>

በሶስት ምክንያቶች ደርግና ህወሀት በማዕከላዊ  ለንጽጽርም የሚበቁ አይደሉም (መሳይ መኮንን) 

ብዙ ጊዜ ሃይለማርያም ሲናገር ያዝናናኛል። በሱ ንግግር ከመዝናናት ባለፈ የተናደድኩበት ጊዜ ስለመኖሩ አላስታውስም። ባለፈው ረቡ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ሃይለማሪያም አናደደኝ። ”በደርግ ጊዜ የሰው ልጅ ማሰቃያ የነበረው ማዕከላዊ……” ብሎ ሲጀምር ትኩር ብዬ አየሁት። አይኑ እንኳን አይርገበገብም። እኔ ግን በንዴት ቦግ አልኩኝ። እንዳልኩትም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የትኛውም የህወሀት ዲስኩር፡ በሃይለማርያም አንደበት ሲመጣ ቶምና ጄሪን እንደማየት በፈገግታ አልፈዋለሁ። የረቡ ዕለቱ ግን ከውስጥ ጠቅ የሚያደርግ ንዴት ሰውነቴን ነዘረኝ። ደግሜ ደጋግሜ አየሁት። በደጋገምኩት ቁጥር የማይበርድ ንዴት ይንጠኛል። ለምን ይሆን?

ከማዕከላዊ የሰማናቸው የቶርቸር አሰቃቂ ዜናዎች፡ ስቃዮች፡ የጣር ድምጾች ከጆሮአችን ጓዳ ሳይወጡ ሃይለማርያም ስለደርግ ዘመን ሲያወራ መስማት በእርግጥም ያማል:: ከደርግም በከፋ መልኩ በዘር ማንነታቸው እየተዘለፉ፡ ብልታቸው የተኮላሸ፡ ጥፍሮቻቸው በጉጠት የተነቀሉ፡ ጡታቸው በኤሌክትሪክ ሽቦ የተተለተሉ፡ በርበሬ ታጥነው፡ የገማ ጨርቅ በአፋቸው ተወትፎ ወፌላላ ተዘቅዝቀው የተገረፉ፡ በእግራቸው ተራምደው ገብተው በቃሬዛ አስክሬናቸው የወጣ፡ የስንቱን ወጣት ስቃይና መከራ እየሰማን ሀዘን ልባችንን ወግቶት ባለበት በዚህ ወቅት ”ማዕከላዊ በህወሀት ዘመን ኩሪፍቱ ሎጅ ነው” ማለት የቀረውን የሃይለማርያምን ደረቅ ውሸት ከመስማት በላይ ምን ቅጣት አለ? ሃይለማርያም ከአራት ኪሎ ቤተመንግስት ሆኖ ”ማዕከላዊ በደርግ ዘመን….” እያለ ሲያላዝን በአንድ ኪሎሜትር ርቀት አራዳ ፒያሳ ከሚገኘው ማዕከላዊ የኢትዮጳያ ልጆች በህወሀት ገራፊዎች ቶርቸር እየተደረጉ ነበሩ።

ደርግና ህወሀት በማዕከላዊ ለንጽጽርም የሚበቁ አይደሉም። በሶስት ምክንያቶች። አንደኛው ከዘመን አንጻር ነው። ሁሌም ዛሬ ከትላንት ይሻላል። ነገ ደግሞ ከዛሬ። የሰብዓዊ መብት፡ ዲሞክራሲ፡ እኩልነት፡ ፍትህና ነጻነት ዓለምን እየዋጁ፡ የበላይነትን ይዘው የሀገራት የዕድገት መለኪያ በሆኑበት ዘመን የተፈጠረው ህወሀት ከትላንቱ ደርግ ጋር በአንድ ሚዛን መቀመጥ አይገባውም። ሁለተኛው ምክንያት ደርግ ማዕከላዊን በማሰቃያነት የተጠቀመው ለጥቂት ዓመታት ብቻ ነው። የቀይ ሽብር ዘመን ካበቃ በኋላ በማዕከላዊ ቶርቸር የሚፈጸም መሆኑን የሚገልጽ መረጃ ላገኝ አልቻልኩም። እናም ከ17 ዓመቱ የደርግ የስልጣን ጊዜ ማዕከላዊ በማሰቃያነቱ የዘለቀው ከአምስት አመታት በላይ አይሆንም። ህወሀት እነሆ ለ27ዓመታት ማዕከላዊን የኢትዮጵያውያን የስቃይ ማዕከል አድርጎ በመጠቀም የእድሜውን ያህል ቆይቷል።

ሶስተኛው ምክንያት በደርግ ዘመን ገራፊዎቹ ወይም ገዳዮቹ ከአንድ ብሄር የተወለዱ አይደሉም። ስቃይ የሚደርስባቸው ኢትዮጵያውያንም በዘር ማንነታቸው ተሰፍረው አልነበረም። የሚገርፉትም የሚገረፉትም ኢትዮጵያውን ነበሩ። በህወሀት ጊዜ ገራፊዎቹና ገዳዮቹ ከአንድ ወገን፡ ስቃይና መከራን የሚቀምሱት ደግሞ በዘር ማንነታቸው በህወሀት መዝገብ ”ጠላት” የተደረጉ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ነው። ሀብታሙ አያሌው እንደነገረን ”ትግርኛ ቋንቋ በሰማሁ ቁጥር የማዕከላዊ ስቃይ እየተመላለሰ ያስጨንቀኛል።” ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙ እንዳጫወትችንም ”መቀሌ እስር ቤት ያለሁ ነው የመሰለኝ።” ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እንደሚለውም ”ማዕከላዊ የህወሀት የምርኮ ቦታ እስኪመስል ገራፊ ከትግራይ የተሰባሰቡበት ቦታ’

ለማንኛውም ሃይለማርያም ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ አናዶኛል። ከዚህ በላይ ምንም ቢናገር የሚያናድድኝ አይመስለኝም። በተረፈ ህወሀት ማዕከላዊን የመዝጋት ሞራል የለውም። ህንጻ ቢዘጋ ምን ትርጉም አለው? ከማዕከላዊ የከፉ ስንት ስውር የማሰቃያ ቦታዎች እንዳሉ እናውቃለን። በሀሽሽ በጦዙ፡ በአልኮል በናወዙ፡ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በደረቀባቸው ነውረኛ የትግራይ ደህንነቶች በየስውር ማሰቃያ ቤቱ እየተፈጸሙ ያሉትን ግፎች ሂሳብ የምናወራርድበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም። የማዕከላዊ የስቃይ ዘመን የሚያከትመው በህወሀት መቃብር ላይ ነው።

Filed in: Amharic