>

"በተቃዋሚ ተስፋ ቆርጠን ከወያኔ ማህጸን ለዉጥን ብንጠብቅ ልንወቀስ አይገባም" ይሉሃል የወያኔ የመደብ አጋር ተቃዋሚዎች (ሸንቁጥ አየለ)

በወያኔ ስርዓት መሰረታዊ ባህሪያት የሚስማሙ ብዙ ሰዎች ወያኔ እንቅፋት የመታት ሲመስላቸዉ ገልበጥ ብለዉ የወያኔ ተቃዋሚ መስለዉ ይቀርባሉ::ሆኖም በወያኔ ህገ መንግስት ይስማማሉ::በወያኔ የክልል አከላለል ይስማማሉ:: በወያኔ ስነ መንግስት አመሰራረት ዘይቤ ይስማማሉ::
ወያኔ 26 አመታት ሙሉ በኢትዮቶጵያ ህዝብ ላይ በወሰደዉ ወንጀለኛ እርምጃ ይስማማሉ::ይባስ ብለዉም ወያኔ እንደሚለዉ ሁሉ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር በተረት ተረት የተፈጠረች: በቅኝ ግዛት የተሰበሰበ ህዝብ ያላት ሀገር ናት ብለዉ ይሰብካሉ:: ልባቸዉ በከፍተኛ ጥላቻ ከመሞላታቸዉ የተነሳ ከነሱ ጎሳ ዉጭ የሚያልቀዉ ሰዉ አያስጨንቃቸዉም::ነገ ተያይዞ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመሰግበት የእርስ በርስ የጎሳ ጦርነት ሀሴት ያጭርላቸዋል::ልባቸዉ ግማሽ ጥቁር እና ግማሽ ብርሃን ነዉ::ሆኖም ፍጹም ፈሪዎች እና አድር ባይ ናቸዉና ዛሬ የያዙትን አቋም ነገ ለመለወጥ ፈቃደኛ ናቸዉ::

እነዚህ ሀይሎች በድርጅት ስብስብ ትንታኔ ሲቃኙ ዝርዉ ናቸዉ::አንድ ድርጅት ዉስጥ አታገኛቸዉም::ወይም ደግሞ በአንድ አካባቢ አታገኛቸዉም::ዉጭ ሀገር ወይም ሀገር ቤት ሊሆኑ ይችላሉ::ግን አንድ የሚያሰባስባቸዉ ባህሪ ወያኔ እና ወያኔአዊ አሰራር በጣም ይመቻቸዋል::ፍትህ እና እዉነት ለነሱ ቦታ የለዉም::መደባቸዉም ሲጠና አንድ ነዉ::ወያኔነት::
ወያኔ ሊወድቅ የተንገዳገደ ሲመስላቸዉ ሰለሽግግር መንግስት ወይም ስለ እርቅ አለዚያም ከወያኔ መሃል ተነስቶ ወያኔን ስለሚጥለዉ ጀግና ይሰብካሉ::ልክ ግር ግሩ ሲያልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ እና መከራ ይረሳቸዉ እና በጀርባቸዉ ለጥ ብለዉ እየተኙ ከወያኔ ጋር የፖለቲካ ድሪያቸዉን ዉስጥ ዉስጡን ያቀልጡታል:: ወያኔ ጉዳዮች እና ስብሰባዎች ላይ በኦህዴድነት: በብአዴንነት : በደህዴነንት ወይም በሆነ ፓርቲ ጥላ ስር አለዚያምም በሆነ ሲቪል ማህበር ስር ተወሻሽቀዉ ከወያኔ ምናምንቴ እና ርኩስ ሀገር የማጥፋት ሴራ ጋር ሲተባበሩ ይገኛሉ:: እናም ለምን ተብለዉ ሲጠየቁ ያለማፈር “ፖለቲካ ፍሌክሲብል መሆን ይጠይቃል::ድርቅ አትበሉ::አክራሪ አትሁኑ” ይሉሃል::ያንተን ጀግንንተ በነሱ ጭቃ ባንዳነት አኮስሰዉ እነሱ ባንተ ላይ የስነልቦና የበላይነት ሊያሰፍኑ መሆኑ ነዉ::

እነዚህ ሰዎች አንድ አስደናቂ እና ታላቅ የማጭበርበር ተሰጥኦ አላችዉ::በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ለዉጥ የመጣ ከመሰላቸዉ የለዉጡ አካል በፍጥነት ይሆናሉ::በጣም ሳያፍሩም ለዉጡ ከወያኔ ከራሱ እንደሚመጣ ጭመር ይሰብኩሃል::እነሱ ሚሊዮኖች ስለሚደርስባቸዉ ነገር ጉዳያቸዉ አይደለም::
በአጋጣሚ እንቅ አድርገህ የያዝካቸዉ እንደሆነ ግን እጅግ በጣም አስገራሚ እና ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለዉን ተቃዋሚ ያሙልህ ይጀምራሉ::አሜታቸዉን ሲደመድሙም እንዲህ ይሉሃል::
“በተቃውሚ ተስፋ ቆርጠን ከወያኔ ማህጸን ለዉጥን ብንጠብቅ ልንወቀስ አይገባም” ይሉሃል ::ይባስ ብለዉም አንተም አብረህ ከነሱ ጋር ከወያኔ ማህጽን ለዉጥ እንድትጠብቅ ይጎተጉቱሃል:: ሀያ ስድስት አመታታ የኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ መሰሉ ድራማ ዉስጥ አልፏል:: የሰሞኑ ድራማም የነዚህ ድኩማን ሀይላት ተባባሪነትን ባያገኝ ኖሮ እንዲህ በርካታ መደናገሮችን አያስከትልም ነበር::ሆኖም የኢትዮጵያ እዉነተኛ ጀግኖች በማንም የባንዳ ሀሳብ ተወዣብረዉ አያዉቁም::ሽህ አመት የተዋጋ ህዝብ: ህሽ አመት በምድር ላይ የኖረች ኢትዮጵያ በስዉር ጀግኖቿ ልዩ የማይናወጽ ትግል  ብሎም  በእግዚአብሄር ታምና ጭምር ነዉ እንጅ ፈተናት ከዘመናት እስከ አዝማናታ ተለይቷት አያዉቅም::: እንደ ወያኔ እና እንደ ወያኔ ተባባሪ ሀይላት ቢሆንም እማ ኢትዮጵያ ጠፍታ አልነበር?

ለጊዜው ኢትዮጵያ ጀግኖቿ በጨለማዉ ዉስጥ እየተጓዙ ስለሆነ የሀገሪቱ ጀግኖች የማያዩዋቸዉ ይመስላቸዋል::በጨለማ ዉስጥ የሚመላለሰዉ ጀግና እና በመከራ ዉስጥ የወደቀዉ ህዝብ ግን በደንብ ያዉቃቸዋል::እራቁታቸዉን አቁሞ ይመረምራቸዋል::በህዝቡ እና በጀግና መሃከል እየገቡ እነዚህ አድር ባይ ሀይሎች ግን በርካታ የብተና ስራ ስለሚያከናዉኑ የትግል ጉዞዉ ሊረዝም ችሏል::ግን ጉዟችን ረዥም ትግላችንን መራራ የሚሉ ጀግኖች በጨለማዉ ዉስጥ በጥንቃቄ መመላለሳቸዉን አላቆሙም:: እዉነትም ጉዞዉ ረዥም ትግሉም መራራ እንጅ አስመሳዮች እንደሚሉት ወያኔን ለመንቀል ከወያኔ ዉስጥ የሚነሱ ወንጀለኛ ሀይሎች የኢትዮጵያን ህዝብ ከባንዳዉ የወያኔ ስርአት በቀላሉ ነጻ አያወጡትም::

እናም በጥንቃቄ ስትመረምራቸዉ ወያኔ ለሃያ ስድስት አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ እንዲጨፍር ዋና ባለድርሻዎች እነዚህ መሆናቸዉ ግልጽ ነዉ::ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ያለዉን ተቃዋሚ አጣጥለዉ ጸረ ኢትዮጵያዉያን ወያኔዎችን ወይም የወያኔ አሽከሮችን ያነግሱልሃል:: ከእነዚህ ፈጽመህ እራቅ::በተለይ በሞቀበት የመተባበር አይነት ባህሪ ካለህ በቀላሉ እንደሚያሳስቱህ አዉቀህ እንዲዝህ አይነት ሀይላት መረብ ዉስጥ እንዳትገባ በደንብ መርምራቸዉ::

Filed in: Amharic