>

የእንቁዎቻችን ጥሪ፡ “LAMMII KOF NAN FIIGA” "ለወገኔ እሮጣለሁ" ትገኛላችሁ?

የእንቁዎቻችን ጥሪ፡ “LAMMII KOF NAN FIIGA” “ለወገኔ እሮጣለሁትገኛላችሁ?

የኢትዮጲዉያን እንቁ የሆኑት አትሌቶቻችን በታሕሳስ 22 ከሶማሊያ ክልል ለተፈናቀሉ  ወገኖቻችን ማቛቛሚያ የሚውል የሩጫ ዝግጅት ማዘጋጀታቸው ይታውቃል። በዚህ ዝግጅት በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በነቂስ ወጥተው እንደሚሳተፉ እገምታለሁ። ይህ ተፈናቃዮችን የማቛቛም ስራ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን አገራዊና ሰብአዊ ቀውስ በመሆኑ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚኖሩ ሌሎች ኢትዮጲዉያን በገፍ ወጥተው በዚህ ዝግጅት እንዲሳተፉ መልእክት ለማስተላለፍ ነው።

ለመሆኑ እነዚህ ኢትዮጲዉያን እንቁዎች እነማን ናቸዉ? በግል የተወዳደሩትን ትቼ ኢትዮጲያ በኦሎምፒክ መሳተፍ ከጀመረችበት አንስቶ ያለውን ብናይ የሚከተሉትን እናገኛለን።

Gold Silver Bronze
Rio, 2016 Almaz Ayana (10000M) Feyisa Lelisa (Marathon) Mare Dibaba (Marathon)
1G, 2S , 5B Genzebe Dibaba (1500M) Tirunesh Dibaba (10000M)
Tamirat Tola (10000M)
Almaz Ayana (5000M)
Hagos G/Hiwot(5000M)
London, 2012 Tiki Gelana (Marathon) Dejene G/Meskel (5000 M) Tariku Bekele (Marathon)
3G, 2S, 2B Tirunesh Dibaba (10000M) Sofia Assefa (3000, Steeplchase) Tirunesh Dibaba (5000M)
Meseret Defar (5000M)
Beijing, 2008 Tirunesh Dibaba (10000M) Sileshi Sihine (10000M) Tsegaye Kebede (Marathon)
4G, 1S, 2B Kenenisa Bekele (10000M) Meseret Defar (5000M)
Tirunesh Dibaba (5000M)
Kenenisa Bekele (5000M)
Athens, 2004 Kenenisa Bekele (10000M) Ejigayehu Dibaba (10000M) Derartu Tulu (10000M)
2G, 3S, 2B Meseret Defar (5000M) Sileshi Sihine (10000M) Tirunesh Dibaba (5000M)
Kenenisa Bekele (5000M)
Sydney, 2000 Gezahegn Abera (Marathon) Gete Wami (10000M) Tesfaye Tola (Marathon)
4G, 1S, 3B Derartu Tulu (10000M) Assefa Mezgebu (10000M)
Haile G/Selassie (10000M) Gete Wami (5000M)
Million Wolde (5000M)
Atlanta, 1996 Fatuma Roba (Marathon) Gete Wami (10000M)
2G, 1B Haile G/Selassie (10000M)
Barcelona, 1992 Derartu Tulu (10000M) Addis Abebe (10000M)
1G, 2B Fita Bayisa (5000M)
Moscow, 1980 Mirus Yifter (10000M) Mohammed Kedir (10000M)
2G, 2B Mirus Yifter (5000M) Eshetu Tura (3000 steeplechase)
Munich, 1972 Mamo Wolde (Marathon)
2B Mirus Yifter (10000M)
Mexico, 1968 Mamo Wolde (Marathon) Mamo Wolde (10000M)
1G, 1S
Tokyo, 1964 Abebe Bikila (Marathon)
1G
Rome, 1960 Abebe Bikila (Marathon)
1G

Source: https://www.olympic.org/

እንቁዎቻችን የአገራቸው ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ እኛም ኮራ እንድንል በዓለም ዙሪያ የምንታወቅበት መጠሪያ፡ የረዥም ርቀት ሩጫ ባለቤቶች (ከረሐብና ጦርነት ውጪ) አድለውናል። ከግል ችሎታቸው ባሻገር የቡድን የአጋርነታቸው(All for one and One for all) ዓለምን ያስደመመ ነው። 1980 ሞስኮ ኦሎምፒክ አጋርነታቸውና የቡድን ስሜታቸው ለድል እንዴት እንዳበቃቸው የዓለም ጋዜጣዎች በሰፊው ዘግበውታል። ይህ ሊንክ ሶስቱ እንቁዎቻችን፡ምሩፅ ይፍጠር መሐመድ ከድርና ቶለሣ ቆቱ የተፎካካሪያቸውን መንፈስና ጉልበት በግል ጥረትና በጋራ እንዴት አሸንፈው ለድል እንደበቁ ያሳያል። https://www.youtube.com/watch?v=C6eHUXDCKmQ

2004 የአቴንስ ኦሎምፒክ የቀነኒሳ ሐይሌና ስለሺ አጋርነት ቢያስደምመው እውቁ  የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ ቀነኒሳ አዲስ አበባ ሳይገባ አንበሳ፡ቀነኒሳታሪክ ተሰራ የሚለውን ዜማ አበረከተለት። ይህንን ሊንክ ይመልከቱ https://www.youtube.com/watch?v=Ios9C1V3RCM

የኢትዮጲዉያን እንቁ የሆኑት አትሌቶቻችን በታሕሳስ 22 ከሶማሊያ ክልል ለተፈናቀሉ  ወገኖቻችን ማቛቛሚያ የሚውል የሩጫ ዝግጅት እኛው ለኛ በሚል መርህ አዘጋጅተው ለወገን ደራሽ ወገን ነው ብለው አድመውናል። በኦሎምፒክ ሜዳ ይሳዩንን አብሮነትና አጋርነት የመጀመሪያውን ሩጫ  በአዲስ አበባ በማድረግ ገቢው ብቻ ሳይሆን አብሮነታችንና አጋርነታችን ለወገን ደራሽነታችን ይጠነክር ዘንድ እድል ሰጥተውናል። እንደታዋቂነታቸው ቢሆን London or New York or Washington DC ቢያደርጉ የሚሳተፉት እነማን እንደሆኑ መገመት ይቻላል።  የሚገኘውም ገቢ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ታዋቂነታችውንና የተቀረው ዓለም ስለእንቁዎቻችን የሚለውን ለማየት ይቺን ሊንክ ይመልከቱ። http://www.vogue.com/article/dibaba-family-ethiopian-distance-runners-olympics-2016-rio-de-janeiro

http://viiphoto.com/articles/fastest-family-world /የሚቀጥለውን ሩጫ አትሌቶቻችን ድል በተቀዳጁባቸው የአውሮፓና አሜሪካ ታላላቅ ከተሞች በማዘጋጀት ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ማቛቛሚያ እንደሚያሰባስቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

በአገር ውስጥ ያለን በሩጫው በመሳተፍ፣ መሮጥ የማንችል ለሚሮጡትና ራቅ ካለ ቦታ ለሚመጡት የመጓጓዧ አገልግሎት በመስጠት፣ ከአገር ውጭ ያለነው ሯጮችን ስፖንሰር በማድረግ አጋርነታችንን እናሳይ። እኛው ለኛ፡ለወገን ደራሽ ወገን ነው።

“LAMMII KOF NAN FIIGA” “ለወገኔ እሮጣለሁትገኛላችሁ?

Filed in: Amharic