>
10:18 am - Friday October 22, 2021

አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዳይሆንብን (ሃራ አብዲ)

«ሁለት መልእክቶች ለሁለት አካላት» https://www.ethioreference.com/archives/9050 የሚለውን ጽሁፍ መለስ መለስ ብዬ አነበብኩት።በሀገራችን ላይ እየመጣ ያለዉን አደጋ ተገንዝበዉ እንደዚህ ለትግራይና ለሌላዉም ህዝብ በጎ ሃሳባቸውን የሚለግሱ የትግራይ ተወላጆች በብዛት ለማየት እኔም ሆንኩ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ ምኞታችን ነዉ።
በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተፈጠረዉ ሃሳብን በነጻነት የማንሸራሸር እንዲሁም ጠቃሚ ኢንፎርሜሽኖችን የመለዋወጥ ባህል መዳበር የተነሳ በህዝባችን ስነልቦና ዉስጥ ሊበረታታ የሚገባዉ መቀባበል ተፈጠሮአል። ይህን እምነት ተደግፌ የተጉዋደሉ ሃሳቦችን ጣልጣል ለማድረግ እሻለሁ።
በቅድምያ የጽሁፉን በጎ ምልከታዎች ከዚያም ጽሁፉ የዳሰሳቸዉን ጉዳዮችና በተጻራሪ ያሉ እውነቶችን
በመጠኑ እቃኛለሁ። እንደ ሌሎቹ ጽሁፎች ሁሉ ይሐኛዉም የህወሀትን ማንነት በግልጽ ያስቀመጠ በመሆኑና ለሀገራችንና ለህዝባችን ይበጃል ያላቸዉን ምክሮች የያዘ በመሆኑ ይበል ያሰኛል። ሀገራችን ኢትዮጵያ በህወሃት
የውስጥ ቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ ምክንያት ለዘመናት በህብረትና በመፈቃቀድ አብሮ በኖረዉ አንድ ህዝብ ምትክ በጎሳ በነገድና በቁዋንቁዋ በተከፋፈሉ ህዝቦች ተተክታለች። ይህ ለህዝባችን ኑሮ መሻሻል በነጻነትና በመተባበር ለማደግ ቢሆን ባልከፋ ነበር። ችግሩ መለያየቱ የተፈጠረዉ ህወሃት ስራዬ ብሎ ህዝብን ከህዝብ በማጋጨትና አንዱን ጎሳ ከሌላው ጋር በማዋጋት መሆኑ ነዉ ። ችግሩ እንደልቡ በመላዉ ሀገራችን የሚገኘዉን ንብረትና የተፈጥሮ ሃብት ለመዝረፍ እንዲያመቸዉ የጣለው መሰረት መሆኑ ነዉ። ይህ የአፓርታይድ ፖሊሲ አንድን አናሳ ጎሳ በስልጣን ላይ ለማቆየት ማንኛዉንም የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ ፤ የወታደራዊ፤ የደህንነት የሃገር ዉስጥና የዉጭ ግኑኝነት ጠቀልሎ ይዞ ህዝባችንን በመሳርያ ረግጦ መግዛት በራሱ ላይ ከባድ መዘዝ እያስከተለበት መጥቶአል። እንግዲህ ካለፈዉ አመትና ሁለት አመታት ቀደም ሲል በመላዉ ኢትዮጵያ እንደ እንጉዳይ ከዚህም ከዚያም መፍላት የጀመረዉ እምቢ አልገዛም ባይነት ምክንያት አልቦ አይደለም።
አሳዛኙ ነገር ደግሞ ይህ አልገዛም ባይነት መገለጫዎቹ የግድ የሚያርፉባቸዉ ስፍራዎች መኖራቸዉ ነዉ። ስፍራዎቹ የህወሃትን አገዛዝ መሰረት መናድ፣ ህወሃት መነሻና መድረሻዬ ነዉ የሚለዉ የአፓርታይዱን አገዛዝ ለመቃወም ያልፈለገዉ/ያልደፈረዉ በሃገር ዉስጥና በዉጭ ሃገር የሚኖረዉ የትግራይ ተወላጅ፣ትውልደ ትግራይ፣ የነሱ የሆነዉና ቀደም ሲል የነሱ ያልነበረዉ ሃብትና ንብረት ናቸዉ። እንግዲህ ወደተነሳሁበት ጽሁፍ ስመለስ የትግራይን ህዝብ በተመለከተ፤

የመረጃ እጦት፤

እዉነታዉን በግልጽ ለማየት አለመፈለግና አንዳንድ የትግራይ አክቲቪስቶች የሚያቀርቡትን እሳቤ በመያዝ በህልዉናዉ ላይ እየመጣ ያለዉን አደጋ በዉል እንዳይረዳዉ እንዳደረገዉ ያደረበትን ስጋት ጽሁፉ ይጠቁማል። አኝከህ አኝከህ ወደ ዘመድህ ዋጥ በሚለዉ የሀገራችን ብሂል መሰረት ለትግራይ ህዝብ ዝምታ መጠነኛ ሽፋን መሰጠት ሊኖር ይችላል ብዬ ላልፈዉ እችል ነበር። ሆኖም ወቅቱ አለባብሰን የምናርስበት ወቅት አይደለም። በመሬት ላይ ካለዉ እዉነታ ጋር መጋፈጥ ግድ ስለሚል በዚህ አቀራረብ ላይ የጎደለዉን መሙላት ይገባል።
አብዛኛዉ የትግራይ ህዝብ እንደሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የህወሃት ብልሹ አገዛዝ ሰለባ መሆኑ አጠያያቂ  አይደለም። ሆኖም ያን ያህል የመረጃ እጦት አለበት የሚያስብል አይደለም።በተቻለዉ መጠን ለነጻ  ሚዲያ ኢንፎርማሽን ተጋልጦ የህወሃትን ክንቱ ፕሮፓጋንዳ ቸል እንዳይል ቁጥጥር በህዝቡ ላይ ሊደረግ ይችላል። እኛ ከሌለን አንተም አትኖርም ስለዚህ ከህወሃት አላማ ዉጭ ሌላ እንዳያምርህ ተበሎ የፖለቲካ ስራ ሊሰራበት ይችላል። ይህ ምክንያት ብቻዉን ህወሃት ካመጣዉ መዘዝ አያስመልጥም። ወዲያዉም፤ የትግራይ ህዝብ መረጃ እንደሚደርሰዉ ጠቁዋሚ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ በወለጋ ስለተገደሉት ሶስት የትግራይ ተወላጆች በቂ መረጃ ነበረዉ። ይህም በትግራይ ተወላጆች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሶ ሰላማዊ ሰልፍ እስከ መዉጣት( ምንም እንኩዋን በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦች ቢታደሙበትም) አድርሶአል። የትግራይና የአማራ ህዝብ መድረክ በተባለዉ የይስሙላ ስብሰባ ላይ ንግግር ካደረገችዉ ወይዘሮ አባባል መረዳትም እንደሚቻለዉ የትግራይ ህዝብ ጥሩ የመረጃ ፍሰት እንዳለዉ ነዉ። ሆኖም ኢሳትና ታማኝን በሚገባ ለሚከታተል ህዝብ ህወሃት በህዝባችን ላይ
ያደረሰዉንና በማድረስ ላይ ያለዉን አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንዲሁም ህዝቡ ይህን ከማርጀት አልፎ ያረጠ
ስርአት አሽቀንጥሮ ለመጣል የሚከፍለዉን መስዋእትነት ሳይገነዘብ ይቀራል ማለት አዉቆ የተኛን
ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ ይሆናል።
አስገራሚዉ እዉነታ ግን እነዚያ በወለጋ የተገደሉት የትግራይ ተወላጆች ፈንጂ ይዘዉ ህዝብ ላይ ጥቃት
ለማድረስ( ምናልባትም ኦነግ ላይ አበሳቸዉን ለመጠፍጠፍ) ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸዉ የትግራይ
ተወላጆችን በዘር ላይ ያነጣጠረ ግድያ ይቁም ከማለት እንዲቆጠቡ አለማድረጉ ነዉ። ባለፈዉ አመት በባህር ዳር ይመስለኛል ከቃጠሎ የተረፉ ሱቆችን ለማቃጠል ከትግራይ ክልል ተልከዉ ቤንዚንና ክብሪት ይዘዉ በጥቆማ የተያዙትን የትግራይ ተወላጆች ይህ ነገር አያቀባብርም ጥፋት ነዉ ብሎ የትግራይ ህዝብ ትንፋሽ አላሰማም። በመቱ ከተማ የኦሮሞን ህዝብ ጥላሸት ለመቀባት በንግድ ስራዉ ሽፋን የህወሃትን የስለላ ስራ ሲሰራ የጦር መሳሪያ ፈንጂና የኦነግ ባንዲራ ከቤቱ የተገኘበት የትግራይ ተወላጅ ዜና ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ የዜና ሽፋን ተሰጠቶታል። የትግራይ ህዝብ ይህን አልሰማሁም ይል አይመስለኝም።
በየ እስር ቤቱ የሚገረፉት፣ የሚቀጠቀጡት፣ ከሚነድ እሳት ህይወታቸዉን ለመታደግ ሲሮጡ በጥይት እየተቆሉ የረገፉት፣ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞአቸዉን ለማሰማት ሲወጡ በአጋዚ አረመኔና ቅልብ ጦር በጥይት የተረሸኑት ፣በእስር ቤት የሚኮላሹትና ተቀጥቅጠዉ የሚገደሉት እንደ አርማዬ ዋቄ አይነት ወጣት ዜጎች የሃዘን ዜና ሚዲያዉን ያጥለቀለቀ ሲሆን ከአለም ሁሉ ተለይቶ ይህ ዜና ከትግራይ ህዝብ ጆሮ የማይገባበት ምክንያት አይኖርም።

Again, የትግራይ ህዝብ እየመረጠ ይሰማል ካልተባለ በቀር ይህ ሁሉ በምድራችን ላይ እየተፈጸመ
ህወሃትን ለመቃወም የሚያበቃ የመረጃ ድርቅ መትቶታል ማለት አይቻልም። ከፍተኛ አደጋ እየመጣበት
እንደሆነ አልተገነዘበም ማለትም እርባና የሌለዉ መከራከሪያ ነዉ።

እንደ ጽሁፉ ሃሳብ እዉነታዉን በግልጽ ለማየት አለመፈለግ ካለና አንዳንድ የትግራይ አክቲቪስቶች የሚሉትን ግንዛቤ መዉሰድ ይጠቅመኛል ብሎ የተጋረጠበትን አደጋ ቸል ካለም ምርጫዉ የትግራይ ህዝብ ነዉ። በዚህ ጉዳይ ላይ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ጭምር በግልጽ ማስጠንቀቅ በመጀመራቸዉ መልካሙን እመኛለሁ።
በማገባደጃዉ ማንሳት የምፈልገዉ ጉዳይ መነሻ የሆነኝ ጽሁፍ የሚያነሳዉ ኢንተረስቲንግ ነገር ነዉ። ሃብታም ስለሆኑና ድሃ ስለሆኑ የትግራይ ተወላጆች ያነሳና በዚህም ምክንያት የጥቃቱ ኢላማ እንደሆኑ ይገልጻል። መጀመርታ ነገር ሁሉም የትግራይ ህዝብ የኢኮኖሚዉ ተጠቃሚ ነዉ የሚል መደምደሚያ የለም። ሊኖርም አይችልም። ሆኖም በክፍሉ ዉስጥ ያለዉን ዝሆን (ኤፈርትን) ለሌላ ጊዜ እናቆየዉና በዘመነ ህወሀት እንደ አሸን ከፈሉት አዳዲስ የትግራይ ዲታዎች መካከል አቶ ዳዊት ገብረእግዚአብሄርን የመሳሰሉትን ዋቢ ማድረግ  ይቻላል። ከኢትዮጵያ ሶስተኛ ሃብታም የሚባለዉ አቶ ዳዊት እህቱ ወይዘሮ ፈትለወርቅ የህወሃት ምክትል ሊቀመንበር ሆና መሾምዋ የሚያመለክተዉ ህወሃት በፖለቲካ የበላይነትን ለማስጠበቅ የኢኮኖሚዉን የበላይነትም ማስጠበቅ ያስፈልጋል በሚለዉ መርሁ መሰረት ቅድሞ የነበሩትን የሌላ ማህበረሰብ ተወላጅ ባለሀብቶች በኢኮኖሚ ተጽእኖ ከገበያ በማዉጣት በምትካቸዉ የትግራይን ተወላጆች ባለሃብት እንዲሆኑ አድሎአዊ ድጋፍ ሰጥቶአቸዋል።

ለምለም ከሆኑት የሀገራችን ክፍሎች የሚገኘዉን ማንኛዉንም የተፈጥሮ ሃብት፣ የኦሮምያን ለም አፈር ሳይቀር ወደትግራይ እንዲያግዙ ከሚቀጠሩት ሹፌሮችና ደላሎች እስከ ቡና አስመጭና ላኪ፣ ከወርቅ ማእድን ለቤትነት ቁፋሮዉን እስከሚያከናዉኑት የጉልበት ሰራተኞች፣ የደን ሃብትን ከተቆጣጠሩት እስከ ደን ጨፍጫፊዎች መንገድ ተቁዋራጮች ያለጨረታ አቅርቦቱን እንዲፈጽሙ እስከሚሰጣቸዉ ባለኮንትራቶች፣ በአየር መንገድ ከትላልቅ ካፌ ባለቤትነት እስከ ሻንጣ ገፊነት፣ ከኮንዶ ባለቤትነት እስከ ታላላቅ ህንጻ ባለቤትነት ድረስ ወዘተ– የትግራይ ተወላጆች ተጠቅጥቀዉበታል። ስለዚህ ሃብታም ክሆኑ ዘርፈዉ ነው ይባላል የተባለዉን በሌላ አገላለጽ ማየት ይቻላል።

ከምንም ተነስተዉ እንደሌላዉ ኢትዮጵያዊ ለፍተዉ ጥረዉ ግረዉ ያመጡት ሃብት አይደለም። ከትግራይ ህዝብ ዉጭ ሰርቶና ነግዶ ሌላዉ የማህበረሰብ ክፍል ባለሃብት እንዲሆን ህወሃት አይፈልግም። ሕወሃት ከፍጥረቱ ጀምሮ ትግራይ ድሃ የሆነችዉ ጨቁዋኝዋ አማራ ጨቁናት ነዉ በሚሉ ገና ከናታቸዉ አንቀልባ ሳይወርዱ በቅናት ሲለበለቡ ባደጉ ድሃ ትግሬዎች ነዉ የተመሰረተዉ። ምንም እንኩዋን አፍሪካ ድሃ አህጉር፣ ኢትዮጵያ ድሃ ሃገር ብትባልም ከኢትዮጵያ ዉስጥ ደግሞ በመሬቱ ደረቅ መሆንና በተደጋጋሚ በድርቅ መመታት የተነሳ ትግራይ በተፈጥሮ በልማት ያልታደለ ነበር። በዚህም የተነሳ የትግራይ ህዝብ በአንጻራዊነት ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ይበልጥ በደህነት የተመታ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነዉ። አሁን ታሪክ እየተቀየረ ነዉ። እድሜ ለኦሮምያ። በቀን መቶ መኪና ሙሉ ድልቢ አፈር ያለምንም ክፍያ ከኦሮምያ እየተጫነ ትግራይ ለምታ በልምላሜ ወርቅ እስከመሸለም በቅታለች።

በማጠቃለያ የማነሳዉ ጉዳይ ትንሽ ያሳዘነኝ ጉዳይ ነዉ። ይህ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የሚለዉ የትግራይ
ተወላጆች አባባል ከየት የመጣ ነዉ? ከመቸ ጀምሮ ነዉ ህዝባችን ከመካከሉ አንዱን ማህበረሰብ ነጥሎ ጠላቴ ነዉ ማለት የጀመረዉ? ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ድረስ ህዝባችን ሲዋደድ፣ ሰጋባ፤ ሲዋለድ፤ አብሮ ሲበላና ሲጠጣ አይደለም የኖረዉ?

ሕወሃት ምስጋና ይጣና በዚህ የአፓርታይድ አገዛዙ ምክንያት የትግራይ ህዝብ የተቀረዉ የኢትዮጵያ
ህዝብ በጠላትነት ያየኛል ብሎ እንዲያምን ብሬን ዋሽ ተደርጎአል። ይበልጥ የሚያሳዝነዉ ደግሞ የህወሃትን አስቀያሚ ፖለቲካ የሚቃወሙ አንዳንድ የትግራይ ተወላጆች ሳይቀሩ የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የሚያቀነባብሩት ፕሮፓጋንዳ የትግራይ ህዝብ እንዲጠላ አድረጎታል ሲሉ ይደመጣሉ። ይህ ስህተት ነዉ።

የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት አለዉ ከተባለም ከህወሃት ዉጭ ሊሆን አይችልም። ህወሃት ታሪክ አዋቂ ጎምቱ ጎምቱ አዛዉንትን ጭፍጭፎ የቀደመ ታሪክ ለልጅ ልጆቻቸዉ እንዳያወርሱ በአማራዉና በትግራይ መካከል ስለነበረዉ ድንበር ምስክር እንዳይሆኑ አድርጎአል። በጸናዉ የክርስትና እምነታቸዉ የጸና ትዉልድ እንዳይፈጥሩ መነኮሳቱን ሳይቀር በማጥፋት ገዳማት በመመዝበር ለአሁኑ እምነት የለሽ መረን አስተሳሰብ በህወሃትና ተከታዮቻቸዉ ዉስጥ መስፈን ህወሃት ተጠያቂ ነዉ።የትግራይ ህዝብም ጠላት ነዉ።

ከዚህ ሌላ በትግራይ ህዝብ ላይ ሂሳብ የሚያወራርድም ሆነ የሚወራረድ ሂሳብ ያለ አይመስልም። አለባብሰዉ ቢያርሱ ባረም ይመለሱ እንዲሉ ለትግራይ ህዝብ ዝምታ ሺህ ምክንያት መደረደር ከጥፋት አያስመልጥም። የግፉ ጽዋ ሞልቶ እየፈሰሰ ባለበት ባሁኑ ወቅት ፈጥኖ ሰልፍ ማስታካከል ያለበት በዋነኝነት የትግራይ ህዝብ ነዉ። ምን አልባት ህወሃት ባጋዛዙ ይቀጥላል እኛም ከጊዜ ሁዋላ ያፈራነዉ ሃብት አይጎድልብንም ብሎ የሚያስብ ካለ ጥብብ ይጎድለዋል። የተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጀቱ ሰደብን ሲገረፍ፤ ሲገደል፤ ከእርስቱ እየተነቀለ በትግራይ ተወላጆች ፊት መሳለቂያ መሆኑ እያበቃለት ነዉ።

Filed in: Amharic