>
5:21 pm - Saturday July 21, 3066

ሰዓሊተ ምህረት ቤ/ክ በአጋዚ ሲታመስ ዉሏል። በጉርድ ሾላ ተገኝቼ እንደታዘብኩት (ሰልማን መሀመድ)

 ዛሬ በአከባቢዉ ተገኝቼ ለማጣራት እንደሞከርኩት ሰዓሊተ ምህረት ቤተ-ክርስትያን አካባቢ ወታደሮች አስለቃሽ ጭስና ጥይት መጠቀማቸው ለማረጋገጥ ችያለሁ የፌዴራል ፖሊስ አካቢበውን ቁጥጥር እንዳደረገ ለማየት ችያለሁ።
በጠዋት የደረሰው ልዩው የአግአዚ የወታደር የቤተክርስቲያኒቱ ዙሪያ አጥሯን ከቦ ያረፈደ ሲሆን አማኞችም የወያኔ ተላላኪ የሆነዉን የቤተክርስትያኒቱን ሰበካ ጉባዔ በመቃወም ሰልፍ ወጥተዋል።
ምዕመናኑ ትግራዋዩ ቅዱስ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ሌላኛዉ ትግራዋዩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ አይተ ጎይቶም እንዲሁም ዘራፊ አስተዳዳሪዎቿ ‘ሰበካ ጉባዔው የቤተክርስትያኒቱን ገንዘብ ያለአግባብ እየዘረፈ ነዉ’ በማለት ሲወቅሱ ተሰምተዋል። 
ህዝቡ ከአጋዚዎች መጋጨቱን  አካባቢው ብዛት ባለው ህዝብና መሳሪያ በታጠቁ ሃይሎች ተሞልቷል። በተለይ አዛውንቶች በቀጥታ ከአጋዚ ወታደሮች ጋር መጋጨታቸው ይነገራል ምክን ያቱ ደግሞ ከልጆቻችን በፊት እኛን ጨርሱን በሚል መሆኑ ይነገራል። ችግሮችን በሰላም መፍታት የማይችለው ህወሃት ፊቱን ወደ ሃይማኖት ተቋማት አዙሯል።
ዉጥረቱ የተነሳዉ አንዲት የእምነቱ ተከታይ የሰበካ ጉባዔው አስተዳዳሪ በማምለጥ ምዕመናን ወደ ቤተክርስትያኗ እንዲሰባሰቡ ደወል ሲደወል እንደነበር ለማወቅ ችያለሁ። የአከባቢዉ ወጣቶች እንደነገሩኝ ምዕመኗ ደዉሉን ሲደዉሉ የፌዴራል ፖሊስ ደወሉን ለማስቆም ሞክሮ ነበር።
አስከትለዉም “ቤተ-ክርስትያን የአምልኮና የፀሎት ሥፍራ እንጂ የመዝናኛና የቅንጦት ቦታ አይደለችም!” እንዲሁም “ቤተ-ክርስትያን የህዝብ እንጂ የግለሰብ ወይም የመንግስት አይደለችም” የሚሉ መፈክሮችን
ይዘው ነበር ሰልፍ የወጡት።
ተቃዉሞ የወጣ የእምነቱ ተከታዮችም “ቤተ-ክርስትያን በልማት ስም የግለሰቦች መጠቀሚያ አትሆንም”፤ “ባልመረጥነው ሰበካ ጉባዔ ቤተ-ክርስትያን አትመራም” የሚሉ መፈክሮችም ተስተውለዋል።
ወያኔ በእስልምና እምነት ላይ ያደረገዉን ጣልቃ ገብነት በኦርቶዶክስ እምነት ላይም አጠናክሮ ቀጥሎበታል።
.
ሃይማኖታዊ ነፃነት ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን !!!
ወያኔ ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እጁን ያንሳ !!!

.
Filed in: Amharic