>
9:08 pm - Tuesday January 31, 2023

ወያኔዎች በአርበኞች የደረሰባቸውን ሽንፈት እንዲህ ገመገሙ.... (ነፃነት ሚዲያ)

በባህርዳር የተደረገው የጥምር አመራሮች ስብሰባ ያለ ስምምነት ተበተነ። በአማራ ክልል እና በቢንሻንጉል ክልል የሚንቀሳቀሱትን የአርበኞች ግንቦ ፯ የነፃነት ታጋዮችን ” ለመደምሰስ” ወጥቶ በነበረው እቅድ ዙሪያ የእቅዱን አፈፃፀም ለመገምገምና ለቀጣይ መደረግ ስላለበት ለመወያየት በተጠራው ስብሰባ የተገኙት፦

1ኛ =>ከመከላከያ

2ኛ =>ከብሔራዊ ደህንነትና መረጃ

3ኛ =>ከፊዲራል እነሰ ከክልል ፖሊስ

4ኛ => የክልልና የፊዲራል ከፍተኛ አመራሮች

5ኛ =>የዞን እና የወረዳ አመራሮች

6ኛ =>በክልሉ የሚገኙ የከተማ አመራሮች

7ኛ =>የፀረ_ሽብር እና የልዩ ኃይሎች አመራሮች ተብዬ አካላት በስብሰባው የተገኙ ሲሆን ከላይ እንደተገለፀው አጀንዳቸው፦

1ኛ =>በየቦታው ያሉትን የጎበዝ አለቃዎችን እስከ ተከታዮቻቸው ለመደምሰስ ያወጣነው እቅድ አፈፃፀም ለመገምገም

2ኛ =>ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር ተያይዞ የተቋቋመው ጥምር የፀጥታ ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴ መገምገም

3ኛ =>ከታህድሶው ጋር ተያይዞ የተመለሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች … ወዘተ ለማየት

ከጅምሩ ለግምገማ በተቀመጠው አጀንዳ ላይ አለመስማማት ተፈጠረ፡፡ ምክነያቱም “እነዚህ የጎበዝ አለቃዎች የምንላቸው በተመለከተ፤ ከአሁን ቀደም ሽፍታዎች ስንላቸው ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የጎበዝ አለቃዎች ትላላቹሁ፡፡ ለምን መደባበቁ እና መዋሸቱ አስፈለገ፡፡ ህዝቡ እኮ እነዚህን ሰዎች ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ እነሱ እኮ በሁሉም መልኩ በሰው ኃይል፣  በመሳሪያም፣ በአደረጃጀትም … የተሟሉ ናቸው፡፡”

ተሰተያየቶች ሲቀጥሉም “….እንደሚባሉት የጎበዝ አለቃዎች ሳይሆኑ የተደራጅ ድርጅቶች ናቸው፡፡ እነሱም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሰዎችናቸው፡፡ በመሆኑም ከመደባበቅ በግልፅ እንጥራው፡፡  የምንታገለው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ነው ተብሎ ሊቀመጥ ይገባል፡፡  ይህን ድርጅት ስሙን መጥራት አለመፈለግ እና ስሙን ማንኳሰስ ድርጅቱን ሳይሆን ያኳሰስነው የኛን አቅም ነው ያሳነስነው፡፡”

በተጨማሪም ተናጋሪው “ይህ ሁሉ የሞት፣ የመቁሰል፣ የመማረክ፣ የመክዳት… ወዘተ ችግሮች በእርግጥ በኛ ላይ ያደረሱቡን የጎበዝ አለቆች ናቸው? ለማለት ሞራል አይኖረነም፡፡” በማለት አንደኛው ተሰብሳቢ ሲናገር አዳራሹ በጭብጨባ ተናወጠ፡፡  መድረክ ሲመሩ የነበሩ የህወሓት ወታደራዊና ሲቪል አመራሮች ተደናገጡ፡፡

ከዚያም ተሰብሳቢው በአብላጫና በጭብጨባ በገለፀው መሰረት የጎበዝ አለቃ የሚለው ወደ  አርበኞች ግንቦ ፯ ይቀየር?  አይቀየር? በሚለው ስምምነት መድረስ ሳይቻል ከ40 ደቂቃ በላይ ፈጀ፡፡ መድረክ መሪው “የጎበዝ አለቃ አልናቸው ግንቦት ሰባት አልናቸው ልዩነት የለውም፡፡ እነዚህ ፀረ-ሰላም፣ ፀረ-ህዝቦችና ፀረ-ልማቶች ናቸው፡፡ በስም አጠራር ዙሪያ መጨቃጨቅ የለብነም፡፡ በመጀመሪያው እንቀጥል፡፡” በማለት ሲናገር አሁንም ተቋውሞ ገጠመው፡፡

ከዚያም አንድ ተሰብሳቢ “እኛ አሁን ከዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ መጨቃጨቅ ያለብን አይመስለኝም፡፡  ህዝቡ እኮ እኛ የጎበዝ አለቃዎች እያልን የምንጠራቸው አርበኞች ግንቦ 7 አባላት መሆናቸውን ያውቃል፡፡ ደግሞም ከታህድሶ በኃላ በግልፅነት እንሰራለን እያልን አሁን ይህን መደባበቅ ምን አመጣው? የምንዋሸው እና የምናታለው ራሳችንን ነው፡፡ ደግሞስ አሁን የሚያጨቃጭቁን ሰዎች በክልል አንድ በኩል ሲያዙ ቴሊቪዥኑ፣ ሪዲዩው፣ ጋዜጣው … አርበኞች ግንቦት ሰባት ተያዙ፣ ተገደሉ፣ ቆሰሊሉ … ይላል፡፡

…. በእኛ አማራ እና ሌሎች ክልሎች ሲሆን አንድዬ ሽፍታ፤ ሊላ ጊዜ የጎበዝ አለቃ እያልን መጥራቱ ለምን አስፈለገ? ሊላው ከእኛ ክልል አስራቹሁ የወሰዳችሗቸው ሰዎችንስ ስትመረምሩ እና ስትከሱ የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት በማለት አይደለምን ወይ? ሰዎችስ በምርመራ ነን በሉ እየተባለ አይደለም ወይ የሚሰቃዩት? አሁን ለምንድነው በመድረክ ለመናገር ጭንቅ የሆነባቹሁ?” በማለት ሲናገር አሁንም አዳራሹ በጭብጨባ ተናወጠ፡፡

ከዚያም ርዕሱ ከጎበዝ አለቃ ወደ አርበኞች ግንቦት ሰባት ተቀይሮ ተስተካከለ፣ የምሳ ስዓት በመድረሱ ስብሰባው ለከሳዓት ለመቀጠል ቀጠሮ ተይዞ ተበተነ ።

ስብሰባው ከስዓት ቀጠለ አጀንዳ ያስቀየሩትም በሰላም ተመልሰው በስብሰባው ተገኙ፡፡ ከመድረክ የሚከተለው ቀረበ፡፡ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የዚህ ዓመት ፀጥታን በተመለከተ ግምገማ የተደረገ ሲሆን በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ለመቆጣጠር በተሰራው ስራ ውጤት የተገኘ ሲሆን፤ ነገር ግን በአማራ እና በከፌል ቢንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚንቀሳቀሱ፤ ይስተካከል በተባለው መሰረት የአርበኞች ግንቦ ሰባት ኃይሎች ላይ በተደጋጋሚ ለመደምሰስ የተደረገው ጥረት ውጤት አላመጣም፡፡

በኦሮሚያ የነበረውን የግምገማ ውጤት ከዚህ ላይ ማቅረብ አስፈላጊ ባለመሆኑ አልፈዋለሁ ካለ በኃላ በተለይ በጎንደር፣ ዳባት አጅሪጃኖራ፣ እንቃሽ፣ችንፋዝ በገና፣ ስላሪ፣በለሳ አርባያ፣ጉኃላ ሀሙሲት ፣አለፋጣቁሳ ፣ ቋራ፣ መተማ፣ ጭልጋ፣ አዳኝ አገር ጫቆ፣በደንቢያ ቆላድባ፣ ጯሂት፣ ቻይና ፕሮጀክት፣ በተለይ የመከላከያ ካምፖች በሆኑ ጭልጋ ነጋዴ ባህር፣ ዳባት ጃኖራ፣ ወገራ አምባጊዩርጊስ የተፈፀሙ ጥቃቶች ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡

በተጠቀሱት ከተሞች የተመቱ የፖሊስ ጣቢያዎች፣ እስረኞችን ማስፈታት፣ የመንግስት ተቋማትን የማፍረስ ስራዎች ተገምግመዋል፡፡ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን በሊቦ ከምከም፣ በእብናት፣ በጋይንት የተፈፀሙ ጥቃቶች በተለይ በቅርቡ በእብናት ከተማ ሰኔ12 ቀን 2009 ዓ.ም. ወሳኝ የሚባሉ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ለአብነት ኩማንደር አወቀን ያጣንበት ጥቃት ትልቅ ውድቀት ሁኖ ታይቷል።

በመሆኑም በአንዳንድ ከተሞች የተፈፀሙትን የቦንብ ጥቃቶችን ማስቆም ቢቻልም አሁንም አልፎ አልፎ የተጠኑ በሚመስል መልኩ እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ በቅርብ በአዲስ አበባ በፌዲራል ፖሊስ መጋዝን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት መመልከት ይቻላል። አጠቃላይ ግምገማው ብዙ ጉዳዬችን አይቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ግን ለምድን ነው? በተቀመጠው እቅድ መሰረት እነዚህን ፀረ-ሰላምና ፀረ-ህዝቦችን መደምሰስ ያልተቻለው? በዚህ ዙሪያ ላይ በሰፌው መወያየት አለብን በማለት መድረኩን ከፈተው፡፡

ከዚያ አንድ የፀረ ሽምቅ አመራር አካሄድ በማለት እጅን አወጣ እንዲናገር ተፈቀደለት “መድረኩ በራሱ ችግሮች አሉበት በዚህ ዓመት  የሞተው አመራር ብቻ ነው ወይ? ስንቱ ወታደር ተገቢ ባልሆነ አመራር በእንቃሽ፣ በአጅሪ ጃኖራ፣ በችንፈዝ፣ በእብናት፣ በሊቦከምከም፣ ቋራ፣ በአላጥሽ የሞተው ምነው ተረሳስ? ሌላው የሞተው የመከላከያ አመራሮች ብቻ ናቸው ወይ? የሞቱት ለምን በጃኖራ፣ በሊቦ፣ በጎንደር …  የተገደሉ የፀረ ሽምቅ አመራሮችና አባሎች አልተነሱም? ሌላው በካሳ አከፋፈል ላይ የፊደራል ፖሊስና ከመከላከያ የአጋዚና የህወሓት አመራሮች ሲሞቱ ከቀብር አንስቶ አስከ ቤተሶቦቻቸው ድረስ የሚደረገው እንክብካቢ እና በገንዘብ በኩልም ለነሱ ቤተሰቦች ብር 80,000 ( ሰማኒያ ሺ) ሲሰጥ ለ፤ ለሌላው በተለይ ለፀረ ሽምቅ ፣ ለሚኒሻ አባላት ብር 30,000 ( ሰላሳ ሺ) ብቻ የሂይወት ካሳ ይሰጣል፡፡ ይህ ለምን ይሆናል?” በማለት ሲናገር ድንገት መድረክ መሪው ንግግሩን ሊያስቆመው ሲል ተሰብሳቢዎች ይጨርስ አታቋርጠው በማለት ጩኽት አሰሙ፡፡

ከዚያም ሰውየው ቀጠለ “ጨርሻለሁ አንድ ነጥብ ይቀረኛል፡፡ ወታደሮች ሲሞቱ ከአመራሮች ውጭ ያለው አስክሬን አይነሳም ደግሞም አብዛኛዎቹ አይቀበሩም፡፡ሲሞቱም ለቤተሰቦቻቸው መርዶ አይነገርም፡፡ ይህ ለምን ይሆናል?  የሚባለውን ልናገር የነዚህ የሞቱ ወታደሮች የወር ደሞዝና ሎጀስቲካቸው ስለሚቋረጥ የዋናዎቹ አመራሮች ጥቅም ለመጠበቅ ተብሎ ነው ልብ በሉ፡፡ ከሰዎች ክብር ሕይወት በላይ ለሆዳሞች ጥቅም የበለጠ የሚቆረቆር አመራር ነው ያለን፡፡ የደም ዋጋ የሚበላ፤ የከዳውን ቤት ይቁጠረው፡፡ እናስ እንዲት አድርገን ነው የታሰበውን ውጤት የምናመው?”  በማለት ጥያቄ አቀረበ፤ አዳራሹ በጭብጨባ ተናወጠ።

መድረክ መሪው አካሄድ እንደዚህ መሆን የለበትም፡፡ ከአጀንዳ መውጣት የለብንም፡፡ በተነሱ ነጥቦች ብቻ ነው መወያ ት ያለብን፡፡ የሚል ማሳሰቢያ ነገር ተናገረ። ከዚያም አንድ የክልል ከፍተኛ አመራር የሆነ ለሆድ ያደረ አድር ባይ ወዳጄ እነዚህን ሲጠራቸው “ባሪያዎች” ይላቸዋል፡፡ የመድረክ መሪውን ሃሳብ የሚያጠናክር አስተያየት ጨመረ፡፡ ከዚያም በመቀጠል አንድ ተሰብሳቢ እጁን አነሳ እድል ተሰጠው እሱም “እኔ እንደምረዳው ችግሩ ያለው ከዓላማ ላይ ይመስለኛል፡፡ ይህም ከላይ ያለነው ባለስልጣናት ትዕዛዝ እናወርዳለን፡፡ የበታች አካላት ትዕዛዙን አይፈፅሙም፡፡ ለምንድን ነው? ስንላቸው እኛ እየሂድን ሕይወታችንን እያጣን፤ አካላችንን እያጣን ሊላው ግን ራሱንና ቤተሰቡን በምቾት አንደላቆ ያኖራል፡፡ እኛ ውጊያ ላይ ሆነን አመራሮች ግን ጮማ እየቆረጡ፤ ውስኪ እየተራጩ፣ ሴቶችን እያማገጡ፤ እጅግ ውድ በሆኑ ሆቴሎች በልዩ ጥበቃ እየተጠበቁ ሲዝናኑ፤ እኛ የድሃ ልጆች ማንን ለማኖር ነው የምንሞተው?  የሚል ጥያቄ ያቀርባሉ፡፡

“….  ከዚህ ላይ እኔ እንደተረዳሁት የዓለማ ችግር ያለ ይመስለኛል፡፡ ተልዕኮ ተሰጥቶት ለስራ የሚሄደው አካል ለምን ጉዳይ እንደሚሄድ እንኳን አያውቅም፡፡ ይህ ነጥብ ቢታይ ጥሩ የመስለኛል፡፡” በማለት ተናገረ፡፡ ከመድረክ አሁንም ሌላ አስተያየትና ጥያቄዎች ካሉ ቀጥሉ በማለት ተናገረ፣ ድንገት የሻይ ስዓት ደረሰ በብሎ እረፍት ተወጣ፡፡

Filed in: Amharic