እኔ ደርግ ለሰራው ግፍ ጥብቅና ለመቆም አልዳዳም።ነገር ግን ደርግ ዜጎችን አማራ ወይም ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ አላሰቃየም።ማንንም ቢሆን በዘሩ ለይቶ አላጠቃም።ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ትልልቅ ባለስልጣናቱ ሳይቀር ከአጋሚዶው ቡድን ዘር የሚመዘዙ ናቸው።ነገር ግን እንደዚህ አይነት ቆሻሻ ነገር ውስጥ አልገባም።
ርዕዮተ አለማዊ ልዩነትን ታሳቢ አድርጎ የትውልድ እልቂት መፈፀሙ ግን እሙን ነው።
እነዚህ እርኩሶች ግን ዜጋን በዘሩ ወይም በብሄሩ ብቻ 27 አመት አሳሩን ሲያሳዩ ነፍሱን ሲቀጥፉ ኖረዋል።ሰው እኮ በማዕከላዊ የሚሰራውን ብቻ ይሆናል ግፍ የሚለው።ነገር ግን በተጠናና በተደራጀ መልኩ በተለይም አማራው ላይ ሲቀጥልም ኦሮሞው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተለያየ መልኩ ተፈፅሟል።
ደርግ የዘር ማጥፋትና ማፅዳት ወንጀል አልፈፀመም !
ይሄ አጋሚዶ ቡድን እኮ ከ5 ሚሊዮን በላይ አማራና ከዛ ያላነሰ የኦሮሞ ተወላጆችን ፈጅቷል።ጋምቤላ ላይም የዘር ማፅዳት ወንጀል ፈፅሟል።ሱማሌ ክልል ላይም ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀል አካሂዷል።
ኮንሶ ላይ እሳት አዝንቧል።በጋሞጎፋ ዞን የቅጫ ህዝብ ላይም እንደዛው። ሲዳማውም አልቀረለትም በጠራራ ፀሃይ የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዶበታል።ስንቱን እንዘርዝር…..
ይህ ሁሉ ግፍ ከማዕከላዊ ውጪ ነው። ማዕከላዊ ውስጥ ደግሞ ወገን በወገኑ ላይ ያደርጋል ተብሎ የማይገመት እጅግ ዘግናኝና አሳፋሪ ወንጀሎች ተፈፅመዋል።የሚገርመው ደግሞ ያ ሁሉ ግፍ ሌትና ቀን ይደርስ የነበረው ሰዎች ወንጀል ስለሰሩ ሳይሆን አማራ ወይም ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ነው።
ማዕከላዊን ሙዚየም ማድረግ ከታቀደ ሙዚየም ውስጥ የሚቀመጡትን ቅርሶችም ምን መሆን እንዳለባቸው በደንብ ሊጤንበት ይገባል።
እንደእኔ እንደእኔ…..
ማሰቃያ ብረት ፣መስቀያ ገመዶች ፣ጥርስ መንቀያና ጥፍር መንቀያ ጉጠቶች ፣ስለቶች ፣መግረፊያ ጎማዎች ፣ኤሌክትሪክ ገመዶች ፣ ሽንት ማጠራቀሚያ ጀሪካኖች ፣ቀዝቃዛ ውሃ ማጠራቀሚያ በርሜሎች ፣ የፕላስቲክ ውሃ መያዣዎች ፣የአረመኔዎች ፎቶዎች ፣የጥቃት ሰለባ ፎቶግራፎች ፣የስቃይ አይነቶች ፣የቶርቸር ፎቶዎች ፣የአስገድዶና የቡድን ደፋሪዎች ታሪክና ፎቶዎች ወዘተ ታሳቢ መደረግ አለባቸው።
እናም እራሱ ከእስር ያልወጣው ተጠቅላይ ሚኒስትር ዘጠኝ ጊዜ ተስተካክሎ ያነበበው መግለጫ ስላቅ ከመፍጠር ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም።
እስረኞች የሚፈቱት በአጋሚዶዎች መልካምነት የተነሳ ሳይሆን በህዝባዊ ትግሉ መፋፋም የተነሳ ነው።ይህ ትግል ደግሞ በምንም መልኩ አይቀለበስም።ስርዓቱን መቀመቅ ሳይከት አይቀለበስም።
ፍትህ ለንፁሃን …..ድል ለግፉዓን !!!
ውድቀት ለእርኩሳን !!!!