>
10:47 pm - Wednesday February 1, 2023

ጨፍጫፊዎችን አስቀምጦ ተጨፍጫፊውን ሕዝብ የሚያወግዝ ባንዳ እንጅ የሃይማኖት አባት አይደለም!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

በነዚህ ሦስት ቀናት (ለነገሩ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ አድርጎታል) ትግሮች በተለያዩ ቦታዎችና የትምህርት ተቋማት የፈጸሟቸውን ግድያዎች በመቃወም በተለያዩ ስፍራዎች ተማሪዎች (በዚህ አጋጣሚ ጉዳዩ የተማሪዎች ብቻ ባለመሆኑ ሁላችንም ፈጥነን ተማሪዎችን መቀላቀል እንዳለብን ማሳሰብ እወዳለሁ) ተማሪዎች ተቃውሟቸውን በሚያሰሙበት፣ ተገቢ የሆነ የአጸፋ ምላሽ ለመስጠት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ወያኔ የሃይማኖት አባቶች ተብየዎችን እያስመጣ ተማሪዎችን በማስወገዝ ተማሪዎች አርፈው እንዲቀመጡ፣ ሲገሏቸው እንደ መሥዋዕት በግ በዝምታ እንዲገደሉ፣ ሲዘልፏቸው፣ ሲያዋርዷቸው፣ ሲያበሻቅጧቸው ያለ አንዳች ቅያሜና ተቃውሞ ስድባቸውን እንዲሸከሙ፣ ውርደታቸውን ያለማቅማማት እንዲታቀፉ፣ አንጀታቸው እያረረ፣ ልባቸው እየደማ ሐዘናቸውን፣ ግፍ በደላቸውን ዋጥ አድርገው እንዲቀመጡ እየተጫኗቸው እያስገደዷቸው ይገኛሉ፡፡ “የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” ይሉሀል ይሄ ነው፡፡ ትንቢት የተነገረባቸው በረከሰ ግብራቸውና በአደራ በላነታቸው መጽሐፍ እንደ ቁራ የጠቆሩ የሚላቸው የስምንተኛው ሽህ ካህናት ይሉሀል እነኝህ ናቸው፡፡

ቀኖና ቤተክርስቲያን እንደሚያዘው፣ ከቤተክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው፣ ከአበው ሐዋርያት፣ ከጻድቃን ሠማዕታት፣ ከሊቃውንት ካህናት ሕይወትና ገድላት የምናውቀውና አድርገውትም ያየነው በዳዮችን፣ ደም አፍሳሾችን፣ ግፈኞችን፣ አረመኔዎችን ገዥዎች አውግዘው ከሕዝብ ወይም ግፍ ከሚፈጸምባቸው ጎን ቆመው መከራ በመቀበል ለሠማዕትነት ሲበቁ፣ አክሊል ሲቀዳጁና ክብርን ከአምላካቸው ሲያገኙ እንጅ የደም ተጭዎች ተባባሪ ሆነው ደም ተጭዎችን “አትንኩ!” የሚሉ፣ በደም ጠጭዎች ላይ “አትነሡ!” ብለው ሕዝብን ወይም ግፍ የሚፈጸምባቸውን ያወገዙ አባቶች በቤተክርስቲያን ታሪክ ታይቶና ተሰምቶም አይታወቅም፡፡

እንዲህ ዓይነቱን የገዳዮች፣ የአረመኔዎች ተባባሪና አገልጋይ ቤተክርስቲያን ጨርሶ አታውቀውም፡፡ እግዚአብሔርም ፈጽሞ አያውቀውም፡፡ ለጥቅም ብሎ አምላክ የጣለበትን አደራ ከድቶ፣ በቅዱስ ቃሉ ላይ ሸፍጦ በካህናት ስም ከወንበዴዎች ጋር በመተባበር፣ አረመኔዎችን በማገልገል በእረኝነት፣ በአባትነት ላይ ውንብድናና ክህደት ፈጽሟልና እንዲህ ዓይነቱ ካህን ነኝ ባይ የወያኔ ካድሬ (ወስዋሽ) ከእግዚአብሔር ዘንድ የገሃነም ፍርድ ይጠብቀዋል፡፡

እነኝህ አባቶች፣ እረኞች፣ ካህናት ነን ባይ ምንደኞች ቅንጣት ታክል እንኳ የቤተክርስቲያንና የመንጋው ነገር፣ የአምላክ አደራ የሚሰማቸው፣ የሚገዳቸው፣ የሚቆጫቸው፣ የሚያሳስባቸው ቢሆን ኖሮ “…. የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርጌ ሠብሬያለሁ!” ብሎ እንደደነፋ ለሚያውቁት የአረመኔ አገዛዝ፣ ቤተክርስቲያንን በጊሪደር (በደርማሽ) ተሽከርካሪ አፈራርሶ ንዋዬ ቅድሳትን የትም የሚወረውር ሲበዛ ግፈኛ አላዊና አረመኔ አገዛዝ እንደሆነ ለሚያውቁት አገዛዝ የማገልገል ፍላጎትም ሆነ ዝንባኔ ጨርሶ አይኖራቸውም ነበረ፡፡ እነሱ ግን የሥጋቸው እንጅ የነፍሳቸው ጉዳይ ጨርሶ የማያሳስባቸው ሆድ አምላኪዎች በመሆናቸው በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ ስንት ጥፋት እንዳደረሰና ሊያጠፋትም እየጣረ ያለ አረማዊ አገዛዝ እንደሆነ እያወቁ ጥቂት እንኳ ሳይሰቀጥጣቸውና ሳያሸማቅቃቸው በትጋት እያገለገሉት ይገኛሉ፡፡

እጅግ የሚገርመኝ ነገር ቢኖር እነኝህ ምንደኛ ካህናት ከሕግ ውጭ ሆነው፣ የአምላካቸውን አደራ በልተው ለእንዲህ ዓይነቱን ፀረ ቤተክርስቲያንና አረመኔ አገዛዝ ያደሩ ሆነው እያለ የእግዚአብሔርን ስም እየጠሩ ለማውገዝና ለመገዘት መድፈራቸው ነው፡፡ ለነገሩ እግዚአብሔርን መፍራቱና ለእሱም መታመኑ የላቸውምና ይሄንን አይደለም ለወያኔ ተሰልፈው መሣሪያ መዘው ነፍስ ቢያጠፉ እንኳ የሚገርም አይሆንም፡፡ በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ! የእንዲህ ዓይነቱ ምንደኛ፣ ከሀዲ፣ እርኩስ ካህን ነኝ ወይም አባት ነኝ ባይ ምንደኛ ካድሬ ውግዘት ከቶውንም አይሠራምና ውግዘቱን አትፍራ፡፡ ይልቁንም ግፍና መከራ እያደረሰብህ ያለው የግፈኛው የአረመኔው የወያኔ የጥፋት ኃይል አንዱ ነውና እሱንም አትማረው!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 
amsalugkidan@gmail.com

Filed in: Amharic