>

የኬንያ ሁለተኛ ምርጫ ሊካሄድ የቀረው ጊዜ 24 ሰዓታት ብቻ ነው (ዮናስ ሃጎስ)

ሰዎች  ምን እያሉ ነው?
***
«ገዥዢውም መደብም ሆነ ተቃዋሚዎች ሁከት ከማነሳሳትና ሐገሪቷን ወደ ብጥብጥ ቀጠና ከመቀየር መቆጠብ አለባቸው። ሰዎች መምረጥ ሕገ መንግስታዊ መብታቸው እንደሆነ ሁሉ ያለ መምረጥም ሐ ገመንግስታዊ መብት ነውና ጉዳዩን በስምምነት መቋጨት ያስፈልጋል። ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተልነው ነው።»
በአሜሪካ አምባሳደር የተመራው የውጭ ዲፕሎማቶች በኬንያ ስብስብ
***
«ለኬንያ እየፀለይኩኝ ነው…»
የካቶሊክ ጳጳስ ፖፕ ቤኔዲክት
***
«የካቶሊክ ጳጳስ ሁሌም ለሁሉም ሰው ፀሎት እንዳደረጉ ነው። ይመስለኛል ስራቸው እንደርሱ ነው። ይበልጥ ግን ለኡሁሩ ኬንያታና ለዊልያም ሩቶ በስርቆትና በሙስና ለበሰበሰች ነፍስ ቢፀልዩላቸው መልካም ነበረ። የውጭ ዲፕሎማቶች ያልገባቸው ነገር እኛ ለነፃነታችን ነው እየታገልን ያለነው። ነፃነታችንን እስክናገኝ ድረስ ሐገር የብጥብጥ ቀጣና ትሆናለች ብለን ወደኋላ የምናፈገፍግበት አንዳችም ምክንያት የለም። እነርሱ በኬንያ ውስጥ ስላሉ የቢዝነስ ተቋሞቻቸው ደህንነት ስጋት ላይ ስለሆኑ ነው የሚያለቃቅሱት። እኛ ደግሞ የምንጨነቀው ስለኬንያውያን እና ስለ መጪው ትውልድ ነው። እነዚህ ዲፕሎማቶች ስለ ኬንያ ከሚጨነቁ መጀመርያ ኦልሬዲ የብጥብጥ ቀጣና የሆነችውን ሶማሊያን ሄደው ያረጋጉ።»
ጄምስ ኦሬንጎ የተቃዋሚው ቡድን ናሳ ጠበቃ
***
«እኛ ለምርጫ ዝግጁ ነን። የምርጫ ካርዶች ሕትመታቸው ተጠናቅቆ በሐገሪቷ በመሰራጨት ላይ ናቸው። ከማንም ጋር የምናደርገው ንግግር የለም። የምርጫ ሳጥኑ ነው የሚገላግለን። ጓዶች እባካችሁ ይህን ነገር በፍጥነት አጠናቅቀን ወደ ስራችን እንመለስ?»
ኡሁሩ ኬንያታ፤ ፕሬዝዳንት
***
«ኡሁሩ ወደ ስራ እንመለስ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ታውቃላችሁ? ወደ ዝርፍያችን፣ ወደ ሙስናችን እንመለስ ማለቱ ነው። ያ እንዲሆን ደግሞ እኛ አንፈቅድም። ኬንያ ባለፉት 5 ዓመታት የዕዳዋ መጠን ከትሪሊዮን ሺሊንግስ በላይ ሆኗል። በሙስና የተማረሩ የውጭ ድርጅቶች ለኬንያ የሚያደርጉትን ድጋፍ አቋርጠዋል። ለምሳሌ በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት ለጤና ጥበቃ ሚንስትራችን ይሰጥ የነበረውን ድጋፍ “ባለስልጣናቱ ሙስና እየበሉ ስላስቸገሩ” በሚል ይፋዊ ምክንያት ማቆሙን አስታውቋል። ይህን ነገር ላንዴና ለመጨረሻው ጊዜ የምንቀይርበት ሰዓት ደርሷል። ሐሙስ ምንም ዓይነት ምርጫ አይኖርም!»
ራይላ ኦዲንጋ የተቃዋሚው ናሳ ቡድን መሪ
***
«ሐሙስ ዕለት በሞምባሳ ምንም ዓይነት ምርጫ ልታካሂዱ ከሞከራችሁ ሕገ መንግስቱ በሰጠን መብት ተጠቅመን የመገንጠል ጥያቄ እናቀርባለን!»
አብዱናስር የናሳ የፓርላማ ተወካይና የሞምባሳ ሴናተር
***
«አሁን የሚደረገው ምርጫ ነሐሴ ከተደረገው ምርጫ በላይ ብዙ ሕገ መንግስታዊ ነገሮች ያልተሟሉለት ስለሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ እንደሚያደርገው ምንም ጥርጥር የለውም።»
አኮምቤ፤ በቅርቡ ስራዋን የለቀቀችው የምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር
***
«ስለሌላው አያገባኝም። እዚህ ኪሱሙ ግን ምርጫ ይካሄዳል ብላችሁ በፍፁም እንዳታስቡ!»
የኪሱሙ ገቨርነር
Filed in: Amharic