>

የአግዓዚ ጦር ከ10 ሰዎች በላይ ገድሎ ብዙ ሰዎችን አቁስሏል (ዮናስ ሃጎስ)

«ካሁን በፊት አግዓዚ የሚባል ኃይል የለም። ሁሉም ክልል የራሱ ልዩ ኃይል አለው። ስለዚህ አንድ ክልል ችግር ሲፈጠር ቀድሞ የሚደርሰውም ሆነ እርምጃ የሚወስደው የዛው ክልል ልዩ ኃይል ነው…» የሚል ነገር አግዓዚን ለመከላከል ከብዙ የትግራይ አክቲቪስቶች ይሰማ ነበረ።
***
የአግዓዚ ጦር ወያኔ በ1997 የደረሰበትን ቀውስ እንዲያዝን በልዩ ሁኔታ ሰልጥኖ ስራ የጀመረ ቡድን ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየቦታው በተላከበት እየተወረወረ የወያኔን የስልጣን ጊዜ ለማራዘም ሲባል በሲቭሎች ላይ ጭፍጨፋ የሚፈፅም ጦር ሆኖ ቀጥሏል።
***

ይህ ጦር ዛሬም በአምቦ ተገኝቶ ከ10 ሰዎች በላይ ገድሎ ብዙ ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል። እንደገናም የአምቦ ክልል ኮሚኒዩኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጋዲሳ ደሳለኝ የተሰማራው ጦር የአግዓዚ መሆኑን አፍረጥርጠው

ተናገሩ።

***
ተቃዋሚዎች አግዓዚ ነው የዘመተብን ምናምን ሲሉ «አግዓዚ የሚባል ነገር የለም… ሁሉም ክልል የራሱ ጦር አለው» እያሉ ሲቦተርፉን የነበሩ የሕወሐት ጀሌዎች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ዛሬ አቶ ጋዲሳን ምን ብለው እንደሚያስተባብሉ ግራ ገብቷቸው እየተንተባተቡ ይገኛሉ። ሕወሐት ገና ብዙ የጥፋት ድግስ ለትግራይ እየደገሰላት መሆኑን ማየት ያልቻለ የትግራይ ተወላጅ በጣም የዋህ እንደሆነ ነው የማስበው።
***
ለማንኛውም ፖለቲካውን በኋላ እንደተረዳነው እናስቀምጠዋለን፤ ላሁኑ ለሞቱት ነፍሳቸው እረፍትን ታገኝ ዘንድ ለቆሰሉትም የውሻ ቁስል ያድርግላቸው ዘንድ እንፀልያለን። ገዳዮቹ የእጃቸውን እንዲያገኙ ሁላችንም ተባብረን እንስራ!
Filed in: Amharic