>
5:13 pm - Wednesday April 20, 2738

ተክደናል -ከመግለጫው በኃላ ኦሮሚያ ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ያለ ስሜት ሆኗል። (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

ኦህዲድ ከኢህአዴግ ጋር በዋናነት መነጋገር ያለበት ስለ መከለካያ ስልጣን ስለ ደህንነቱ ስልጣን ስለ ጠቅላይ ሚንስትርነት ስልጣን እና ስለ ሌሎች ጉዳዮች አይደለም።ኦህዲድ በዋናነት መነጋገር ያለበት በህዝብ መብቶች ላይ  ውይይቶችን በግልፅ እና በህገመንግስቱ መሰረት ስለመፈፀም ነው መነጋገር ያለበት።ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ኦህዲድ ለ27 ዓመት እየበላ እንድቀጭጭ ያደረገው አሰራር  ነው።ኦህዲድን ድንክዬ ሆኖ እንድቀር ያደረገው ሌላ ነገር ሳይሆን ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚሉት ጥርነፋ ነው።በዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መጠርነፍ ለሰሜን ባህል ልቀርብ ይችላል።በገዳ ስርዓት ውስጥ ላለፈው የኦሮሞ ባህል ግን እጅግ ባዓድ እና ገዳይ ነው።ኦህዲድ ያላፉትን 1 ዓመት በኦሮሞ ህዝብ ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ጭምር ተስፋ የተጣለበት ድርጅት እንዲሆን ያደረገው ሌላ ነገር አይደለም።ይህንን የዲሞክራሲያዊ ማዕካላዊነት ጥርነፋ ስለጣሰ ብቻ ነው።ላለፈው 1 ወርም ኦህዲድ የተንገዳገደው በዚህ  በዲሞክራሲያው ማዕከላዊነት በመጠኑም በመጠርነፉ ነው።ከዚያ ውጭ የድርጅቱ መሪዎች እንዲሁም የሚገርም ነገር አድርገዋል።አልተለወጡም።ይህ ግን የህዝብ እውነት ሳይሆን የኔ እውነት ነው።
የኦህዲድ መሪዎች በኢህአዲግ ግምገማ እና ስብሰባ ላለፉት 18 ቀናት  ያደረጉትን አኩሪ ታሪክ በፊት ለፊት ብያደርጉ መላው የኢትዮጵይም ህዝብ ከጫፍ ጫፍ  ከአይን ያውጣችሁ ብሎ እንደሚያጨበጭብላቸው ምንም ጥርጥር የለኝም። አሁን ግን ነገሮች በፍጥነት እየተለዋወጡ ነው። አሁን ግን ህዝቡ አይናችሁ ይውጣ ማለት ጀምሯል።እሄ ደግሞ ምክንያቱ ኦህዲድ ገና የረጋ ደጋፍ አለፈራም።ደጋፍዎቹ በኦህዲድ የ27 ዓመት አስቸጋር ጉዞ ውስጥ አልፈው የመጡ ስለሆነ ኦህዲድ የሚሰራቸው መጠነኛ ስህተቶች እንድንሸራተቱ ያደርጋቸዋል።

ስለዚህ ኦህዲድ በሆነ መልኩ ስለ ሰሞኑ ስብሰባ በመጠኑ እንኳን ነገሮችን ግልፅ ካላደረገ በስተቀር በቋፍ ላይ ያለው የኦሮሚያ ሁኔታ መተረማመሱ ነው። ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚመጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት በወጣቱ መሃል  ከመግለጫው  በኃላ ተክደናል የሚል ወሬ እንደሰደድ እሳት እየተሰራጨ ነው።
ስለዚህ የኦህዲድ ስራ አስፈፃሚን ቀላል ነገር እንዲያደርግ ብቻ እንጠይቃለን። ሌላ ስራ ስራ እያልናችሁ አይደለም። በቃ የሚያስመሰግናችሁን ነገር አርጋችኃላ።እሱን በመጠኑ ለህዝብ ግለፁ። ያለምግባራችሁ በቋፍ ላይ ያለውን ኦሮሚያ እሳት ውስጥ አትክተቱ። ኢህአዲግንም ሆነ ሀገሪቷንም እንድትፈርስ ምክንያት አትሁኑ።
ይህ ነገር በፍጥነት ካልሆነ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ጥቅም የለውም። መፍጠን ያዋጣል።

Filed in: Amharic