>
5:30 pm - Wednesday November 1, 1415

ሽለላ እና ቀረርቶውን ቀነስ !! (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

“ወጥ በወጥ ሆናችኃል” ዳንዔል ብረሃን
“ስብሰባው ላይ የፀፀት እምባ እያነቡ ነው።” ፍፁም ብረሃኔ
“ፈስ በፈስ ሆናችኃል።” ዘፀዓት
“በስሌቱ መሰረት እናሸንፋለን።በሌኒንዝም ደግሞ ተሸናፍ ቀለል ስል purging ከበድ ካለም eliminate ይደረጋል።”
ተስፋኪሮስ

እነዚህ በfacebook ላይ ጉምቱ የህዋሃት ደጋፍዎች ትላንትና ያንፀባረቁት ሃሳብ ነው።
የሃሳቡ ተመሳሳይነት የሃሳቡ ምንጭ ከተመሳሳይ ማዕከል የተቀዳ መሆኑን ያሳያል።
እኔን ያልገባኝ ነገር ፦
እየተደረገ ያለው ጦርነት ሳይሆን የኢህአዲግ አባል ፓርቲዎች ግምገማ እና ስብሰባ ነው።እናም ይህ ሁሉ ቀረርቶ ለምን አስፈለገ ? 
በእርግጥ ህወሃት በውይይት ላይ ካራ እንደሚመዝ ገና በመመስረቻው ላይ የትግራይ ሙሁራን እና ወጣቶች የመሰረቱትን ማህበረ ገስግስታት ( ስሙን ከተሳሳትኩ ይቅርታ።) ለድርድር ከጠራ በኃላ በድርድሩ ላይ የተገኙትን በሙሉ በአንድ ሌሊት አርዶ እንደጨረሰ የትግራይ ክልል ፕረዝዳንት የነበሩት እና አንጃ ተብለው የተባረሩት አቶ ገብሩ አስራት በመፅሃፋቸው ገልፀዋል ።
እናም ይህንን ታሪክ ብናውቅም ህወሃት ላለፉት 27 ዓመት ከተማ ስላሳለፈ ተላምዷል ብለን እንገምት ነበር። ድመት ሞልክሳ አመሏን አትረሳ እንደሚባለው ያ ዓመል ዛሬም ካልለቀቀው በስተቀር ይህ ሁሉ የ elimination theory እንዴት ትዝ አላቸው?
ሌላው በጣም ገራሚው ነገር ከአህያ የዋለች ግደር ፈስ ትለምዳችለ እንደሚባለው ሆኖ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጭምር ሸገር እና ድረዳዋ በመሳሰሉ ከተሞች የተማሩ ወዳጆቻችን ባህሪያቸው ከከተማው ይልቅ ወደ ጦር ሜዳ ውሎ ማዘንበሉ እና ቀረርቶ መጀመራቸው ነው።
ይህ አካሄዳቸው ምነው እኛ ከምናውቀው ሌላ የሆነ ነገር አለ እንዴ እንድንል አድርጎናል።
ለማጠቃለል ይህንን የ elimination theory ወደ ማህበራዊ ሚዲያ ያመጣነው እኛ ቢንሆን እሄኔ ዋናዎቹ የዘር ፍጅት አውጃሃል በማለት ለቅሶ ብጤ ሲጀምሩ ግልገሎቹ ደግሞ ቃሊት እና ቂልንጦ እንልከሃለን ብለው ዛቻ ላይ ናቸው።
ለማንኛውም የአሁኑ የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ግምገማ እና ስብሰባ ህወሃት ወይም ሌላ አካል ፈልጎ የገባባት ሳይሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ እና የኦሮሞ ህዝብ በተለይ አስገድዶት ያደረገው ነገር ነው።እነ ለማ እና አቢይም የዚሁ የህዝብ ግፍት ውጤት እንጂ በ1980ዎቹ እንደተለመዱት የኦህዲድ ሰዎች ህዋሃት ጠጡ ስላቸው ጠጥተው ሽኑ ስሉአቸው የሚሸኑ አይደሉም ።
ለማለት የፈለኩት ለኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ግምገማ እና ስብሰባ ገፍ ምክንያቶቹ አሁንም ባሉበት አሉ። የህዝብ ብሶቶች ከመጀመሪያውም በላይ ሞልተው እየፈሰሱ እንጂ አልቀነሱም።መከራ የሆነውም ይህንኑ የህዝብ ብሶት ማስታገስ ነው።ይህንን የህዝብ ብሶት ዘንግቶ እብጥ እብጥ ማለት መዘዙ ፈስ በፈስ ከመሆን አልፎ ቅዘን በቅዘን ሊያደርግ ይችላል እንዳልል እኔም ቀረርቶ ነገር እንዳይሆንብኝ ትቼዋለሁ።
ስለዚህ ቀረርቶ እና ሽለላውን ገታ አድርገን ግምገማው ላይ ያሉ ሰዎች ቀልብ ገዝተው ሀገር የሚያድን ነገር ይዘው እንዲወጡ ብንመክር ጥሩ ነው።
Filed in: Amharic