>

መለስ ዜናዊና  ሀሳብ ምን አገናኛቸው? (አቻምየለህ ታምሩ)

ታላላቆቹ አሳቢዎች እነ ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ፣ አቶ  አበበ ረታ፣ አቶ በለጠ ገብረ ጻዲቅ፣ ብላታ ደሬሳ አመንቴ፣ሐዲስ አለማየሁ፣መኮነን ሀብተወልድ፣ከተማ ይፍሩ፣ ነጋድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ፣ አለቃ አስረስ የኔሰው፣ ብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል፣ አለቃ አያሌው ታምሩ፣ . . . ወዘተ  በነበሩባት ምድር ተሰርቶ ያላለቀው፣ የእውቀት ጾመኛውና ማይምነትን  በኩራት እንደጌጥ ለብሶ የኖረው የትግራይ ነውረኛ ሽፍቶች አለቃ መለስ ዜናዊ «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ» ተብሎ ሲነገር ከመስማት በላይ  በሰው አእምሮ መሳለቅ የለም።

ለመሆኑ መለስ ዜናዊና ሀሳብ፤ መለስ ዜናዊና እውቀት ምን አገናኛቸው? መለስ ዜናዊ የነበሩትንን የሀሳብና የእውቀት ተቋማት ወደ ድንቁርና ማዕከላት አውርዶ  ወደ መቀመቅ የወረደ የእውቀት ጾመኛ ነው። ሀሳብ  በተፈጥሮው ድንበርና ወሰን  የለውም። የመለስ ዜናዊ ድንቁር ግን የሚጀምረው አንድን ነገር ከቅዬውና ከመንደሩ  አሻግሮ  ማሰብና ማየት ካለመቻሉ ነው።  መለስ ዜናዊ የሀሳብ  ገዳይና ቀባሪ  እንጂ የሀሳብ ተከታይና  ሀሳብ ሲያልፍ ያላየው ቂመኛ አውሬ  ነበር።

ከዚህ በፊት ጽፌው እንደነበረው መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ  የጮሌነት ውድድር ያደረገው አንዴ ብቻ ነው። ይህም በ1960ዎቹ አጋማሽ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ማህበር [University Students Union of Addis Ababa] የካውንስል ምርጫ ሲያካሄድ ነበር። ይህ ውድድር መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ ለመጀመሪያም ለመጨረሻው ጊዜ ያካሄደውና  አለማወቁን ያሳወቀበት  ሐቀኛ ውድድር ነበር። በውድድሩ መለስ ዜናዊ በአዚዝ መሐመድ [አሁን ዶክተር ሆኗል] በሰፊው ተበልጦ በዝረራ ተሸንፏል።

ወያኔዎችና ቀለብ የሚሰፈርላቸው «ቋንቋ በቀል» ሆድ አደሮች «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ» የሚሉት መለስ ዜናዊ በሕይወት ዘመኑ አንዴ ባካሄደው  ሐቀኛ የጮሌ  ውድድር በጠባቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ማህበር የካውንስል ወንበር ተወዳድሮ በአዚዝ መሐመድ በዝረራ ተሸንፎ ከጨዋታ ውጭ የሆነውን ጉድ ነው።

በሻዕብያ አንጋሽነት የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ ሆኖ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ከተሰየመ በኋላ መለስ ዜናዊ ያሳየው ጠባይ ቢኖር «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ» ሳይሆን ተሰርቶ ያላለቀ በጥላቻ የናወዙ የትግራይ ሽፍቶች አለቃ መሆኑን ነበር።  መለስ ዜናዊ ዛሬ አንድ ቅንጫቢ ነገር ካነበበና ስለአንድ ነገር ቁንጽል ወሬ ከፈረንጅ አፍ ከሰማ፤ ሌሊቱን ስለዚያ ስላነበበው ቅንጫቢ ነገር ወይንም ከፈረንጅ አፍ ስለሰማው ቁንጽል ወሬ በጉዞ ማስታወሻ ደብተሩ ሲሞነጭር ያድርና በበነጋታው ወደ አገራዊ «ፖሊሲ» ይቀይረዋል። ADLI፤ ውሀ ማቆር፤ BPR፤BSC፤ ማይክሮ ፋይናንስ፤ ውጤት ተኮር፤ ጥቃትንና አነስተኛ ተቋማት፤ልማታዊ መንግስት፤ ወዘተ የሚባሉት የመለስ ዜናዊ  «ልማታዊ መስመሮች »  የሚባሉት ሁሉ በዚህ መልኩ «አገራዊ ፖሊሲ» የሆኑ  የድንቁርና መገለጫዎች ናቸው።

መለስ ዜናዊ እንኳን «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»ሊሆን ሀሳብ በደረሰበት ያልደረሰ፣ የሀሳብ ድህነትን የአገዛዙ ማዕከል  ያደረገ፣በሞያና በእውቀት የበለጸጉ ኢትዮጵያውያንን  በማንነታቸው ምክንያት  እያሳደደ አገሪቱን በሙሉ  መጻፍና ማንበብ በማይችሉ  ደንቆሮ የትግራይ የገበሬ ወታደሮች  ያጥለቀለቀ፣  እንደ ሳሞራ የኑስ አይነት አንድም  የኦፊሰር  ትምህርት ቤት  ደጃፍ እንኳ ያልረገጡ  የትግራይ የገበሬ ወታደሮችን  ከአርባ አመት የትምህርትና የአገልግሎት ዘመን በኋላ  የሚገኘውን  ሙሉ ጀኔራልነትን ያደለ፤  በሀሳባቸው ምንክንያት አርባ ሁለት የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን ያባረረና የሀሳብ ምድራዊ ጠላት ነበር።

ባጭሩ መለስ ዜናዊ ማለት ያነበበውን ቅንጫቢ ነገር ወይንም የሰማውን የፈረንጅ ቁንጽል ወሬ ሁሉ ባነበባው ቅንጫቢ ነገር ላይ ተመስርቶ ወይንም የሰማውን ቁንጥል የፈረንጅ ወሬ ይዞ በማግስቱ ወደ «አገራዊ ፖሊሲ» በመለወጥ ስራ ላይ ተጠምዶ በየጊዜው እየተገለባበጠ ሲያምታታ የኖረ ለቀበሌ መሪነት እንኳ የማይበቃ የስነ መንግሥት አስተሳሰብ ሲያልፍ ያለነካው ነውረኛ ግለሰብ ነበር። ቅንጫቢ «አዲስ ነገር» ባነበበ ወይንም ቁንጽል የፈረንጅ ወሬ በሰማ ቁጥር ትናንት ያወጣው «አገራዊ ፖሊሲ» ላይ የፈረመበት ቀለም ሳይደርቅ ወይንም ትናንትና ያወጣውን «አገራዊ ፖሊሲ» ፍሬ ሳያሳየን ዛሬ ባነበበው በሌላ ቁንጽል ነገር ወይንም ከፈረንጅ አፍ በሰማው ቅንጫቢ ወሬ ሲለውጥ የኖረ ባሪያ አሳዳሪና የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ አምበል ነበር።

ባጠቃላይ መለስ ዜናዊ የአገር ፖሊሲ ያህል ሀሳብ  እንደ መስሪያ ቤት ማኑዋል በየቀኑ እየቀያየረ ሲያወናብድ የኖረ፤ «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»  ሊሆን ቀርቶ ሀሳብንና ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች አሳዶ ያጠፋ፣ ከሀሳብ ጋር ትውውቅ የሌላውና በኢትዮጵያ ምድር  የጨለማ ግርማን ያሰፈነ የእውቀት ጾመኛ ነበር።  ከምንም በላይ ደግሞ ሀሳብ ላላቸው ሰዎች  መለስ ዜናዊ ማለት በኢትዮጵያ ምድር ሰማያዊውን የሲዖል በር የበረገደ፤ በመሞቱና በህይወት በመኖሩ መካከል ያለው ልዩነት ሞቱ ጠቃሚ፡ ኑሮው ጎጂ የነበርና  ድንቁርን ተቋማዊ ያደረገ፣ የአዋቂ ሰዎችና  የእውቀት ምድራዊ ጠላት ነበር።

መለስ ዜናዊን «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»  ያደረጉት ሰዎች እስቲ የሚከተሉትን  ጥያቄዎች ይመልሱ፤

1. «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈው»  መለስ ዜናዊ   ብቃት ኢትዮዽያን በድህነት ከምትታወቅበት ደረጃ ፈቀቅ ያላደረገው ለምንደን ነው?

2. ኢትዮዽያ ውስጥ ተሰሩና ታነፁ የሚባሉት የመሰረተ ልማትና የትግራይ ቱጃሮች ሕንዳዎች  የተገነቡት «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ አሸነፈ» ባላችሁት በመለስ ዜናዊ   አመራር በተገኘው አንጡራ ሃብት ነው ወይስ አሜሪካና ሌሎች የምዕራብ መንግሥታት ሁሌም እንደሚያደርጉት ወዳጅ አምባገነኖችን መላዕክ የሚያስመስል አሳሳችና ሁሉን ተጠቃሚ የማያደርግ የEconomic Boom የሚፈጥር የሚመስል እርዳታ ስለተዥጎደጎደ?

3. «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»   እድሜ ልኩን ከጥራጥሬ ጀምሮ እስከ ቢሊዬኖች ዶላር እርዳታ እየተንጋጋለት የልመና መዝገብ ቋሚ ደንበኛ ይሆናልን? ኢትዮጵያን የ30 ቢሊዮን ባለ እዳ ከማድረግ «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ» እራሱን ችሎ ነፃ መሆንን አይመርጥም?

4. «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»   ከእርዳታዎች ጋር ተያይዘው ለሚመጡ ተፅዕኖዎች[conditions] እየተንበረከከ፤ እርዳታዎችም  የተንበርካኪነቱ  ሽልማቶች እያደረገ፤ በኢትዮጵያ ስም በሚበደረው ገንዘብ ትግራይን በኤፌርት ለማልማት እያዋለና እየዘረፈ  የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል  ግን  በውድቀት አፋፍ ላይ  እያጣጣረ  የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሶ እንዴት ሊገኝ ቻለ?

5.ተግባር ከቃል የጎላ ድምፀት አለው ነው የሚባለው፤ ታዲያ «የሀሳብ ድህነትን  ታግሎ ያሸነፈ መሪ»   በቃላትና በፊደል የሚሟሟ ይመስል የህትመት፣ ብሮድካስቲንግና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያወችን፤ ማለትም የግል ጋዜጦንና መፅሔቶችን ፣ የግል ሬዲዮኖችንና የቴሌቪዥን ስርጭቶችን፣ የሚነበቡና የሚደመጡ ዌብ ሳይቶችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ተቺ ምሁራንንና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችን ትንሽ ትልቅ ሳይል በጠላትነት ፈርጆ በማፈን፣ በማዋከብ፣ በማሰርና በማወክ ስራ  ላይ እድሜ ልኩን ተጠምዶ የኖረው  ለምንድን ነው?  እስቲ መልሱልኝ?!

Filed in: Amharic