ከአራት አመታት በፊት ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ ትውልዱን በሚመለከት አንድ ገላጭ ንግግር አድርጎ ነበር። ንግግሩ. . .
በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ በወንጀል ክብረ ወሰን የተቀዳጀ አገዛዝ በግፍ አስሮ ሲያሰቃያቸው የኖራቸውን የሕሊና ሰዎች ጊዜ ለመግዛት ሲል ከጠባብ እስር ወደሰፊው እስር ቤት እንዲዘዋወር በረጅሙ አስሬ እለቃቸዋለሁ ስላለ እንደ በጎነት ተቆጥሮለት በምድር ላይ ሲመሰገን ያየነው ብቸኛው የአለማችን አፓርታይድ አገዛዝ ወያኔ ብቻ ይመስለኛል!
ምድሪቷን በጭካኔ ያጨቀያት የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ ሳይወገድና ሕዝባዊ መንግሥት ሳይቋቋም ዛሬ የፖለቲካ እሥረኞች ቢፈቱ ነገ ተመልሰው ወደ ዘብጥያ ላለመውረዳቸው ምን ዋስትና ኖሮ ነው ገና «የፖለቲካ እሥረኞች ይፈታሉ» ስለተባለ ጮቤ የምንረግጠው? ከዚህ በፊትም ጨካኙ መለስ ዜናዊ «የአገር ሽማግሌዎች» የሚባሉት እነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የኢትዮጵያ ሚሊኒዬም በሚከበርበት ወቅት «እስር ቤቱን ሁሉ ባዶ አደርግላችኋለሁ» ብሎናል ብለውን ነበር። በተግባር ግን ከኢትዮጵያ ሚሊኒዬም በኋላ ዘብጥያ የወረደውን የህሊና እስረኛ ብንቆጥረው በታሪካችን እስር ቤት ከገባው ቁጥር አንጻር መለስ ዜናዊ «እስር ቤቱን ሁሉ ባዶ አደርግላችኋለሁ» ካለ በኋላ የታሰረው በብዙ እጥፍ ይበልጣል።
በጣም አስቂኙ ነገር ደግሞ ማዕከላዊ ተዘግቶ ሙዚየም ይሰራበታል መባሉ ነው። ይታያችሁ! በማዕከላዊ የማሰቃያ ቦታ ላይ ሙዚየም እገነባለሁ የሚለን ሲያሰቃዬን የኖረው የስቃዩ ጌታ ወያኔ ነው። አንድ እውነት አለ፤ በማዕከላዊ የማሰቃያ ማዕከል ሙዚየም መገንባት አለበት። ሆኖም ግን ሙዚየሙ መገንባት ያለበት ሲያሰያቃን በኖረው በግፈኛው ክብረ ወሰን በሰበረው በወያኔ ሳይሆን በግፉዓን ታሳሪዎችና ከወያኔ ግፍ በተረፉ ንጹሀን ኢትዮጵያውያን ነው። ሲያሰቃየን የኖረው ወያኔ ማዕከላዊ ማሳቀያ ላይ ግርፋት ያብቃ ብሎ ሙዚየም ቢገነባ እንደ ቀይ ሽብሩ የመታሰቢያ ሙዚዬም a mockery of justice and history የሚሆን መሳቂያ የድንጋይ ክምር ካልሆነ በስተቀር የግፍ ማድረቂያ ቃል ኪዳን ሊሆን አይችልም። ወያኔ በማዕካዊ ማሰቃያ ሲተለትለን የኖረው የቀይ ሽብር የመታሰቢያ ሙዚዬምን አዲስ አበባ መሃል ላይ አቁሞ መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
ባጭሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት በግፍ የእግር ብረት ውስጥ ሆነው በትግራይ መርመሪዎች የሚሰቃዩት የህሊና ሰዎች ብቻ አይደሉም። ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከትግራይ በበቀሉ ፋሽስቶች የማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ ነን። ኢትዮጵያ ከፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ እስር ነጻ ሳትወጣ «አሸባሪ» ብለው በግፍ ያሰሯቸውን የህሊና ሰዎችን በጭካኔ ካሰሩበት ከጠባቡ የሰው መታረጃ ቄራ ወደሰፊው የማሰቃያ እስር ቤት እንዲዘዋወሩ በረጅሙ አስረው ስለለቀቋቸው ፍትህ የተገኘ፣ ሰላም የመጣ፣ ነጻነት የተጎናጸፍን አድርገን አንቁጠረው። በቃላት ከሚገለጸው በላይ ጨካኝ ወንጀለኛ የሆነው ወያኔ ከነ ሕገ አራዊቱና የአፓርታይድ ድንጋጌው ተወግዶ ግፈኞች እኛን ያሰቃዩበት እጃቸው የኋሊት በመጫኛ ታስሮ እውነተኛ ችሎት ፊት ቀርበው ለፈጸሙት ጭካኔ ፍርዳቸውን እስካላገኙ ድረስ ለትንፋሽ ማግኛና ለጊዜ ለመግዣ ብለው «የፖለቲካ እሥረኞች ይፈታሉ» ስላታለሉን በወያኔ ግፍ በጨቀየችዋ ኢትዮጵያ ስርየት ሊኖር አይችልም።
ኦሮማራ ይለመልማል! ሕዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!