>
4:34 pm - Tuesday October 17, 0197

"ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ድረስ ነው" (ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝ)

ትላንትና ጥቅምት 3/2010ዓም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የለአመክሮ መንግስት የፈረደበትን የግፍ ፍርድ ሙሉ ለሙሉ ጨርሶ የሚወጣበት ቀን ነበር! ቢሆንም የዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች ተመስገንን “አንፈታም” ብለዋል። እኛም አንፈታክም ያሉትን ልንነገረው  ቆመን እየጠበቀን ነበር ምን ተብሎ እንደሚነገር እያሰብኩ የከበቡን ሦስት ወታደሮች ተመለከትኩ የኛን መውጫ ዘግተው ቆመዋል ያውም በተጠንቀቅ ከደቂቃ በኃላ 2 ወታደሮች ከፊት ሌላ ሁለት ወታደር ከኃል አንድ ወታደር ከጎን ሆኖ ተመስገንን ከበው ሲመጡ አየሁ ሰዓቱ ከቀኑ 9 ሊሆን 1 ደቂቃ ይቀረዋል እለቱ አርብ ነው ተመስገን የተናገረውን አስታወስኩ “ለሀገሬ ስል ጉዞዬ እስከ ቀራኒዬ ድረስ ነው” ያለውን። በዕለተ አርብ ቀን ጌታችን መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቀን ልክ 9 ሰአት ላይ የጌታችን ነብስ ከስጋው የተለየችበት ሰዓት መሆኑንም አሰብኩ አሁንም 9 ሰዓት ላይ ለሀገሬ ስል ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ነው ያለው ተመስገን በወታደሮች ተከቡ ሲመጣ አየሁት ተመስገን ቀራኒዮ ያለውን አሰብኩት።
ደግሞም ይቺ አርብ ቀን በስልምና እምነት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለት ወዷ የጁማ ቀን ነች። ለብቻ የሚደረግን ሰ

ግደት አርብ እለት በመሰባስብ በአንድነት በመስኪድ የሚሰገድባትም ቀን ነች። በዚህች አርብ ቀን ነው ተመስገን በአምስት ወታደሮች ተከቦ ሲመጣ የማየው። ተመስገን ፍትህ ብሎ የጠየቀባት ሁሉም የሰው ልጆች ሰበአዊ መብት ያለቅድመ ሁኔታ ለሁሉም በኩል ይከበር ያለበት ተመስገን አንባገነኖቹን እህስ ለማለት አደባባዩ ምን ያሀል ይርቃል ብሎ እርቀቱና መነሻውን ያለካበት. ተመስገን ሲኖዶሱና መጅሊሱ ህብረታቸው ከቤተ መንግስት ሳይሆን ከእምነታቸው ጋር እንዲሆን ያሳሰበበት ተመስገን የአቢዮቱን አይቀሬነት ቡሎም አቢዮቱ እንደሚነሳ ብቻ ሳይሆን  ከየት እንደሚነሳ ጭምር ሀኔታውን ተንትኖ ያስቀመጠበት ሞት የማይፈሩ ያላቸው ወጣቶች ወደ አደባባዩ ያመሩበት ኢትዮጵያዊነት ዋጋው ስንት ነው ያለበት የፈራ ይመለስ ብሎ አቢዮቱ የፈጠረበት ለዚሁሉ መነሻ የሆነው የፍትህ ጋዜጣ የምትወጣበት ቀን በዚህችው በዕለተ አርብ ነው።

ይህን እያሰብኩ ቀድሞም ያልነበረው ፍትህ ዛሬም እንደሌለ የሚያውቀው ተመሰገን በአምስት ወታደሮች ተከቡ በፈገግታ አጠገባችን ደረሰ ሰለምታ ከተለዋወጠን በኃላ አየኝ አስታየቱ ጠያቄ እንደሆነ ስለገባኝ “ቀንህን እንደጨረስክ እናውቃለን ግን አንፈታክም” ብለዋል አልኩት። የፊቱ ፈገግታው አልጠፋም ለማሰብም ግዜ አልወሰደም ምን መሰላችሁ ብሉ መናገር ጀመረ “ምን መሰላችሁ እዚህ እስር ቤት ውስጥ አንድም እስረኛ ከሶኝ አያውቅም እስር ቤቱም በቆይታህ ግዜ ይህን አድርገሀል ብሎ አናግሮኝ አያውቅም ምን የስነስራአት ጠፋት አደረክ ተብዬ አላውቅም አመክሮ ባልገመገምም አመክሮ የሚያስከለክል ምክኒያት የላቸውም ነበር አመክሮም ተከልክልሃል ያለኛ ማንም የለም አመክሮ እንደተከለከልኩ ያወኩት ከእስር ሳልፈታ ስቀር ነው ይህ ደግሞ በኔ እንጂ በሌላ እስረኛ ላይ ሆኖ አያውቅም። ፍትህ ዛሬ አይደለም እንደሌለ የማውቀው ዛሬም እስሩ ፖለቲካዊ እንደሆነ ተጨማሪ ምክኒያት የሚሆን ነገር ነው የገኘሁት። ለማንኛውም ፍርድ ቤቱ ፍትህ ባይኖረው የሚያውቀው ዛሬ እንደተፈታሁ ነው ካአሁን በኃላ ያለሁት በዝዋይ እስር ቤት ሀላፊዎች እጅ ነው” አለን የከበቡትን 8 ወታደሮች አየተመለከተ መረጋጋቱና ፈገግታው ሳይጠፋ “ማዘርን ሰላም ብልልኝ እናተም እንዳይመሽባችሁ ሄዱ” ብሎን እንደ አመጣጡ ተመልሶ በወታደሮቹ ተከቡ ሄደ።
ከፍርድ ቤት ጀምሮ “እኔ የምከራከረው ነፃ ለመሆን አይደለም ለታሪክ ነው ፍርዱም የፍርድ ቤቱ እንዳልሆነ አውቃለሁ” ብሎ የፍርድ ቤቱን ሙግት የጀመረው ተመስገን በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎ የቅጣት ማቅለያ አቅርብ ሲለው ተመስገን “ቀድሞንም ተናግሬ ነበር ውሳኔው ፖለቲካዊ እንደሆነ ጥፈተኛ ስላልሆንኩ ምንም የማቀርበው የቅጣት ማቅለያ የለኝም” ማለቱ የሚታወቅ ነው።
ተመስገን ዛሬም የሚከብር የሚተገበር ህግ በሀገሪቷ ውስጥ እንደሌላ ያውቃልም ይረዳልም ለዚህ ነው ተመስገንም ህግ ይከበርልኝ ሳይል ፍትህ በሌለበት ፍርድ ቤት ተፈርዶብኝ አሁን ደግሞ በዝዋይ እስር ቤት ሀላፊ ወታደሮች እጅ ነኝ ብሎ ወደ እስር ክፍሉ ያመራው።
እኛም ህግ የለምና ህግ ይከበር አንልም ከዚህ ያልቅ “እኔ ለሀገሬ ስል ጉዞዬ እስከ ቀራኒዮ ደርስ ነው” ያለውን የተመስገንን ቃል እናከብራል። ዛሬም በዚህች አርብ ቀን በዝዋይ እስር ቤት ፍትህ በተመሰገን ላይ ድጋሚ ተቀበረች።
የተሠበረ ክንፍ ከቶም ባይጠነክር 
አያድርም ተኝቱ ለመብረር ሳይሞክር
የታሠረ እግር የተቀማ ብዕር
አያልምም ሌላ ከነፃነት በቀር
(ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከጊዜ ለኩሉ መፅሀፍ ከዝዋይ እስር ቤት ከፃፍው ግጥም)
ጥቅምት 4/2010ዓም
Filed in: Amharic