>

ማሰር እንጂ መፍታት በወያኔ አጥንት ውስጥ የታለ? (ሃራ አብዲ)

ማእከላዊ ወንጀል ምርመራን ለመዝጋት ማወጅ፤ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ላይ፣ የቁም እስር ማወጅ፤ከመጀመሪያው ይልቅ ሁለተኛው ወያኔ ፣ ወያኔ ይሸታል። ይህ የጥንብ አንሳ ቡድን፤ ስብእና ከመቀማት ሌላ ምን ያዉቃል!!!

እንዲህም አድርጎ ለሀገር መፍትሄ የለም! የወያኔ ማፍያዎች ሌሎቹን ድርጅቶች በሸሚዛቸው ኮሌታ አንቀው፤ ለ18 ቀናት በጠረጴዛ ዙሪያ ከኮለኮሉአቸው በሁዋላ፤ለሀገር መፍትሄ አመጣን ሲሉ መግለጫ አወጡ። መግለጫው ካብ አይገባ ድንጋይ ሆኖ ህዝብ ከግራም ከቀኝም እያነሳ ሲወረውረዉ፤ደርግ በዜጎች ላይ ስቃይ ሲፈጽምበት የኖረዉን የማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ዘግተን፣ ሙዚየም
እናደርገዋለን፣ ሲሉ ከኪሳቸዉ ድንገት ውልቅ አድርገው አወሩ። (መንግስታት አዋጅ ሲያውጁ ሰምተዋል አይደል?) ቀናት ሳይቆጠሩ፤የኦሮምያ ርእሰ መስተዳድርና የኦህዲድ ሊቀመንበር የሆኑትን አቶ ለማ መገርሳን
ፓስፖርታቸዉን ነጥቀው፤ ከሰው እናዳይገናኙ አድርገው የቁም እስረኛ አደረጉአቸዉ።
እኛ የምንልህን ካላደረግህ፤ በራስህም፤ በልጆችህም፤ ላይ ሳይቀር እርምጃ እንወስዳለን ብለው በማስፈራራት፤ ወያኔዎች፣ መግለጫ እንዲሰጥ አድርገዉታል። ይህን አሳዛኛ ክስተት ዛሬ ምሽት ከግዮን ሚዲያ ላይ በተደረገ ቃለምልልስ ስሰማ፤ ክፉኛ ልቤ ቆሰለ።

አላስ!!! እነዝያ የእርያ ስጋዎች፤ እነዚያ ታጥቦ ጭቃዎች፤ በራሳቸው አንደበት እንዳሉት፤ እነዚያ
የበሰበሱ ፤ወትሮስ፤ እነሱን ብሎ ገዢ ፓርቲ፤ እነሱን ብሎ ሀገር መሪ! ኢትዮጵያ፤ በዚህ መጠን ወድቃ፤ የተዋረደችበት፤ዘመን አለ ሲባል አልሰማሁም!! ግን፤ ይህ ዘመነ- ፍዳ በሀገራችን ላይ መድረሱ እውነት መሆኑ ካልቀረ፤ ካለነዚህ የትውልድ አራሙቻዎች፤ ቅቅታሞች፤ ችጋራሞችና ምቀኞች በስተቀር በማን ሊደርስብን ይችላል?? ከእነሱ ትንሽ የተሻለ ስእብና ያላቸው ሰዎች ቢሆኑ፤እንዲህ ረክሰው፤ ሀገራችንን አያረክሱም ነበር። ወግ አልቀረባቸዉም! ማእከላዊን ዘግተን ሙዚየም እናደርጋለን ሲሉ፤ አያፍሩም። ማእከላዊን ዘግተዉ፤ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን የቁም እስረኛ ሲያደርጉለት የኢትዮጵያ ህዝብ እልል ይላል ብለው ይጠብቁ ይሆን?
ለነገሩ፤ ደርግ ሰቆቃ ሲፈጽምበት የነበረውን ሲሉ፤ ገረሞኝ ነበር። አሁንስ ሌት ከቀን በህዝባችን ላይ
ሰቆቃ ከሚፈጽሙባቸዉ እስር ቤቶች መሀከል ማእከላዊ ዋናው አይደለም እንዴ በማለት ተደምሜ
ነበር። ለካስ እንዘጋለን የሚሉት የደርግን እንጂ እነሱ ሰቆቃ የሚፈጽሙበትን የእስር ቤት አይነት ገናም
በመክፈት ላይ ናቸዉ። ሌቦች፤ ነፍሰ-በላዎች!!
እንዴት፤ እንዲህ ይደድባሉ? ወያኔዎች ማንን ለማዘናጋት ነው፣ የማእከላዊን ወደ ሙዚየምነት መቀየር እያወሩ በጎን ደግሞ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን በቁም እስር ላይ የሚያግቱ? ደግሞ፤ ልጆቹን ሳይቀር፤ በነፍሰ-ገዳዮቻቸዉ የሚያስፈራሩት? ወያኔዎች ስሙ! የፕሬዚዳንት ለማን መግለጫ ስመለከት፤ ልክ ያልሆነ ነገር እንዳለ፤ተገንዝቤአለሁ። እርግጠኛ ነኝ፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝባችን ወያኔ፤ ወያኔ የሚሸት መግለጫ ከጀግናዉ ለማ መገርሳ አንደበት ሲወጣ ሰምቶአል። ጎሽ ለልጅዋ ስትል ተወጋች እንዲሉ።

እናንት የደደቢት ደደቦች፤ ለማ የተናገረዉ መግለጫ፤ የአንድ ሰባራ ሳንቲም ታህል የፖለቲካ ትርፍ
አያስገኘላችሁም። ልጆቹን እያዋከባችሁ፤ፓስፖርቱን ነጥቃችሁ፤ ከሰዉ እንዳይገናኝ አግዳችሁ በቤቱ
አስቀምጣችሁ 24 ሰአት ዙሪያዉን ከባችሁ፤ እንዲሰጥ ያደረጋችሁት መግለጫ፤ ማእከላዊ አስራችሁ፤ገርፋችሁ፤ በዝረራ ጥላችሁ ቃላቸዉን ሰጡ ፤ከምትሉት የፖለቲካ እስረኞች ቃል የተለየ አይደለም!!!! በዚህ አይነት  ማእከላዊን እናንተ አትዘጉም። ጀግናዉ ህዝባችን፤ እናንተን ከውስጥ ቆልፎ፤ ለአንዴና ለመጨረሻ  ጊዜ፤ማእከላዊን ይዘጋል። ጊዜዉም ፤ ፈጽሞ ሩቅ አይሆንም። ህወሃት፤ የዘመናችን መርገምት፤ ከእንግዲህ፤ አቶ ለማ ሌላዉ ቀርቶ እናንተን እያገነነ እንኩዋን መግለጫ ቢሰጥ፤ ዉርደቱ የእናንተ ነዉ። ለማ መገርሳ በተፈጥሮ በታደለዉ ግርማ ሞገሱ የናንተን ውርደት ሳያውቀዉ  አሳብቆአል። የለማ ስእብና ከመግለጫዉ ጋር ሊጣበቅ አልቻለምና።
ለማ መገርሳን ልታስሩ፤ ልታሰቃዩ፤ እንዳላችሁት፤ ልጆቹን ሳይቀር፤ ልትቀጥፉ ወደሁዋላ እንደማትሉ፤ እናዉቃለን፤ ድርጊታችሁን በቅርብ ፤እግር በእግር ከመከታተል አንቦዝንም። ግን በጣም ረፍዶባችሁአል።  ከእንግዲህ ለማ የሀገር ፈርጥ ነው! የኢትዮጵያ የአይንዋ ብሌን። የህዝብዋ ዝማሬ ነው፤ የአንድነትዋ መልህቅ።
ለማ ፤ገፍታችሁ፤ ገፍታችሁ፤ በኢትዮጵያ ህዝብ እቅፍ ላይ የጣላችሁት ጀግና ነዉ። ጻዲቅ ሲሞት
መንግስተ- ሰማይ ይገባል፤ ለማ፤ ጠላቶቹ ቀድመዉ ይርገፉ እንጂ፤ ሳይሞት መንግስተ- ሰማይ የገባ ነዉ።
ለሰዉ ልጅ አንድ ጊዜ መሞት ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት ለፍርድ መቅረብ የተገባ ነዉ እንደሚል
መጽሁፍ ቅዱስ፤ ለጀግና ደግሞ፤ አንድ ጊዜ ታሪክ መስራት፤ ከዚያም በመጭዉ ዘመናት፤ለትውልዱ
መልካም የታሪክ አሻራ አኑሮ ሲወደስ መኖር የተገባ ነው። (That is going to be Lema Magaressa’s destiniy) የጣእር ቀናችሁ ፤ እየተቆጠረ ላለዉ፤ ለእናንተና ለወገኖቻችሁ፤ ወዮላችሁ።
ይልቁን፤ ህክምና ነበረዉ,,, ጀርመን ሀገር ምናምን ሲባል ነበር። አንድም ዶክተር፤ ምንም መድሀኒት
እንዳይሰጠዉ፤ ቤተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት። እናት ሀገሩ ከተያዘችበት የአፓርታይድ በሽታ
በላይ ለማን የሚያመዉ የለም። እናንተ ነፍሰ-ገዳይ ወያኔዎች፤ የመርዝ መርፊያችሁን ፤አርጅተዉና
ጃጅተዉ በዉሻ እድሜ ለሚኖሩት፤ ለነ ስብሀት ነጋ እና ለነሳሞራ የኑስ ስጡአቸዉ።የተረፈዉን ለጌታቸዉ
አሰፋ ጨመር አድርጋችሁ ስጡት። ይህ አሮጌ ጅብ፤ ልጆቹ ልእልቲ ጌታችዉ አሰፋና ማርያማዊት ጌታቸዉ
አሰፋ የት ነዉ በዉድ ዋጋ፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ ይማራሉ፤ ያሉት? እንግሊዝ ሀገር? የለማ መገርሳን
ልጆች ጫፋቸዉን ንኩና ከዚያ ወዲያ፤ የነ ልእልቲን፤ ደህንነት ትጠይቃላችሁ!! እዚያም ቤት እሳት አለ
እንዳሉት አለቃ ገብረሃና።
ለማንኛዉም፤ ማእከላዊን እንዘጋለን፤ የፖለቲካ እስረኞች እንፈታለን ብላችሁአል። መላዉ ኢትዮጵያዊና
መላዉ አለም አፍጥጦ እያያችሁ ነዉ። መቸም ማሰር እንጂ መፍታት በአጥንታችሁ ውስጥ የለም፤ ውድ
የኢትዮጵያን ልጆች ያለምንም ቅድመ- ሁኔታ ፍቱ፤ የኦሮምያዉን ርእሰ-መስተዳድር፣ የኢትዮጵያን
ብርቅ ልጅ፣ ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳን ነጻነቱን አትገድቡ። ለራሳችሁም፤ ለወገኖቻችሁም ደህንነት ስትሉ፤
በለማ መገርሳ ላይ አንዳች ክፉ ነገር ከማድረግ ታቀቡ።

Filed in: Amharic