>

ወያኔ የጎንደርን አርሶ አደር ልታስጨፈጭፍ የሱዳንን ሰራዊት "ግባ!" ብላ ግሪን ካርድ አሳይታለች

                                                                         ቬሮኒካ መላኩ
በኢትዮጵያ የሺህ አመታት ታሪክ ውስጥ ሱዳን ኢትዮጵያን በጦርነት ያሸነፈቻት አንድ ጊዜ ብቻ ነው። በአፄ ዮሀንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት። በአፄ ዮሀንስ ዘመን ሱዳኖች ጦርነቱን አሸነፉ የንጉሱን ጭንቅላት ቆርጠው ወሰዱ። ከዚህ በፊትም ሆነ ከዚህ በኋላ ሱዳን ኢትዮጵያን አሸንፋ አታውቅም። 
ከዛ በፊት ሱዳኖች እንኳን ኢትዮጵያን ሊያሸንፉ ይቅርና በከባድና ዘመናዊ መሳሪያ ታጅቦ የመጣውን የግብፅና የሱዳን ጥምር ጦር ወጣቱና ገና “ሽፍታ ” የነበረው የቋራው አንበሳ ካሳ ሀይሉ (ቴዎድሮስ) ደባርቅ ላይ አፈርድሜ አብልቶ መልሶታል።
ዛሬ ኢሳት በዜናው ” ሱዳን በመተማ በኩል ኢትዮጵያን ወረረች ” የሚል ዜና ፅፎ አነበብኩኝ። እንኳን ይችን ተራ ኮንስፓይሬሲ ይቅርና ካለሰፈሯ የመጣች ትንኝ ለይተን እናውቃለን። ወያኔ የሱዳንን ሰራዊት “ግባ! ” ብላ ግሪን ካርድ አሳይታ የጎንደርን አርሶ አደር አጋፍጣ ልታስጨፈጭፍ። ሄሄሄ።
ሱዳን ዛሬ ድንገት ተነስታ ኢትዮጵያን የምትወርበት ሃባ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የላትም።
ወገኔ የሆንከው የጎንደር አማራ አርሶ አደር ሆይ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በታንክ የታጀበ የሱዳንን ዘመናዊ ሰራዊት በአጭር ምንሽርና በረጅም ምንሽር እየነፋህ ስታስፈረጥጠው እንደነበርክ እንከፉ ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝና ታሪክ ምስክር ነው። ለዚህ ጀግንነትህ ሜዳሊያ መሸለም ሲገባህ ፓርላማ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሽፍታ ” ተብለሀል።
አሁን ሱዳን ድንበርህን ጥሶ ቢገባም ” ይለፈኝ! ” ብለህ ይሄን አርቲፊሻልና ፌክ ወረራ ዝለለው።
Filed in: Amharic