ስንቱን በስም ዘርዝሬ እችላለሁ? በዚሁ አቃቢ ህግበሚል ሽፋን በአራዳ ሁለተኛ ችሎት ጉዳዩ የታየላቸውና የሚንከራተቱ ነበሩ።

ወሽመጥ….

ዕውቁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ከኢሳት ሆኖ ወደ አ ዲስ አ በባ ስልክ ደወለ። ስልኩን ያነሱት ጓል ጎላነበሩ። ወይም ወይዘሮ አዜብ መስፍን።
ወይዘሮ አዜብ መስፍን?” አለ ሲሳይ አጌና።
ስልኩን ያነሳችው ወይዘሮ አዜብ አዜብ አይደለሁምስትል ሸመጠጠች። አዜብ አዜብነቷን እያወቅን ተገረምን። ጠያቂው ሲሳይም ከዚያ በላይ መሄድ አ ልቻለም። ድምጽዎት የርስዎ ነው!” ቢላትም እኔ አይደለሁም!!” ስትል ደረቀች። ምን ማድረግ ይቻላል?

ዛሬየትላንቱ አ ቃቢ ህግ የጋዜጠኞችንና የፖለቲከኞችን ጉዳይ ክሱን በማቀናበርና በማቅረብ ሲያንገላታ የነበረውን አንተ ካሳሁን!…ማለት አ ይቻልም። ዳቦ ሳያስቆርስ ባወጣውና በቀየረው ደንኤል አበበ በተሰኘው ስሙ ሃጢያቱን ሰርዯል። ከምናውቃቸው ወንጀለኞች ለየት የሚያደርገውና ድርቅናውንና ፈጣጣነቱን የምናይበት በድምጽም በምስልም ከፊትከፊት መቅደሙንና መድፈሩን ስንመለከት ነው። ዛሬ ወንጀለኛውና ከርሱን በንጹሃኖች እንግልት ሲሞላ የነበረው ሰው የተቃዋሚዎችን መድረክ ከፊት ሆኖ ያሾረዋል። ጃስ!…” ይለዋል። እንደትላንቱ አስራ አራትም ሃያ አንድ ቀን ባይጠይቅብንም በተነጠፉለት ”እርጥብ ቁርበቶች” ያስገላምጠናል። ይገላምጠናልም። ጅብ ባልታወቀበት ሃገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ….” አለ የሚሉት ያበው ተረት ህይወት ዘርቶ መለ መላውን ለመመልከት ተገደናል። ለዕውነት መስዋዕትነት የከፈሉትን ዳኛ ወልደሚካኤልን፣ ብርቱካን ሚዴቅሳን በየመድረኮቹ ባናያቸው የማይገርመን ለዚህም ይሆናል።

«በሰነፎች መካከል ከሚገኝ የገዥዎች ጩኽት ይልቅ የጠቢባን ቃል በጸጥታ ትሰማለች።»

በጸጥታቸው ውስጥ የምንሰማቸውን ከላይ ለመነካካት ሞክሬያለሁ። ደፋሮች፣ታታሪዎች፣ለሃገራቸው ቀናኢ አመለካከት ከግንዛቤ ጋር ያላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያኖች አውቃለሁኝ። አንቱ የተባሉ የሃሳብ ጎምቱዎች። በዝምታቸው ውስጥ ጩኽታቸው የሚሰሙ ደጀኖች። በአንጻሩም ሆዳሞች፣ ፍጥጥ ያሉና ይሉኝታን የማያውቁ፣ ትላንትና ገድለው፣ አስረው አንገላተው ያልረኩትን እነ ካሳሁን አድማሱ የዛሬው ዳንኤል አበበ ዓይነቶችን ማየት የዲያስጶራ የዕለት ተዕለት ውሎና አዳር መሆኑ አይገርምም። የምተርክላችሁ ይሁዳ ባሁኑ ወቅት በኖርዌይ የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያሊቀመንበርና በነገው ዕለትም በሚካሄደው የኢትዮጵያውያኖች ማህበር አስመራጭ ኮሚቴ ሆኖ የሚሰየመውን ነው። የሚያውቁትም፣ የማያውቁትም ወገኖችብብታቸው እስኪታይ ድረስ እጃቸውን ያወጡለታል። ጓንቶቻቸውን አውልቀው ያጨበጭቡለታል። ሰውየው ይሄ ነበረ የሚለው ጥቆማና የወገን መረጃን የሚያናንቁ ፈቅደው የተነጠፉ ‘ቁርበቶች’ ሊሆኑ ይችላሉ። ውሃ የሚያነሳ መረጃን አናንቀውታልና። ምክንያቱም በሰነፎች መካከል የተገኘ ገዥ ሆኗልና። ጲላጦስ ክርስቶስ ላይ ከመፍረዱ በፊት ምን ላድርገው ይሄን ሰው? ሲላቸውየጯሂዎች ጩኽት እንደበረከተው ሆኗልና። ለዚያም ነው በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን የሰቀለላቸው።

በሃሳብ ወደኋላ የማልቀርበት ስብሰባ

እንደ ስሙ ታማኝ የሆነው ታማኝ ወደኖርዌይ የመጣው ለህዝብ ዓይንና ጆሮ የሆነውን ኢሳትን ለመታደግና ከነዋሪው ጋር ለመወያየት ነበረ። ቀደም ባሉት የተለያዩ የህዝብ ውይይቶች ላይ እንደዜጋም እንደጋዜጠኛም መሳተፌ እኔ‘ ‘ህሊናዬና ሙያዬ በልሲለኝ ነው። ሙድ ይበልጣል ከፉድእንዲሉ ሙዴን እመለከታለሁ። ሙድሲተነተን ያሰቡትን፣የፈቀዱትን መሆን ነው። የግል ነጻነት ነው። የግል ግፊት ነው። ያ እኔ ነኝ። ታማኝን ማየት፣መስማት፣ማድመጥ ማጀብ ከሙድምበላይ ነው ለኔ። የአቋም ሰው ነውና፣አክብሮትም ፍቅርም ቢኖረኝ ለሃገር የሆነውና የሚሆነውን ስለማውቅ ነው። በኢሳት ዝግጅቶች ላይ መገኘት የሙያ አጋሮቼን በዓይነ ህሊናም በአካልም የማግኘት ያህል ስሜት በውስጤ ይፈጠራል። ባንድ ቢሮ ውስጥ አምሽተን፣ ያነጋንባቸው ክፉምደግም ውጣ ውረድ ያሳለፍናቸው የነጻ ፕሬስ ሰዎች በውስጡ የታጨቁበት አካልና ኢንስቲቲዩሽንነው። እንዲህ ያሉ ስብስቦች ላይ በስፍራው ብገኝ እንጂ ብቀር አረካም።ስለዚህም በቦታው ተገኘሁ።

አንድ አጭር ወደመነጋገሪያው ስፍራ ቀረበ። የዲሞክራሲያዊ ለውጥ…..”ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ ተሰኝቶ ነበር የቀረበው። ዓይኔን ብረቱን ተጠራጠርኩ። ይህን ክቡር ስፍራ በሰጡት ሰዎች አዘንኩ። ሁለት ቃላቶች ከቆመበት ስታንድላይ ሲናገር በዓይነ ህሊናዬ ከኖርዌይ አዲስ አበባ ቀጨኔ አራዳ ፍርድ ቤት መጠኩኝ። ”…የተከበረው ፍርድ ቤት በዚህ በታማኝና በተቀሩት ተከሳሾቼ ላይ መረጃዎቼ ሊጠፉ ሲለሚችሉ የሃያ አ ንድ ቀን ቀነ – ቀጠሮ ይሰጠኝና በእስር ቤት ይቆዩልኝየሚል ንባብ የሚያነብም መሰለኝ። ከተቀመጥኩበት እንዴት እንደተነሳሁና እንደወጣሁኝ አላውቅም። ስብሰባውን ጥዬ ወጣሁኝ። ወጥቼ ሲጋራ አ ቀጣጥዬም ይሁን እኔ ተቀጣጥዬ አላስታውስም። ቆሽቴ ግን ለራሴ ይሸተኝ ነበር። ወይ ነዶአልኩኝ። እንዲያ ሆኜ ነበር ወደቤቴ ያመራሁት። የተፈጥሮ አንጎልህ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የሆነውን ነገር በተጨማሪ አንግሎልህ መዝግበው…” እንዲሉ የተሰማኝን ስሜት ማስታወሻዬ ላይ አሰፈርኩት።

ምን ማድረግ ነበረብኝ?

ለሚመለከታቸው ሁሉ መነገር ነበረበትና የትላንቱ ካሳሁን አድማሱ አበባው የዛሬው ዳንኤል አበበን ማንነት እንደዜጋም እንደጋዜጠኛም ለሚመለከታቸውና በአመራር ላይ ለሚገኙት ለመግለጽ ሞከርኩኝ። ከወያኔ መረጃ የሚያመጣልን ታላቅ ሰዋችን ነው ተባልኩኝ። ቁልፋችን ነው አሉኝ። ጅቡ ብዙ ቁርበቶች እንዳገኘም ተረዳሁኝ። ከበቂ በላይ መልስ አገኘሁኝ። በሃሳቤ ይሁዳቢመላለስብኝና ብከትበው ይሁዳ የዋህ ሆኖ አገኘሁት። የሰበሰበውን ዲናር መበተኑንና መሰቀሉን አወቅሁኝ።የይሁዳን ምግባር ሳሰላስል ነፍስ ይማር!” ለማለትም ዳዳኝ።
ጥያቄ አንድ። ወያኔዎች የነሱ የሆነ አቃቢ ህግ ለዚያውም መሪ ተዋናያናቸውን ስሙን ለውጦ በየመድረኩ ሲንጎራደድ ለምን ዝም አ ሉት?
የኔ መልስ። አብሮአቸው ስለሚሰራ።ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም። ገና ድሮ ”ትግራይ ኦንላይን” ወይም ”አይጋ ፎረም” ላይ እንመለከተው ነበርና። 

1.«ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ» የጎጃም ህዝብ

2. «ዕውነትን ለመናገር አትፍራ። ሃሰትን ለመናገር አትድፈር።» መጽሃፍ ቅዱስ

1.1 በቀድሞው የቅኝ ግዛት ትግል በላይ ዘለቀ ጀግና ነበረ። ትልቅና ከመጀመሪያው ረድፍ ላይ የተሰለፈ ጀግና። የቅኝ ግዛቱ ወረራ በድል በተጠናቀቀ ማግስት ጀግና የተባለው በላይ ዘለቀ በተከበረበት በተወደሰበትና ባስከበራት ሃገር መሪ በስቅላት እንዲሞት (እንዲቀጣ) ተደረገ። ጉዳዩን መንገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆናልና ተውኩት። የጎጃም ህዝብም ለትውልድ የሚተርፍ ተረት በጩኽት ሳይሆን በውስጡ አጉረመረመ። በዝምታው ውስጥ የተሰማው ጩኽት ተረት ሆኖ ለትውልድም ተርፎ ይሄው እኛም እያልነው ነው «ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ሞኝ ነሽ ተላላ ….. የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ»

2.1 በራሳቸውና በግላቸው ህሊናና ዕውነት የሚተማመኑና የሚተገብሩ ሰዎች ሁልጊዜም የሚፈሩት ፍርሃትን ብቻ ነው። ዕውነትን ለመናገር ከርሳቸውን አያስቡም። እዚህ ዓለም ላይ እራቁታቸውን እንደመጡና እራቁታቸውን እንደሚሄዱ ያስተውላሉና ስለዕውነት ይኖራሉ። የሚተኙትም እንቅልፍ ውብ ነው። በዚህ ውስጥ እስክንድር ነጋ የኔ ምሳሌ ነው። እስክንድር ነጋን የምወደው በመታሰሩ አይደለም። ለዕውነት የሚከፍለው መስዋዕትነትና እየከፈለ ያለው ዕውነት ጥግ የለውም። እስክንድር ምሳሌ ነው። የዕውነት አለቃ። የድፍረት ንጉስ። «ዕውነትን ለመናገር አ ትፍራ። ሃሰትን ለመናገር አ ትድፈር።» ሲተነተን እስክንድር ነው 

አበቃሁ ኢሜሌ ይሄውላችሁ። girma077@gmail.com

Filed in: Amharic