>

ለመስማትም ሆነ ለማውራት የሚዘገንነው የትግራይ ወታደሮች በአማራ ላይ የፈጸሙት ግፍ! (አቻምየለህ ታምሩ)

“አንገቱ ላይ፣ ደረቱ ላይ፣ ሆዱ ላይ እና ብልቱ ላይ አምስት ጊዜ በጥይት የተመታ እና በደም የተሸፈነውን የወንድሜን አስከሬን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁ”

***
“ማመን ነው ያቀተኝ። ወንድሜ ላይ ግፍ ነው የተፈጸመው። ገብረመስቀል አንድ ጥይት የሚበቃው ልጅ ነበር። የቤተሰቡን አንጀት ነው የቆረጡት። እናቱን ወዳጅ፤ አባቱን አክባሪ ነበር። እሱን ብቻ ሳይሆን ቤተሰቡን ነው የገደሉት። የአምስት ዓመት ሴት ልጅ አለችው አሁን የተፈጠረውን ነገር መቀበል አልቻለችም”

ገብረመስቀል ታቦት ሸኝቶ ሲመለስ መብራት ኃይል አካባቢ በነበረበት ወቅት ምንም አይነተ ረብሻ አልነበረም። ”ለምን መግደል እንዳስፈለጋቸው አላውቅም። ይህን ስላደረገ ነው የተገደለው የሚለን እንኳ አላገኘንም” ይላል።

ከአንድ ወር በፊት ሌላ ታናሽ ወንድማቸውን በህመም እንዳጡ… ”በሃዘን ላይ መሪር ሃዘን ነው የጨመሩብን” ሲል ይናገራል። ”የታናሽ ወንድማችንን 40 ቀን እንኳን ሳናወጣ ነው ሃዘን ላይ እያለን ሃዘን የተጨመረብን” ብሏል።

“እሁድ ዕለትም ጸጥታ አስከባሪዎች የቀብር በሥርዓቱ እንዳንፈጽም እክል ሲፈጥሩብን ነበር የሚለው ኪዳኔ ”አስክሬኑ ቅዳሜ ምሽት ወልዲያ ኪዳነምህረት ቤተ-ክርስቲያን ፍትሃት ሲደረግበት አደረ፤ ከዚያም ከኪዳነምህረት አውጥተን ለቀብር ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ስናመራ፤ መከላከያዎች እና አድማ በታኞች ጥይት እና አስለቃሽ ጪስ በመተኮስ ለቀብር የመጣን ህዝብ ሲበትኑ ነበር”

Filed in: Amharic