>

ወያኔና ~የግብፅ አብዮት ጠ..ር..ጥ..ር.. (መኮንን ከበደ)

አሁን በኦሮምያ እየተከናወነ ካለው አመጽ እና ከፍተኛ የኢህአዲግ የፓርቲ አመራሮች የስራ ሀላፊነት መልቀቅ ጀርባ ያለው ህወሀት ሀገራዊ ትርምሱን እየገመገመ በዝምታ አድብቷል ።
ማን እየመራው እንዳለ ባልታወቀው የሰሞኑ አመጽ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ተነስተዋል ። የፀጥታ ሀይሎች ከህዝቡ ጎን ቀመው ታይተዋል ። የኦሮሞ ህዝብ አካል ያልሆኑ ግለሰቦች የኦነግ ባንዲራ ሲበትኑ ተይዘዋል ። አፍቃሪ ህወሀቶች በደስታ ከወትሮ በላቀ ዘግበውታል ። ከፍተኛ አመራሮች ስልጣን መልቀቂያ አስገብተዋል ። አመፁም ያለውግዘት ቀጥሏል ። እርግጥ ስርአቱ የላካቸው ነፍሰ ገዳዮች በተወሰኑ ቦታዎች ሠዎችን እየገደሉ ነው ። አንዳንድ ቦታ የንብረት ውድመት ተመዝግቧል ።
ለምን ስልጣን የሚለቁ ባለስልጣናት የውጭ ሀገር ጉዞ አልታገደም? ከፍተኛ ሚስጥር የያዙና ሙሰኛ መሆናቸው ለወያኔ ካለው ስጋትም ሆነ ጥቅም አንጻር ከሀገር ሲወጡ ህወሀት በር ከፍቶ ማሳለፉ የሚናቅና በቸልታ የሚታይ አይደለም ።
1. አዲሱ የወያኔ ስልት ሊሆን የሚችለው ያጣችውን ህዝባዊ ተቀባይነት አርቴፊሻል አመፅ በመቀስቀስ (መልእክቱ ምን ይሁን ምን) ማጋጋል እና ዉጥረት መፍጠር ለወያኔ ይጠቅማል ።
2. ከፍተኛ አመራሩ ስልጣን እንዲለቅ ማግባባት :- ፖለቲካ አመራሩ ስልጣን እየለቀቀ በሳሳ ቁጥር ኢህአዴግ እየተዳከመ ይሄዳል። ይህ ፓርቲ እድሜው እንዳበቃ ወያኔ ታውቃለች ። ስለዚህ ሙት ፓርቲዋን ለመቅበር የህወሀት ቀጣይ ስጋቶችና የበቀል ሰለባዎችን ለመምታት (ኦህዴድና ብአዴን) ከጨዋታ ለማስወጣት መስራት አለባት ። የነዚህ አባል ድርጅቶች እና አመራሮች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፈጠሩት ህዝባዊነት እና ህብረት ጨርሶ ያልታሰበ ነው ። ከህወሀት ማኒፌስቶ ከራእይዋም ውጭ ነው ። በዚህም ሁለቱም የትምክት እና ጥበት ምሳሌ ተደርገዋል ።
ህወሀት በህዝብ ጥላቻ መደበቂያ ባጣችበት በዚህ ወቅት ሚሊተሪው ብቸኛ ይዞታዋ ሲሆን ወያኔ የቀራት እድልም እሱው ነው ። ስለዚህ ብጥብጥ በጨመረ ቁጥር የሚሊተሪው ተፈላጊነት ይጨምራል ። በስራ መልቀቂያ ሽፋን ማእከላዊ መንግስት በተዳከመው ልክ የወያኔ ሠራዊት ያለ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን እንዲጨብጥ አለም አቀፍ ተቋማትን መገዳደሪያ ነጥብ ታገኛለች ። ሜዳው ይመቻቻል ። ሀገር ማረጋጋት እና ህገ መንግስታዊ ግዴታ ለመወጣት የሚሉ ሀረጎች ሽፋን ይሆናሉ ።
የግብጽ አብዮት ሙባረክና ባለስልጣኖቹን ነፃ ለማድረግ ጄነራሎቹ የዋሉትን ውለታ ወያኔ ታውቃለች ። ለራስዋም ለጅብ ልጆችዋም ደህንነት ስትል ዘዴው አርጌውን ትራስ በአዲስ ቀይራ ማሰቢያ ቀን መኖሪያ እድሜ ፍለጋ አድብታለች ።

Filed in: Amharic