>

''ጣና ሀይቅ ደረቀ ማለት ናይል የለም'' (የግብፅ ጋዜጠኛ በጣና ዙሪያ)

ሰሞኑን እውቁ ግብፃዊ ጋዜጠኛ እጅግ አስገራሚ ነገርን ፅፎዋል። የጣናን ሀይቅና የአባይ ወንዝን ስጋት ላይ የጣለው የእንቦጭ ጉዳይ ግብፅ በቀላል አታየውም በቅርብ በሚስጥር የሱዳንና የግብፅ የውሀ ሀብት ተንታኞች ተገናኝተው ስለጉዳዩ እያዩ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስ የሀገሪቱ ህልውና ዋና ማገር የሆነውን ይህን ጉዳይ ዝም ማለቱ ትልቅ ግርምትን እንደፈጠረባቸውና ይህን ጉዳይ በቸልታ ማየቱ ለምን የሚል ጥልቅ የሆነ ጥናትን እያካሂያዱ መሆኑን ዘግቡዋል።
የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ሚዛን የሀገሪቱ ትልቅ የውሀ ሀብት በዚህ መልኩ ተወሮ አገሪቱን የሚመራው መንግስት ህዝብ በጉልበት ወቶ ይህን ሲያደርግ በዝምታ ማለፉ ትልቅ ጥያቄን አጭሩዋል ሲል በሰፊው አተታውን ሰቱዋል።
ጋዜጠኛው ሲቀጥል ” የጣና እና የአባይ ስጋት የሆነው ይህ እምቦጭ የተባለው ጉዳይ በዚሁ ቀጥሎ የማይቆም ከሆነ አገሪቱን ወደከፋ ችግር ከመዳረጉም በላይ የፖለቲካውን አለመረጋጋት ያባብሰዋል የሀገሪቱ 55% የዝናብ ምንጭ የሚመነጨው በዚህ ሀይቅ እና በአባይ ወንዝ ነው ይህም ስጋት ካሁኑ ካልተቀረፈ ፈፅሞ ማቆም የማይችልበት ደረጃ ደርሶ ሀይቁ ከመድረቁ በላይ የአባይ ወንዝ ስጋት ይሆናል ሲልም አትቱዋል “

ከዚህም በተጨማሪ የኛ መንግስት በዝምታ ሊያየው አይገባም አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን ነገሮች መጀመር አለበት ሲል የአገሩን ግብፅ መንግስት በውስጥ ከሚደረግ ስብሰባ ወቶ ግልፅ የሆኑ እርምጃወች ይውሰድ ሲልም ተችቱዋል። የጣና ሀይቅ የኢትዮጵያ ህልውና ብቻ ሳይሆን የግብፅም ነው በሚል ትልቅ ወቀሳንም ሰንዝሩዋል።
ይህን ጉዳይ ግብፅ በቅርበት እዛው ጣና ድረስ በድብቅ ሌሎች ሰወችን አስልካ መረጃውን በቪዲዮ ቀርፀው ለሚመለከተው አካል ያቀረቡ ሲሆን ምናልባት ለህዝቡ ይፋ ቢወጣ ከባድ ነው ሚሆነው በሚል ለመሸፋፈን ቢሞክሩም በናይል ወንዝ የግብርና ምርምር የሚያደርጉት ግብፃዊው አህመድ ግን ” ይህ ጉዳይ ከባድ ነው ፈፅሞ ናይልን ሊያሳጣን ይችላል ውሀን መጦ የማድረቅ አቅሙ ፈጣን ነው ። ጣና ሀይቅ ደረቀ ማለት ናይል የለም ስለዚህ መንግስታችን ይከታተለው ብለዋል። ትናንት ማምሻው ላይ የመረጃውን ጥልቀት በስፋይ የተመለከቱት ሲሆን በቀጣይ የቱም ነገር ይሁን የኢትዮጵያ መንግስት ዝምታው አስገራሚ ነው የሀገሪቱ ህልውና የሆነን ሀብት በዝምታ ማየቱ ግራ እንዳጋባቸውም ተንትኑዋል። የሱዳን ጋዜጣ” ጣና የኢትዮጵያ ህልውና” በሚል በፃፈው ፅሁፍ የሀገር ትልቅ መሰረት በዚህ ደረጃ መሆኑ እየታየ እዚህ ደረጃ እስኪደርስ ለምን ተጠበቀ በሚል ሰፋ ያለን መረጃ ይዞ ወቱዋል።

የጣና ሀይቅ አደጋ ካልተቀረፈ ሙሉ ኢትዮጵያ በረሀማ ከመሆኑዋም በላይ የዝናቡዋ ምንጭ የሆነው አባይ መነሻው ይህ ሀይቅ ነው እናም ሱዳን ይህን ጉዳይ ቸል ልትለው አይገባም ሲል አፅኖት በመስጠት ተንትኑዋል።

የግብፅ ሌላኛው ዌብ ሳይት ደግሞ ይህን ጉዳይ ወደ ፖለቲካ ትኩሳት ቀይሮታል ግብፅ ይህን በመጠቀም የበላይነቱዋን ልታሳይና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቅኝ ገዥዋን እንግሊዝ ስምምነት ሽረው ግድብ እንዲሰራ ያዙዙ የግብፅን የበላይነት በናይል ላይ ዋጋ ያሳጡት እሳቸው ናቸው የግብፅ የበላይነት አይሰራም የኢትዮጵያን የአባይ ወንዝ የበላይነት በራሳቸው አውጀው ጀምረውታል አሁን ግን እሳቸው የሉም አሁን ያለው መንግስትም የጣናን ጉዳይ ከመለስ ዜናዊ አቁዋም በተለየ ጭራሽ ከመከላከል ይልቅ በታዛቢነት ዝም ብሎ እያየው ነው የግብፅ መንግስታችን በዚህ ሰአት የአባይን ጉዳይ የበላይነት መውሰድ አለበት በሚል ፅፉዋል።

Arbegna Gobe 
Filed in: Amharic