>
1:40 am - Thursday July 7, 2022

ማየት ማመን ነው (ሙላት በላይ)

ህወሀት በረሀ የገባው አማራን ለማጥፋትና የቅዠቷን ታላቋን ትግራይን ለመመስረት  ከንቱ ህልም ይዞ ነው፡፡ ይህን የቅዠት ህልሙን እውን ለማድረግና ዓላማውን ለማሳካት በውሸትና በቅጥፈት ያልፈነቀለው ድንጋይ  ያልቆፈረው ጉድጓድ የለም፡፡  ይህንን እኩይ ራዕዩን ለማስፈጸም ኢትዮጵያን አዋርዷ፡፡ ያለባህር በር አስቀርቷል፡፡ እንደ ሰንበቴ ቂጣ ቆራርሶ ለባዕዳን ሰጥቷል፡፡ በዜጎች በተለይ በአማራው ላይ ከሰማይ በታች ያልፈጸመው ግፍና በደል የለም፡፡ ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ

1  በረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ በየትኛውም የገዥዎች ዘመን አማራው ተጠቃሚ ሆኖ አያውቅም፡፡ ይልቁንስ ለዳር ደንበሯ አንድያ ህይወቱን ሲገበር ኖረ እንጂ፡፡ ህወሃት ግን በአለፉት የግዛት ዘመኖች ሁሉ ኢትዮጵን ሲገዛ የኖረው አማራ ብቻውን እንደሆነ አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል፡፡  ከአዋቂ እስከ ህጻናት አማራው በጨቋኝነትና በገዳይነት ተስሎ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ጭራቅ ተቆጥሮ «አማራ መጣብህ» ተብሎ ማስፈራሪያ እስከመሆን ደርሷል፡፡ የዋሁ አማራ ወገኔ ነው በሚለው ህወሃት ወያኔ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ሆኖ ለፕሮፐጋንዳ ፍጆታ ውሏል፡፡  ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው አቶ ገብረመድን አርአያ በጽሁፍ የአቀረቡት የሟቾች ስም ዝርዝርና እቶ አስራት አብርሀም ከአገር በስተጀርባ በተባለዉ መጽሀፋቸዉ ገጽ 80 ላይ ያሰፈሩት ነዉ፡፡

«ከልጅነት ትዝታዎቸ ሁሉ የሚገርመኝ እማማ ማታ ማታ እንቅልፍ እከሚወስደኝ ድረስ ስለ አማራው የደርግ ወታደር የምትነግረኝ ነው፡፡ የህም የደርግ ወታደሮች ሰው ሳይሆኑ ከብረት የተሰሩ አካላቸዉ ሁሉ ብረት የሆነ የአገኙትን ቤት ሁሉ የሚያቃጥሉ የአገኙትን ሰው ሁሉ የሚገድሉ ከቤት የአገኙትን ድመት አህያ የሚበሉ ስትለን እኛ በጣም እንፈራለን መፍራታችን ስታውቅ ደግሞ አይዟችሁ እኒህ ወታደሮች ታጋይዎችን ከአዩ ፈሪዎች ናቸው፡፡ በሩጫ ድራሻቸው ነው የሚጠፋ ተለናለች»:: እንግዲህ አንባቢ ልብ ሊለው የሚገባ ነገር ህወሀት ወያኔ እኩይ ተግባሩን ለማስፈጸምና  ለእለታዊ ጥቅሙም ሲል ምን ያህል የወረደ ውሸት እንደሚዋሽ ይህ ዓይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ወያኔ የወደፊቱ የትውልድ እጣ ፈንታም አያሳስበውም፡፡ ያ ባይሆን ኖሮ ተፈጻሚነት ለሌለው ህልሙ ትውልድ ሊያጫርስ የሚችል የፈጠራ ታሪክ ባልፈበረከም ነበር፡፡ ለማይፈጽም እኩይ ቅዠቱ የመሬት ስርቆት ውስጥ ባልገባም ነበር፡፡

ህወሀት አነሳሱ የዝቅተነት በሽታ ነው፡፡ ዝቅተነትን ደግሞ የማይድን ክፉ ልክፍት ነው፡፡ ይህንን በሽታውን ለማስታመም ዘርን ቆጥሮ በጠባብነት ስሜት ደጋፊዎቹን ያሰባስባል፡፡ የተቋወሙትን ሁሉ በጭካኔ ይገላል፡፡ ለዚህ ነው ህወሀት ወያኔ ገና ከጅምሩ  በደም የተዋጀ ድርጅት የሆነው፡፡ በመንግስትነት ስም ተሰይሞ በታሪክ ቀደምት የሆነችና የታላቅ ህዝብ ሀገር የሆነች ታላቅ ኢትዮጵያን ይዞ የጠባብነት፣ የአናሳነትና የዘረኝነት በሽታው ያለቀቀው በህግ የማይገዛ አናሳ ቡድን ነው፡፡

2 ህወሀት ሕገወጥ ድርጅት ነው፡፡ ለስሙ ህግ የሚፈጽሙ  የህዝብ ተወካዮችን አስመረጥኩ ይልና ቀድሞ ሕጉን የሚያፈርስ ቡድን ነው ህወሃት፡፡  ወያኔ  በየጊዜው አዳዲስ ሕጎችን በመፍጠር በዓለም አንደኛ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በየጊዜው በሚያወጣቸው ህጎች ዜጎች በነጻነት እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓል፡፡ ዲሞክራሲን በኢትዮጵያ ምድር ጨርሶ በማጥፋት ያስራል፣ ይገርፋል፣ ከአሻውም ይገላል፡፡ መለስ በአንድ ወቅት

« ህጋችን ለማታከብሩ ማንም አያድናችሁም፡፡ ፈረንጅ አያስጥላችሁም፡፡ አበሻ አይደርስላችሁም…..» ሲል ተናግሯል፡፡ ሽማግሌው ስብሀት ነጋ በ2007 በአደረገው ቃለ ምልልስ

«ያወጣነው ህገመንግስት ከፈረሰ አገር ይበተናል፡፡ እኛም ወደ መንደራችን እንሄዳለን እነደገናም እንዋጋለን፡፡ ለኛ ሥራ ተቃራኒ አመለካከት የአላቸው እስረኞች ናቸው፡፡ ለሚቃወመን  ጦርነት እናወርዳለን፡፡ እኛን የሚቃወም አመለካከት ያለው እስርቤት ይገባል፡፡ ባይገባም እስረኛ ነው፡፡» በማለት የመለስን ንግግር አጠንክሮ የእብሪት ንግግር ተናግሯል፡፡ የለምንም ተቃውሞ መገዛት እንዳለባቸው እንዲህ በድፍረት የሚናገሩት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካላቸው ንቀት የተነሳ ነው፡፡ በአንድ ላይ ተነስተን ይህንን እብሪታቸውን እንዳናበርድ ደግሞ በዘረጉልን ወጥመድ ሰተት እያልን እየገባንላቸው በተናጥል እየሞትን ነው፡፡ እነሱ እንደሆን የህዝብ ዐመፅ እነዳይኖር ነጣጥሎ ለመምታት ያመቻቸው ዘንድ  ጎሳን ከጎሳ ነገድን ከነገድ ቀበሌን ከቀበሌ ሀይማኖትን ከሀይማኖት በቆስቋሽነት እያናከሰን ይገናሉ፡፡ ወያኔዎች በዚህ እንኳ አያቆሙም እኩይ ተግባራቸውን ለማስፈጸም እስከታች ይወርዳሉ–እስከ ባልና ሚስት፡፡ አሁን የቀረው የባልና ሚስት ጥል ዘመቻው ነው እንጂ ሁሉም ወቅቱን እየጠበቀ ተፈጽሟል፡፡

3–ለዚህ ሁሉ የሀገርና የወገን ውድቀት ተጠያቂው ማን ነው?

ተጥያቂዎች እኛው ራሳችን ነን፡፡ ህወሃት ወያኔማ ገና ደደቢት ላይ ጥቂት ሆነው ሲመሰረቱ ዓላማቻውንና ተልዕኮዋቸውን  ቁልጭ አድርገው ነግረውናል፡፡ በማኒፌስቷቸው አስፍረው አሳውቀውናል፡፡ በዘፈኖቻቸው ፎክረውብናል፡፡ በግጥሞቻቸው ዝተውብናል፡፡ በየስብሰባቸው ያለምንም ማመንታት ተዘባብተውብናል፡፡ አሁንም እየነገሩን ነው፡፡ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ሲገዙንም ወደ ኋላ ሳይሉ በተለይ አማራውን ከምድረገጽ ለማጥፋት እየነገሩን– በተግባር እያሳዩን–  ሰርተዋል፣ ተንቀሳቅሰዋል፣፡፡

እኛ ነን  እየሰማን ያልሰማን፡፡ እኛ ነን እያየን ያላዬን፡፡ እኛ ነን እየተደበደብን ያላመመን፡፡ እኛ ነን ሲያርዱን ያልተፈራገጥን፡፡ ከዛሬ የበለጠ ኢትዮጵያውያንን እጅ ለጅ አያይዞ በዚህ እኩይ የማፍያ ቡድን ላይ የሚያስነሳ ከቶ ምን መከራ መምጣት አለበት? ዛሬ በወገናችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ፣ስቃይና ሰቆቃ ከገሀነ እሳት አይበልጥምን? ከዚህ በላይ የጋራ በደልና ግፍ ምን ሊያስተሳስረን ይሆን? ይህንን አጥፍቶ ጠፊ ቡድን በአንድ ላይ ሆ!! ብለን ተነስተን አለማስወገዳችን ከቶ ምን ይሉታል?

Filed in: Amharic