>

ወላጁ ህወሃት አርጧል! አስወራጁ ኦህዴድ ወልዷል! (ስዩም ተሾመ)

በመሠረቱ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ “አርጧል” ከተባለ “መውለድ አቋሟል” ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት፣ አዲስ የፖለቲካ ሃይል፤ “Ideology” እና አመራር መፍጠር ተስኖታል፡፡ ነገር ግን፣ ኢህአዴግ በህወሃት መሪነት የተመሠረተ ግንባር ነው፡፡ ግንባሩ የሚመስለው መስራቹን ነው፡፡ ኢህአዴግ ያረጠው ወላጁ #ህወሃት/ኢህአዴግ ስላረጠ ነው፡፡ በተቃራኒው ኦህዴድ/ኢህአዴግ አላረጠም፡፡ በእርግጥ ኦህዴድ በተደጋጋሜ አርግዞ ሊወልድ ሲል አስወርዷል፡፡ ለምሳሌ፣ አልማዝ መኮ፣ ሀሰን አሊ፣ ጁነዲን ሰዶ፣… በመጨረሻ #አባዱላ_ገመዳ is Loading… ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታው ጃርሳው ልጅ ወልዶ እየሳመ ይመስላል፡፡ አሁን ዋናው ጥያቄ “ኦህዴድ ልጆቹን ያሳድጋል ወይ?” የሚለው ነው፡፡ አንዳንዶች “ጃርሳው ሥራውን የለቀቀው ልጆቹን ለማሳደግ ነው” ይላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ ኦህዴድ ልጅ ወልዷል! “የወለደውን ያሳድጋል ወይ?” የሚለውን አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ “የወለደ ከአረጠ በምን ይለያል?” የሚለውን ለመመለስ የህወሃትን ፊት ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ ያረጠው #ወላጁ_ህወሃት ስላረጠ ነው፡፡ እንደው በጥቅሉ “ኢህአዴግ አርጧል” ከማለት ይልቅ “ህወሃት አርጧል!” ብሎ በግልፅ መናገር ይበጃል፡፡ ከጭፍን ድጋፍና ተቃውሞ በአሻገር እውነቱን በግልፅ መናገር ለሁላችንም ይበጃል! ያረጠውም “ይመነኩሳል”፣ የወለደውም “ያሳድጋል”፣ ቤተሰቡ (ህዝብ) ሰላም ያገኛል!! መልካም ቀን!!
Filed in: Amharic