>

"ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!"ማለት ወንጀል ነው የሚለው የትኛው የተጻፈ ሕግ ነው?

 

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው 

ሬ አቶ ገዱና የወልዲያ ከተማ የጸጥታ ኃላፊ በብዙኃን መገናኛቸው ቀርበው ከ32 ሰው በላይ ለፈጁበት የግፍ እርምጃቸው የጭፍጨፋቸውን ምክንያት በደፈናው “ወጣቶቹ በጭፈራ በጸጥታ ኃይል ላይ ትንኮሳ ስላደረጉ ነው!” ብለዋል፡፡ እነሱ በደፈናው የተናገሩትን ሁሌም እንዲህ ዓይነት ችግር በተፈጠረ ቁጥር “ወጣቶቹ አምነውልኛል!” እያለ ለወያኔ ምስክር እየሆነ የሚቀርበው ቅጥረኛ የመኢአድ ዋና ጸሐፊ የተባለ አቶ አዳነ ጥላሁን ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው አገልግሎት ሲገልጽ “ወጣቶቹ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ ብለው በመጨፈራቸው ነው!” ሲል ተናግሯል፡፡

እሽ ለመሆኑ “ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!” ብሎ መጨፈርን ወንጀል ነው ያለው የትኛው የተጻፈ ሕግ ነው??? መሣሪያ አንሥተው በጸጥታ ኃይል ላይ እየተኮሱ ነው ወይ “ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!” እያሉ የጨፈሩት??? እንዳልሆነ አገር ያውቃል፡፡ በዚያውስ ላይ ወንጀል ባይሆንም እንኳ ወንጀል ነው ካሉም እንዲህ አሉ ያሏቸውን ወገኖች በአግባቡ መብታቸው ተጠብቆ ጫፋቸው ሳይነካ ሕግ ፊት ማቅረብ እንጅ ስንጥር እንኳ ያላነሡ ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑ እንዲገድሉ፣ እንዳሻቸው እንዲጨፈጭፉ የትኛው ሕግ ነው መብት የሰጣቸው??? ይሄ አቶ ገዱና የጸጥታ ኃላፊው “ትንኮሳ ተፈጽሟል!” ብለው የሰጡት ምክንያት ዛሬ ብቻ አይደለም ግፈኛ የጸጥታ ኃይሎቻቸውን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት ሁሌም የሚሰጡት ወይም የሚጠቅሱት ተልካሻ ምክንያት እንደሆነ ሁላቹህም የምታውቁት ነው፡፡

እንኳንና ይለያል ዘንድሮ ማለት “ወያኔ ይውደም!” ማለት እንኳ ቢሆን በሕግ ፊት ወንጀል አይደለም፡፡ ይሄንን ማለት የዜጎች ፖለቲካዊ (እምነተ አሥተዳደራዊ) መብት ነው፡፡ “ወያኔ ይውደም!” ማለትን ወንጀል የሚያደርገው ወያኔ ይውደም የምለው ሰው ወያኔን ለማውደም የምጠቀምበት መንገድ ነው፡፡ ያው እንደምታውቁት ሁለት ዓይነት መንገድ ወይም አማራጭ ነው ያለው ሰላማዊ እና የኃይል አማራጮች፡፡

እንዲያው ነገሩን አልኳቹህ እንጅ ወያኔን ለማውደም ወይም ለመክላት ሁለተኛውን ወይም የኃይል አማራጩን ብንጠቀም እንኳ ወንጀልነቱ ለወያኔ ነው እንጅ ለሕግ ወይም ለፍትሕ አይሆንም፡፡ በፍጹም! ምክንያቱም ለ27 ዓመታት እንዳያቹህት ወያኔ ፈጽሞ በሰላማዊ አማራጭ ሥልጣን ለማስረከብ ወይም ለመልቀቅ የሚፈቅድ ኃይል ባለመሆኑና በዜጎችና በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት፣ ጥፋት፣ አደጋ ያደረሰና እያደረሰ ያለ አንባገነን የጥፋት ኃይል በመሆኑ የትኛውንም አማራጭ በመጠቀም ሀገርንና ሕዝብን ከእንዲህ ዓይነቱን አንባገነናዊ የጥፋት ኃይል መገላገል ማላቀቅ የዜጎች የዜግነት ግዴታና ኃላፊነት በመሆኑ ነው፡፡

ሌላው የገረመኝ ነገር ሁሌም አንድ ነገር በተፈጠረ ቁጥር እነ አቶ ገዱን ወይም ብአዴንን ተቆርቋሪ አስመስለው ማቅረብ ቋሚ ሥራቸው የሆኑ የወያኔ ካድሬዎችን ወሬ አንዳንድ የዋሃን ወገኖቻችን እየያዙ አሁን ደግሞ “አቶ ገዱ አለቀሰ፣ የአግአዚ ኃይል ወልድያን ለቆ እንዲወጣ ትዕዛዝ ሰጠ!” እያለ መጃጃላቸው ነው የሚገርመኝ፡፡ እባካቹህን መጃጃሉን ትተን ቆፍጠን እንበል? ገዱ ነው ለአማራ የሚያለቅሰው? የአማራን ጥቅም ከሕግ ውጭ ወይም ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ በግል ውሳኔው ለትግሬ አሳልፎ የሚሰጠው፣ የአምናውን የባሕርዳሩን ጭፍጨፋ “የጸጥታ ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ ትዕዛዝ የሰጠሁት እኔ ነኝ!” ብሎ በይፋ በብዙኃን መገናኛ የተናገረው፣ ሌት ተቀን ለትግሬ ጥቅም ታጥቆ የሚሠራው የወያኔ ባሪያ ነው ወይ ለአማራ የሚያለቅሰው??? መቸ ነው ግን የምትበስሉት? ገዱ ለአማራ ተቆርቋሪ ሆኖ ምን አተረፈልህ? ከምንስ አስጣለህ? አስጨፈጨፈህ እንጅ!

ይሄው አሁንስ ቢሆን ያን ተልካሻና ሕገወጥ ምክንያቱን ጠቅሶ ግፈኛ የአግአዚ ጨፍጫፊዎችን ከተጠያቂነት ነጻ ለማውጣት ጣረ እንጅ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠየቀ ወይ? ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ገለጸ ወይ? እናም እባካቹህ? እባካቹህ? ከወያኔ ግፍ ይልቅ የሚያመኝ ነገር ቢኖር ይሄ እነገዱን ወይም ብአዴንን ለአማራ ሕዝብ የቆሙና ተቆርቋሪ ተደርገው የሚነገረው ነገር ነው፡፡ ማሰብ የተሳነን ካልሆንን በስተቀር የፊትና ኋላን፣ የግራና የቀኙን ቃኝተን አማትረን ማሰብ ማንሰላሰል የምንችል ከሆንን እንዴት ሆኖ ነው እነ ገዱን ወይም ብአዴንን የአማራ ተቆርቋሪ አድርገን ልናስብ የምንችለው? ይሄ ጤነኝነት አይደለም!

ሌላው ደግሞ እራሳችንን ከግፈኞችና ከደናቁርቱ የትግሮች ጥቃት ለመከላከል ስንል በምንወስደው ተመጣጣኝ መሆን ያልቻለ ሕጋዊ ራስን የመከላከል እርምጃ ትግሬ በተነካ ቁጥር ሁሌም በየግልና በቤተክርስቲያን ስም እየወጣቹህ እሪ ሀገር ይያዝልን! የምትሉ፣ የምትንጫጩ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንጋው እረኞች ነን የምትሉ ምንደኞች፣ ቅጥረኞች ሆይ! እያልኩ ያለሁት አማራና ትግሬ ያልሆኑትን ነው እንጅ እነ አቦይ ማትያስና ሌሎች ትግሬ የውሸት የወያኔ ካህናትማ ተጋዳላይ ናቸውና ከነሱ ምንም ልጠብቅ አልችልም፡፡ የሚጠበቅባቸውን አሳምረው ሲሠሩ ቆይተዋል እየሠሩም ይገኛሉ እኔ እያልኩ ያለሁት ከትግሬ ውጭ ያሉ በተለይ አማራ የሆኑ አባቶች፣ እረኞች፣ ካህናት ነን ባዮችን ነው “በእውነት መድኃኔዓለም ክርስቶስ እናንተንም እኛንም ከነጻነቱ ቀን አድርሶን ያገናኘን!” ከማለት ውጭ ምን ብላቹህ በእናንተ ላይ ያለብንን የሚያቃጥል፣ የሚያንገበግብ ቅሬታ ሊገልጽልን አይችልምና ዝም እላለሁ፡፡ ብቻ በዚያች ቀን ያገናኘን!

በሌላ ቦታ እንኳ በሆነ የሃይማኖቱን ግዴታ ለመወጣት ሲል የቃልኪዳኑን ታቦት አጅቦ እየሸኘ በእጃቹህ ያለ ሕዝብ ተልካሻና ሕጋዊ ያልሆነ ምክንያት ተጠቅሶ ሲጨፈጨፍ ዝም ጭጭ ያላቹህ እናንተ ምናቹህ ነው እረኛ፣ ምናቹህ ነው የመንጋው ጠባቂ አባትነታቹህ??? ምድረ አተላ ሁላ ስለ ክርስቶስ ብለን ተውነው፣ ጣልነው፣ ለዓለም እንደሞተ ሰው ነን ላላቹህት ተድላ ደስታቹህ ብላቹህ የዚህን ያህል እራሳቹህን ካዋረዳቹህ፣ አደራቹህን ከበላቹህ ሌላው ሁሉ ቀርቶ በእግዚአብሔር መኖርስ ታምናላቹህ ወይ??? ብታምኑ ኖሮማ እምነታቹህ ትከተላቹህ አልነበረም ወይ? እምነታቹህ በምግባር ይገለጥ አልነበረም ወይ??? ምድረ አተላ ሁላ ዝም ብለህ እያጭበረበርክ፣ እያስመሰልክ፣ እየደለልክ ብላ!!!

ለወገን መናገር የምፈልገው መልእክት ቢኖር ወገን ሆይ! ትግላችንን መልክ እናስይዘው! ስልታዊም ይሁን! የተያያዝነው የነጻነት ትግል ነው፡፡ ይሄንን ትግል በተደራጀ መልኩ መምራትና መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎችን በተጠናና ስልታዊ በሆነ መልኩ መውሰድ ካልቻልን፣ መሣሪያ የታጠቀን ማሰብ ማገናዘብ የማይችል እንስሳ የአጋዚ ሠራዊትን በባዶ እጅ ግንባራችንን ሰጥተን ከተጋፈጥን የምናጣው፣ የምናባክነው፣ የምንጎዳው ነገር ይበዛል፡፡ ትግላችንም ዳር መድረስ ይሳነዋል፡፡ ይሄ እንዳይሆን በምሥጢር እንጀራጅና ትግላችንን እናፏፉም!!! እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሁን!!!

ድል ለአማራ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

Filed in: Amharic