>

የትላንትና ዛሬን ቂም ከመቁጠር ባለፈ የነገ አሳስቧችሁ ያውቃል?? (ስዩም ተሾመ)

ባለፈው ፌስቡክ ላይ ለረጅም ግዜ የማውቀው፤ ቦርጩ እንደ እኔ ትልቅ፣ ጭንቅላቱ ደግሞ በጣም ትንሽ ከሆነ #የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊ ጋር በአካል ተገናኘን፡፡ ይሄ ሰው በህወህቶች ዘንድ አለ የተባለ፣ የመጠቀ ምሁራቸው ነው፡፡ ልክ እንደተገናኘን “ለምንድነው #በትግራይ ህዝብ ላይ ጥላቻ የምታንፀባርቀው?” አለኝ፡፡ አባባሉ በጣም ይገርማል፡፡ ኧረ እንደውም በጣም ያበሳጫል! “ስማ… እኔ ለጥላቻና ቂም የሚሆን ልብ የለኝም፡፡ ነገር ግን፣ በትግራይ ህዝብ ላይ የተጠራቀመው ቂምና ጥላቻ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፡፡ ከምንም በላይ እያሳሰበኝ ያለው እሱ ነው” አልኩት፡፡ “አይ… እሱን እንኳን ተወው!” አለኝና ስለ #ኦህዴድና_ብአዴን ፖለቲካ  ማውራት ጀመረ፡፡ በእርግጥ የሁለቱ ወገኖች መጠላለፍ ለህወሓቶች የህልውና መሠረት ነው፡፡ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ቂምና ቁርሾ መፍጠር የሚሹት ለዚህ ነው፡፡

ይህ ስልት ላለፉት 25 አመታት አኑሯቸዋል፡፡ ነገር ግን፣ አዲሱ የኦህዴድ አመራር ከመጣ በኋላ መላ-ቅጣቸው ጠፍቷል፡፡ በእርግጥ #በአብዲ_ኢሌ አማካኝነት ኦሮሚያን ለማተራመስ ሞከረዋል፡፡ ነገሩ አስቸጋሪ ሲሆንባቸው በኢሉ-አባቦራ በኦሮሞና አማራ መካከል ግጭት ለመፍጠርና የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ መከሩ፡፡ ነገር ግን እሱም አልተሳካም!! በአማራና ኦሮሞ ልዩነትና አለመግባባት ላይ የተመሠረተው የህወሓት ህልውና #በለማ_መገርሳ ኢትዮጲያዊነት ብትንትኑ ወጣ፡፡ ቀድሞ የብሔርተኝነት አጀንዳ አቀንቃኞች የነበሩት ወዳጆቼ ዛሬ የሚይዙትን፥ የሚጨብጡት አጡ፡፡ በኦሮሞና አማራ ህዝብ መካከል ስምምነት ሲፈጠር የህወሓት የፖለቲካ ስልትና አጀንዳ አፈር-ድሜ ይበላል፡፡ የሁለቱ ህዝቦችና ልሂቃን መዘላለፍና መጠላለፍ ሲቀር የህወሓት ሸርና አሻጥር ፈጦ ወጥቷል!! የህወሃት ፖለቲካ ሚስጥሩ ሲታወቅበት በሌሎች ላይ ያጠራቀመው ቂምና ጥላቻ ራሱን መብላት ይጀምራል፡፡ ሆኖም ግን፣ ህወሓት ለዘራው ቂምና ጥላቻ ዕዳ የሚከፍለው ምኑም ውስጥ የሌሉበት የትግራይ ወጣቶች መሆናቸው ያሳዝናል፡፡

እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር ባለፈው አመት በመቀለ ስታዲዮም በአማራ ክልል ደጋፊዎች ላይ የተፈፀመውን ግፍ ስናወግዘ #ዘረኞች ነበርን፡፡ ዛሬም በወልዲያ ከነማ የተፈፀመውን ግፍና በደል ስንናገር ዘረኞች ነበርን፡፡ የእናንተ የዘር ካንሰር እስኪለቃችሁ ድረሰ ስንት ዓመት ዘረኛ እንደምንባል አይገባኝም!! እስኪ “ዛሬ በወልዲያ የሆነው ባለፈው አመት በመቀለ ስታዲዮም በሰራንው ስህተት ነው!” የሚል አንድ ተጋሩ ወዳጅ ፈልጉልኝ፡፡ እስኪ “የአምና ስህተታችን ዘንድሮ መከራ አመጣብን” የሚል አንድ ሰው ከወደ መቀለ ጥሩልኝ? አምና በመቀለ፣ ዛሬ በወልዲያ፣ ነገ በየት፥ ምን ያመጣል?? የትላንትና ዛሬ ቂም ከመቁጠር ባለፈ የነገ አሳስቧችሁ ያውቃል?? ልቦና ይስጣችሁ አቦ!!

Filed in: Amharic