>

የሰሞኑ መከላከያ ጄኔራሎች ስብሰባና የጥፋት ውሳኔ (ገረሱ ቱፋ)

“የሰሞኑ መከላከያ ጀነራሎች ስብሰባ የጥፋት ውሳኔ ሰሞኑን የህወሃት ጀነራሎች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ስብሰባው የወደ ፊት የሀገሪቱን ሁኔታ የሚወስን እንደሆነ በመታመኑ በከፍተኛ ሚስጥር የተከናወነ ቢሆንም ምንጮቻችን የተደረጉ ውይይቶችና ውሳኔዎችን አድርሰውናል፡፡ሰሞኑን በላይ በላይ እየተዳደረ በያለው ወቅታዊ የኦሮምያ ሁኔታና ሁኔታውን ኦህዴድ እየመራበት ያለውፍጥነት ያስደነገጣቸው ጀነራሎች መፈንቅለ መንግሰት ለማድረግ እያሰቡ ነው፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ዴኤታ መድህን(ሜ/ጀብርሃንነጋሽ)የኦህዴድ አመራር ከእጃችን አምልጧል፡፡ይህንን ደግሞ እያደረጉ ያሉት የቀድሞ የመከላከያ አባላት የነበሩት አባዱላ ገመዳና ከዚህ በፊትበመከላከያ ኮረኔልነት ደረጃ የደረሰው እንዲሁም የINSA መስራችና ዳይሬክተር የነበረው ዶ/ርአብይ አህመድ ናቸው ብለዋል፡፡ሁለቱም በውስጣችን ለረጅም ጊዜ አብረውን በመቆየታቸው አሰራራችን በሚገባ ያውቁታል፡፡

ሰሞኑን ሰላምና ልማትን ለማስጠበቅ የተከናወኑ ኦፕሬሽኖችም ያልተሳኩት በእነሱ ምክንያት ነው፡፡ወታደራዊ ስትራቴጅዎችን ጠንቅቀው ስለሚያውቁና የማክሸፊያ ስልት በመቀየሳቸው ኦፕሬሽኖች በሚፈለገው ደረጃ አልተሳኩም ብለዋል፡፡ በህዳሴው ግድብ የኤሌክትሮ እና የሃይድሮ ሜካኒካል ሥራው ወስዶ እየሰራ ያለው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን ስራዎችን በአግባቡ እየሰራ እንዳልሆነና ከሳሊኒ ጋር እየተግባባ እንደሆነ መረጃ ያላቸው የኢፌድሪ ጠ/ሚንስቴር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራውን አቋርጦ እንዲወጣ ማዘዛቸውን ተከትሎ በውሳኔው ደስተኛ ያልሆኑት የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀኔራል ክንፈ ዳኘው አዲሱ የኦህዴድ አመራር በጠ/ሚኒስትሩ ተቀባይነት እንዳለው በሚያሳብቅ አነጋገር የወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ የጠ/ሚኒስትሩ ፍቃድ ሳያስፈልገን ህገ መንግስቱ በሚፈቅድልን መሰረት ሰላምና መረጋጋት በመፍጠር በኦሮሚያ ያለውን አመራር አስረን በማስወገድ ከህዝቡ ጋር ውይይት በማድረግ በ6ወር ጊዜ ውስጥ ሁኔታውን ልናረጋጋ እንችላለን ብለዋል፡፡

ዋነኛው ቁጣቸው ደግሞ በበደሌያዩ ማዳበሪያ ፋብሪካ እንሰራለን ብለው ለ8ዓመታት የከሰል ድንጋይ አውጥተው ሲሸጡ የነበረ በመሆኑና አሁን የኦህዴድ አመራር ስላወቀባቸው ጭምር ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠ/ሚኒስቴር ሀይለማሪያም ደሳለኝ በወታደራዊና የደህንነት ሃላፊዎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነትና የመደመጥ ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ወቅታዊና ትክክለኛ የወታደራዊ እና ስለላ መረጃችን አይደርሳቸውም፤ሃለፊዎችንም ለምክከርና ወይይት ሲጠሯቸው አይመጡም፡፡ጠ/ሚኒስትሩም ፓርላማ ቀርበው የኦሮሚያ ኢትዮጵያ ሱማሌ ግጭት መነሻው የድንበር ሳይሆን የዶላርኮንትሮባንዲሰቶችና ጫት ነጋዴዎች ናቸው ብለው በአሽሙር የሰራዊቱንና የድህንነቱን ሃላፊዎች ስራ አውቄዋለሁ ለማለት የተናገሩት ሲሆን ይህን ንግግር የነበረውን ውጥረት የበለጠ አባብሶታል፡፡

ከዚህ በፊት በወታደሩ ዘንድ በኢትዮጵያ ፖለቲካና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች ሚዛናዊ አስተያየቶችን በመስጠት የሚታወቁትና በጀነራል ሳሙራ የኑስ ቡድን በጥርጣሬ የሚታዩት የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥሌ/ጀነራል ሳህረ መኮንን አጋጣሚውን በመጠቀም ለሳሙራ ታዛዥነታቸውን ለማሳየት በሁለቱ ጀነራሎች የቀረበውን ሀሳብ መደገፋቸው ግርምት ንፈጥሯል፡፡የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊው ጌታቸው አሰፋ ቀኝ እጅ የሆኑት ጀነራል ሳህረ በነጀነራል ሳሞራ ቡድን ብዙም ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በኮንትሮባንድ ንግድ የሚታወቁትና የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ፕረዘደንት አብዲ ኤሌ የጥቅም ሸሪክ የሆኑት ሌ/ጀነራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኩዋተር) ከደቡብ ምስራቅ እዝ የተነሱት በኮንትሮባንድ ንግድ በመሆኑ ይህንን ቂም ለመወጣት ከወታደራዊው መረጃ ሃላፊ ጀነራል ገብሬ ዴላ ጋር በማበር የኦሮሚያ ፕረዘደንት ለማ መገርሳና አብይ አህመድን ለመግደል ሲያሴሩ ነበረና አሁንም ቡድኑን ካላጠፋን በሚል ጠንካራ አቋም ሰንዝረዋል፡፡

Filed in: Amharic