>

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለአቶ በቀለ ገርባ የተፈቀደውን ዋስትና አገደ

(FBC)

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ችሎቱ የተፈቀደውን ዋስትና ያገደው የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቤቱታን ተከትሎ ሲሆን፥ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በማለት ነው።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግባኝ ሰሚ 1ኛ የወንጀል ችሎት ከትናንት በስቲያ አቶ በቀለ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ትእዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል።
በሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎት ይህ ውሳኔ የታገደ ሲሆን፥ አቶ በቀለ ገርባም መልስ እንዲሰጡ ታዘዋል።

Filed in: Amharic