>

በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ የተከፈተው ክስ መሰማት ተጀመረ። ልዩ - ዘገባ (በወንድወሰን ተክሉ)

በለንደን ክራውን ኮርት ችሎት አንደኛ ቀን ውሎ ልዩ-ዘገባ

በወንድወሰን ተክሉ
04-12-2017

በእንግሊዝ መንግስት አቃቤ ሕግ ከሳሽነት በአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር አባል በሆኑት በዶ/ር ታደሰ ብሩ ከርሰሞ ላይ የተከፈተው ክስ ዛሬ በምስራቅ ለንደን ባለው ክራውን ኮርት መጀመሩን የችሎቱን ውሎ የተከታተለው ባልደረባችን የዘገበ ሲሆን በችሎቱም ከለንደን፣ቢርሚንግሃም፣ማንቺስተርና እስኮትላንድ የተጋዙ ኢትዮጵያዊያን እንደተገኙ ገልጻል የሰኞ ታህሳስ 4ቀን 2017 በለንደን ክራውን ኮርት ችሎት ላይ በከሳሽ አቃቤ ህግና በተከሳሽ ዶ/ር ታደሰ ብሩ መካከል የተካሄደውን ክርክር የተከታተለው የባልደረባችን ዘገባ እንደሚከተለው ቀርባል።
**ዶ/ር ታደሰ ብሩ የተከሰሱበት ክስና ጉዳያቸውን የሚያየው የሸንጎ[ጁሪ]ምርጫ
በዶ/ር ታደሰ ብሩ ላይ የተከፈተው ክስ ይዘት የአሸባሪነት ክስ መሆኑ ቀደም ብሎ የተገለጸ ሲሆን ይህም በሁለት ሰክሾኖች[አንቀጾች]ሰክሾኖች 8እና ሰክሾኖች 78 መሰረት የተከፈተ ክስ እንደሆነ በችሎቱ ተነባል።

በከሳሽ አቃቤ ህግና በተከሳሽ ዶ/ር ታደሰ ብሩ መካከል ያለውን ክርክር በመሃል ዳኝነት የሚመሩት የክራውን ኮርት ዳኛ በመጀመሪያው ቀን ውሎዋቸው ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ በተከታታይ እስክ ዲሴምበር 21 2017 ድረስ ለሚፈጀው ክርክር ስራቸውን የሚጀምሩትን 16አባላትን ያቀፈ ሸንጎ[ጁሪ]መምረጣቸውን ዘግባል።

ዳኛው ለሾነጎነት ከቀረቡት 40እጩዎች መካከል 16ቱን ከመረጡ በሃላ ነገ [ማክሰኞ] ቃለ-መሃላ ፈጽመው ስራቸውን እንደሚጀምሩ የተነገራቸው ከ16ቱ ውስጥ 4ቱ ለመጠባበቂያነት እንደተመረጡና 12ቱ ግን እስከ ዲሴምበር 21 2017   እለታዊ የችሎት ውሎ ላይ እንደሚሳተፉ በመግለጽ ማብራሪያ እንደተደረገላቸው ዘጋቢያችን ገልጻል።
ችሎቱ በለንደን ሰዓት አቆጣጠር ከጣቱ 10፡00ሰዓት [4፡00ሰዓት]እንደተጀመረ የገለጸው ዘጋቢያችን እስከ እኩለ ቀን ያለውን ግዜ የፈጀው የዳኛው የችሎቱን ስርዓት ለተከሳሽና ለተሰበሰቡት የሸንጎ አባላት በማብራራት እንደሆነ ጠቅሶ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር በተለያየ መንገድ በስራ፣በቋንቋ፣በጋብቻና መሰል ሁኔታዎች ግንኙነትም ሆነ ንክኪነት ያላቸው እጩ ሸንጎዎች እራሳቸውን በመግለጽ እራሳቸውን እንዲለዩ ዳኛው ገልጸዋል ሲል አትታል።
ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ዺሴምበር 21 2017 ድረስ በሸንጎነት የሚያገለግሉትን አባላት መምረጡ ስራ እንደተጠናቀቀ የከሰዓት በሃላ ያለውን ግዜ በአቃቤ ህግ እና በተከሳሽ መካከል በክሱ ላይ በሚቀርቡት ማስረጃዎች ዙሪያ ለችሎቱ እንዲያስታውቁ ተደርጎ ክርክር ሲካሄድ ውላል ብላል።
በከሳሽ አቃቤ ሕግ በኩል ዶ/ር ታደሰ ብሩን በአሸባሪነት ለመክሰስ ካቀረባቸው ማስረጃዎች ውስጥ የኢሳት ታህሳስ 24ቀን 2017 እለታዊ የዜና ዘገባ አንዱ መሆኑን ጠቅሶ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በስዊዲን እስቶክሆልም ኮሚኒቲ ግብዥ ቪዲዮ፣ከዩ-ቲዩብና ማዶት.ኮም ከተባከ ድረ-ገጽ የተሰበሰቡ ዜናዎችና ፎቶዎችን ለማስረጃነት እንዳቀረበ ዘጋቢያችን ገልጻል።

የተከሳሹ ዶ/ር ታደሰ ብሩ ጠበቃም በአቃቤ ሕጉ በኩል በቀረቡት ማስረጃዎች ስነባህሪይ፣ተዓማኒነትና ባለቤትነት ነጥቦችን እያቀረበ መልስ ሰጥቶበታል።

ከአቃቤ ህግ አቀራረብ በመነሳት የክሱ ጭብጥ የሚያጠነጥነው ዶ/ሩ ፈጽመውታል የተባለን የሽብር ተግባራትን በማሳያት ሳይሆን በኢሳት እና አግ7 ውስጥ ያላቸውን ሚናን በመግለጽ ሁሉቱን ድርጅቶች እንደአሸባሪነት በማቅረብ እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
የአቃቤ ሕጉ-አቀራረብ ለፍርድ ቤቱ የአግ7ና ኢሳትን አሸባሪነትን በማሳመን ዶ/ሩን አሸባሪ ብሎ ለመክሰስ እንደፈለገ ከክሱ ጭብጥና አቀራረብ መረዳት ተችላል።
ሆኖም አቃቤ ህጉ በዳኛው በኩል የቀረበለትን “የአግ7 ድርጅት አሸባሪነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመዝግቦ ያለ ነው” ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ አጥጋቢ መልስ በማጣት “የለም ድርጅቱ በኢትዮጵያ መንግስት እንጂ በዓለም ደረጃ አሸባሪ ተብሎ የተመዘገበ አይደለም”ብሎ ለመመለስ ተገዳል ሲል ዘጋቢያችን ገልጻል።
ክርክሩ እስከ ታህሳስ 21ቀን ባለው ግዜ ውስጥ ካልተጠናቀቀ ለገና [ክሪስማስ]ክብረበዓል በማቃረጥ በመጪው አዲሱ ዓመት 2018 ጥር ወር እናጠናቅቃለን በማለት ዳኛው ያሳወቁ ሲሆን ነገ ከጠዋቱ 11፡00ሰዓት ላይ የተመረጡት ሸንጎ አባላት ቃለ-መሃላ አድርገው ክርክሩን መስማት ይጀምራሉ ሲል የእለት ውሎውን ዘግባል።

Filed in: Amharic