>
5:13 pm - Saturday April 19, 9569

ለካርታውስ ይቅርታ ተጠየቀ! ሕገ መንግሥቱ እንዴት ይስተባበል? (መላኩ ተስፋዬ)

ሰሞኑን በኢቢሲ የተላለፈውን ካርታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ብዙ አነጋግሯል፤ ከዚያም አልፎ ‹‹ይቅርታ›› ተጠይቆበታል- ማዘናጊያ ቢሆንም፡፡
ግን የአማራ ‹‹ክልል›› ከሱዳን ጋር እንደማይዋሰን የሚያሳየው ካርታ በሕግ የጸና መሆኑን ስንቶቻችን እናውቃለን? ቤኒሻንጉል ጉምዝና የትግራይ ክልሎች ጎረቤት መሆናቸውን በሕግ የተደነገገ መሆኑን ስንቶቻችን ተገንዝበናል?
ከሽግግሩ መንግሥት በኋላ የተቋቋሙ ‹‹ክልሎች›› የራሳቸውን ሕገ መንግሥት አጽድቀዋል፡፡ ከነዚህም አንዱ የጎጃም ለም መሬቶችን ይዞ የተቋቋመው ‹‹ክልል›› ቤኒሻንጉል ጉምዝ ነው፡፡ በዚህ ክልል ሕገ መንግሥት መሠረት የአማራ ‹‹ክልል›› ከሱዳን ጋር አይጎራበትም፡፡ በ1988 ዓም በጸደቀው በክልሉ ሕገ መንግሥት መሠረት ክልሉን በሰሜን በኩል የሚያዋስነው የትግራይ ክልል እንደሆነ ቁጭ አድርጎ በአንቀጽ ሁለት ይናገራል፡፡ በዚህ መሠረት እነ ጃዊ፣ ቋራና መተማ የቤኒሻንጉል ሲሆኑ እነ አርማጭሆ ደግሞ ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጋር የትግሬ ሆነዋል ማለት ነው፡፡ ትግርኛ ስለማልችል የታላቋ አዲ ትግራይ ሕገ መንግሥት ምን እንደሚል አላውቅም፡፡
አሁን ጥያቄው የካርታውስ ጉዳይ በይስሙላ ይቅርታ ታለፈ! የተሰረቀው ተራራና የተሰረቀው ቤተ መቅደስም አፉ በሉን ተብሎ ተመለሠ፡፡ ይህ ሕገ መንግሥት ምን ዓይነት ማስተካከያ ሊደረግበት ነው? የሚለው ነው፡፡
ይህን የያዘውን የቤኒሻንጉል ክልል ሕገ መንግሥት ክፍል በፎቶው ላይ ይመልከቱ፡፡

fb_img_1504101025769 fb_img_1504101007599

Filed in: Amharic