>

ከአርማጭሆ እስከ አድዋ (ሀብታሙ አያሌዉ)

          (ከመፀሐፍ ቅዱስ  ራዕየ ዬሐንስን ያነበበ
           ዘይቤኛ ፅሑፌን የበለጠ ይረዳዋል፤ 
           በዘይቤኛ መፃፍ ወትሮም የነበረ ነው)

ጎንደር አርማጭሆ ወርደህ ይሄንን የእምዬ ኢትዮጵያን የአለት ላይ ቅርፅ ስታይ ጎበዝ አናፂ የተጠበበበት እንዳይመስልህ፤  ከላይ ከሰማያት የፈጣሪ ምስክርነት መገለጫ እንዲሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ምልክትነት ቆሞ ዘመናት የተሻገረ አለት ነው። በቅዱስ መፅሐፍ ጌታን ለማመስገን የኢየሩሳሌም ህፃናት ዝም ቢሉ አለቶች ይዘምራሉ እንደተባለ ህወሓት በከዳተኛ ይሁዳዊ ባህሪው በገዳይ (ሰቃይ) አይሁዳዊ ባህሪው እምዬ ጎንደር ስለ ኢትዬጵያ ዝም ትበል ቢል የሚዘምሩ አለቶች እንዳሉ ጭምር ማስረጃዬ አማናዊ ምስክር ነው። “የአማራን አጥፋው” የህወሓትን ፖለቲካ ሙሉ በሙሉ ለማምከን በጎንደር በጎጃም በወሎ በሸዋ ክተት የተባለ እንደሆን “ወስልተህ ብትቀር ማርያምን ትጣላኛለህ”  የሚለውን የእምዬ ምኒልክን ጥሪ እያስታወስን፤
የቴዲ አፍሮን “ወደ አድዋ ሲሄድ ምኒልክ ኑ ካለ
                      እረ አልቀርም በማርያም ስለማለ” ን እየዘመርን እናቀና ዘንድ ጊዜው ይሆናል። በዚያ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ወንድሙን ይታደግ ዘንድ “አማራ ኬኛን ” ን እየዘመረ ኦሮሞ ፈረሱን ያሰግራል፤ ተንቤንና እራያ በራስ አሉላ ወኔ  ” ወድአዲ” እያለ ይመጣል። ጉራጌው፣ ከምባታው፣ ሐድያው፣ ከፊቾው፣ ቤኒሻንጉል ጋምቤላ አፋርና ሶማሌው፣ መገን የሸገር ልጅ እነ እሳት የላሰው የነብር አራስ ሆነው ይደርሳሉ።   ያን ጊዜ …
“ወዮልሽ ኮራዜን ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ ላንቺ የተነገረ ለሰዶምና ለገሞራ ህዝብ ተነግሮ ቢሆን በዳኑ ነበር ”  እንደተባለ ጆሮአቸው የተደፈነ ጨካኞችን ላፈራች ለአድዋ ወዮላት። ንፁሃኑን ከከርሷ ያወጣ ዘንድ መልአኩን ከላከ በኋላ በእርሷ ዘንድ ለቅሶና ዋይታ ይሆናልና።

አምስተኛው ማህተም በተፈታ ጊዜ መልዓኩን ይህ መቼ ይሆናል ንገረኝ አልኩት፤  እሱም  ገና ጥቂት ጊዜ አለ ጠብቅ አለኝ። ዳግመኛም መልዓኩን ይህ ፅዋ ከኛ ያልፍ  ዘንድ እማልድሃለሁ አልኩት፤ መልዓኩም እንዲህ አለ ዮናስ ወደ ነነዌ ህዝብ እንደተላከ እንዲሁ  መልዕክተኞች ወደነሱ ሄደዋል ይድኑ ዘንድ ቢወዱ ቢመለሱም ስለበደላቸውም ቢናዘዙ ቢተዋትም ስለዚህ ነገር ፅዋዋ ታልፋለች። እምቢ ቢሉ በአመፃቸውም ቢፀኑ ነደ እሳት ይበላቸዋል፤ በነሱ ዘንድ ብዙ ልቅሶ እና ዋይታም ይሆናል አለኝ።  እኔም ገና  በፊቱ ወድቄ ነበርና አሜን እንደቃልህ ይሁን አልኩት።

Filed in: Amharic