>
4:34 pm - Wednesday October 16, 8480

ወቅታዊ ጥሪ ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትና ጸጥታ አስከባሪ ሃይሎች (ሃራ አብዲ)

’’ሰዉየዉ ኢትዮጵያን በስም እንኩዋን አያዉቃትም,,, ኢትዮጵያ የምትባለዉ ፍጡር ትግራይ
የሚባል ሀገር ዉስጥ እንዳለች ተገንዝቦአል,,,ትግራይ ሀገር፤ ኢትዮጵያ ክፍለሀገር,,,ያሳዝናል’’
( የመለስ ልቃቂት ገጽ 78 ኤርምያስ ለገሰ)

ለመላዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለመላዉ የኢትዮጵያ የፌደራል ፖሊስ ስራዊት ለመላዉ የሀገር ደህንነትና ጥበቃ አባላት ለመላዉ የክልሎች ልዩ ፖሊስ አባላት በማንኛዉም የሀገራችን መለዮ ለባሽ የእዝ ሰንሰለት ለምታገለግሉ የሀገርና የወገን አለኝታ የቀረበ አስቸኩዋይ ጥሪ።
ህወሃት ገና እግሩ ቤተመንግስት ሲረግጥ የፈጸመዉ ቁጥር አንድ ወንጀል ከአፍሪካ አንደኛ የነበረዉን የሀገር ዋልታ መለዮ ለባሽ በትኖ ሜዳ ላይ መጣል ነበር። አሁንም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ መኮንኖችን ከላይ ሆነዉ ሰራዊቱን እንዲቆጣጠሩ እየመደበ ፤ የሌላ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑት በተለይ የአማራና የኦሮሞ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በቀጥታ ከሚያዙት ሰራዊት ጋር እንዳይገናኙ ለሙያቸዉ በማይመጥን ሁኔታ ከእዝ መስመር እያወጣቸዉ ይገኛል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የዜግነት መንፈስ በዉስጣቸዉ በሌለባቸዉ ይልቁንም ትግራይ ራስዋን የቻለች ሀገር ይመስል ትግራይና ኢትዮጵያ እኩል ናቸዉ በሚሉ ከሃዲና ዘረኛ የትግራይ ተወላጆች የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ወድቃለች። ላለፉት ሃያ ስድስት አመታት ሀገራችንን በብረት ክንድ ረግጦ በመግዛት ላይ ያለዉ ህወሃት  ሀገራችንና በህዝባችን ላይ ይህ ነዉ የማይባል ሰቆቃ የፈጸመዉና በመፈጸምም ላይ ያለዉ ኢትዮጵያን እንደ  ሀገሩ፣ ህዝቡዋን እንደ ወገኑ ስለማያይ ነዉ። ህወሃት የተመሰረተበት አላማም በግልጽ በማኒፌስቶዉ ላይ  እንደሰፈረዉ የትግራይን ህዝብ ሲጨቁን የኖረዉ የአማራ ብሄር ነዉ በማለት አማራዉንና የአማራዉ ሃይማኖት ነዉ የሚለዉን የኦርቶዶክስ ክርስትና ለማጥፋት ነዉ። ከዚያም ቢሳካለት ትግራይን በሃይል በመገንጠል ከኤርትራ ጋር በማደባለቅ የትግራይ ትግርኝን መንግስት በመመስረት በደስታና በተድላ ለመኖር ነበር። ይህ እዉነታ ቀደም ሲል ህወሃትን ያገለገሉና በትጥቅ ትግሉም ሆነ ከዚያ በሁዋላ ህወሃትን አሳምረዉ የሚያዉቁት እነ አቶ አብርሃም ያየህ፣ እነ አቶ ገበረመድህን አርአያ ና ሌሎችም ለእዉነት የቆሙ የትግራይ ተወላጆች በጥልቀት ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነዉ።

ትግራይን ከኤርትራ ጋር አዋህዶ ትግራይ ትግርኝን መመስረት የቀንና የለሊት ሃሳባቸዉ ቢሆንም ሊሳካላቸዉ አልቻለም። ምንም እንኩዋን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኤርትራ ጋር ለመታረቅ አማላጅ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም ከንቱ ምኞታቸዉ ለወደፊትም አይሳካም። ይህ ማለት ግን ትግራይን ገንጥለዉ የትግራይ መንግስት ለመመስረት በትጋት እየሰሩ አይደለም ማለት አይደለም።ለዚህም አስረጂ ሆኖ ሊቀርብ የሚገባዉ ህወሀት ከአንድ ወር በላይ በመቐሌና በአዲስ አበባ እየተመላለሰ በዝግ በተሰበሰበበት ወቅት ትግራይ ብትገነጠል ምን ይመስላችሁዋል? በማለት ከትግራይ ህዝብ የድጋፍ ሃሳብ ለማሰባሰብ ጥረት እንዳደረጉ መታወቁ ነዉ።
ህወሃት በቀጥር አናሳ ከሆነ ብሄረሰብ የተፈጠረ የአንድ ብሄረሰብ ነጻ አዉጭ ቡድን በመሆኑ ህልዉናዉን  ስጠብቆ ሀገራችንን በዉስጥ ቅኝ ግዛት ለመግዛት የሚችለዉ ከትግራይ ህዝብ በስተቀር ሌላዉ ኢትዮጵያዊ በሙሉ እርስ በርሱ እየተገፋፋ፣በድንበር ስም አለያም የሀሰት ታሪክ በመፍጠር የአንዱ ማህበረሰብ አያት ቅድመ አያት፣ የሌላዉን አያት ቅድመ አያት ሲጨቁን የኖረ በማሰመሰል አሁን ያለዉ ትዉልድ እንዲተላለቅ በማድረግ ነዉ። ህወሃት መሰሪ ተንኮሉን ወደሌላዉም የሀገራችን ክፍል በማዛመት ህዝብ ከህዝብ እያጋጨ ከፍ ሲልም የራሱን የስለላ መረብና ደህንነት በጠብ አጫሪነት ካሰማራና ፍጅት ካካሄደ በሁዋላ አስታራቂ መስሎ በመታየት አሁን ሀገራችንና ህዝባችን ያሉበት አስፈሪ ደረጃ ላይ ደርሰናል።
ባጠቃላይ የህዝባችን በጎሳ ስም፣ በድንበር ስም፣ ጥንት ተፈጽሞብናል በሚባል በደል ስም እርስ በርሱ  እንዲገዳደል ሲደረግ፣ ትግራይ ብቻ ሰላም አግኝታ በልማት ትገሰግሳለች። ህወሃት ይህን ሁሉ ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋና ዘር ማጥፋት የሚያከናዉነዉ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዉስጡ ስለሌለ ነዉ። ህወሃት ሃገሬ ነዉ የሚለዉ ትግራይን ብቻ ሲሆን፤ ህዝቤ ነዉ የሚለዉ ደግሞ የትግራይን ህዝብ ብቻ ነዉ። የሀገር መከታ የሆንከዉ ኢትዮጵያዊ መለዮ ለባሽና ጸጥታ አስከባሪ በሙሉ ከእንግዲህ የህወሃት የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ መሳሪያ ከመሆን ታቅበህ ህዝብህንና ሀገርህን ከሀገር በቀል የቅኝ አገዛዝ ስርአት እንድትታደግ አሰቸኩዋይ ጥሪ ቀርቦልሃል።
ሰሞኑን የመከላከያ ሰራዊት ወደ ኦሮምያ ዘልቆ በመግባት በጨለንቆ እልቂት በመፈጸሙና ይህም የክልሉ መስተዳድር ሳያዉቀዉ የተደረገ መሆኑን በመግለጽ የኦሮምያ መስተዳድር ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ መከላከያዉ ከህዝቡ ጎን እንዲቆም በይፋ ጥሪ ማስተላለፋቸዉ ይታወሳል። ንጋትና ጥራት እያደር እንዲሉ ሰራዊቱ በተለይም የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ መለዮ ለባሽ በህዝብህ ላይ ባለመተኮስ ለዚህ ታላቅ ጥሪ ምላሽ መስጠት ይጠበቅብሃል። ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ ወደሁዋላ የለም!!
ከእንግዲህ በሰላማዊ መንገድ መብቱን በሚጠይቀዉ ህዝብህ ላይ በመተኮስ የሀገር አደራ እንዳታጠፋ  ምከርበት። ካለዚያ የትግራይ ጄነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች ተጠያቂነት በሚመጣባቸዉ ጊዜ አሳልፈዉ
የሚሰጡት አንተን በእነሱ ትእዛዝ ተኩሰህ የምትገድለዉን መሆኑን አትርሳ። ከህዝብህ ጎን ብትቆም ግን የሀገርህ ባለዉለታ ሆነህ ክብር ትጎናጸፋለህ እንጂ በጭራሽ ህወሃት እንዳደረገዉ ሜዳ ላይ የሚጥልህ መንግስት በሀገርህ ላይ አይሰለጥንም።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያንና ህዝባችንን ይባርክ።

Filed in: Amharic