>
7:31 am - Friday October 22, 2021

የዱላ ቅብብሉ ፍሬ እያፈራ ነው!! (ደረጀ ገረፋ ቱሉ)

– በቅብብሉ የተሳተፈ ሁሉ ደስ ሊለው ይገባል።

ትላንትና ለዶር መረራ የተደረገው አቀባበል የኦሮሞ ህዝብ የረጅም ጊዜ ትግል ፍሬ ማፍራቱን ያሳያል። ይህንን ፍሬ ህዝቡ በትላንትናው እለት ለዶር መረራ ቢያቀርብም ፍሬው ለዚህ እንዲበቃ የኦሮሞ ህዝብ ላለፉት 50 ዓመታት ያለመታከት ያደረገው ትግል የታየበት መድረክ ነው።
አንዳንዶቹን ለማየት
1 በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ የመጫ እና ቱለማ ማህበር እና አመራሩ የኦሮሞን ህዝብ መብት ለማስከበር የጣሉት መሰረት ለትላንትናው የአምቦ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ዶር መረራን መቀበል ድርሻው ጉልህ ነው።
2 በ1970ዎቹ እና 1980ዎቹ ኦነግ እና አመራሩ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ከፍ እንዲል እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ የመብት ትግል በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ ያደረገው አስታዋፅኦ ለአምቦ እና አከባቢው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ለዶር መረራ የሞቀ አቀባበል ማድረግ ድርሻው ጉልህ ነው።
3 በለፉት ሶስት ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ ላደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የዶር መረራ ፓርቲ(OFC) ፣ብዙ አንጋፋና ወጣት ኦሮሞዎች ፣በፊት ለፊት ባይሆንም ኦህዲድ እራሱ ፣እና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች ያበረከቱት ድርሻ ጉልህ ነው።
ይህ ያለፉት ሶስት ዓመታት የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ብዙ ታሪካው ክስተቶች እንዲከሰቱ አስገድዷል።
ከነዚህ መካከል በኦህዲድ ውስጥ የተካሄደው ስር ነቀል ለውጥ እና የነ ለማ ቡድን የኦህዲድን እና የኦሮሚያን ክልል ስልጣን መቆጣጠር ዋናው ነው።በሌላ መልኩ ዶር መረራን ጨምሮ ሌሎች የOFC መሪዎች እና አባላት ከፍተኛ መሰዋዕትነት ከከፈሉት ውስጥ ናቸው።በአጭሩ በለፈው ከ2006 እስከ 2008 ዓም የኦሮሞ ህዝብ ያደረገውን እንቅስቃሴ ባያደርግ ኖሮ የነ ለማ ወደ ስልጣን መምጣት አይታሰብም ነበር።ለዚህ የ2006 ፣ 2007 እና 2008 እንቅስቃሴ ብዙ ባለድርሻ ቢኖሩትም እንደ ድርጅት የOFC ድርሻ ቀላል አይደለም።በእርግጥ በአንድ ድርጅት ውስጥ ሳይታቀፉ በግላቸው ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ ግለሰቦችን ድርሻ እዚህ ላይ በምንም መልኩ መርሳት አይቻልም።
4 በለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የሆነው ሁሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ያልተለመደ ነው።አዲሱ የለማ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ የአቅሙን ያህል ከኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ውጭ ያፈነገጠበት ጊዜ የለም።
የኦሮሞ ታጋዮችን ከእስር ለቋል።በፌደራል ደረጃ ያሉትን እስረኞች በውስጥም ይሁን በግልፅ እንዲለቀቁ አቋም ይዞ ተከራክሯል።ከተለቀቁም በኃላ ህዝቡ ያለ ምንም ስጋት እና መሸማቀቅ አቀባበል እንዲያደርግላቸው ነገሮችን አመቻችቷል።በለፈው አንድ ዓመት የነ ለማ ኦህዲድ የኦሮሞ ህዝብ ትግል የ1980ዎቹ እጣ ሳይገጥመው እና እድገቱን ሳያቋርጥ እንዲጓዝ አድርገውታል።
ስለዚህ ያለ Oromoprotest የአዲሱን ኦህዲድ አመራር ወደ ስልጣን መምጣት ማሳብ እንዳማይቻል ሁሉ ያለ አዲሱ የኦህዲድ አመራር ትላንትና የአምቦ ህዝብ ለዶር መረራ ያደረገውን አቀባበል ማሰብም አይልቻም።
5 ድርጅት እና መሪ ህዝብን አስተባብረው ለድል ለማብቃት ያላቸው ድርሻ ጉልህ ነው።ድርጅት እና መሪ ህዝቡ ድል ሲያደርግ ዋናጫ የሚያነሱ ምልክቶች ናቸው።ስለዚህ የትላንትናው የሞቀ የዶር መረራ አቀባባል ባለቤቱ መላው የኦሮሞ ህዝብ ነው።ይህንን የኦሮሞ ህዝብ በረጅም የትግል ጉዞው ያመጣውን ዋንጫ ዶር መራራ መቀበል በመቻሉ እድለኛ ነው።ይገባዋልም።
ከላይ እንደገለፅትኩ ይህ ፍሬ በረጅም ጊዜ ህደት የተገኘ ጣፋጭ ፍሬ ነው።ይህንን ፍሬ በበጎ መልኩ እንደ ስንቅ ተጠቅመን ኦሮሚያ ውስጥ እያበበ ያለው ዲሞክራሲ እንዳይረግፍ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል።እየጎሞራ ያለው መደማመጥ እና አንድነት ከዚህም በላይ እንዲበስል የሁሉም ድርሻ ከፍተኛ ነው።ያገኘነውን ይዘን የቀረንን ለማግኘት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከቡድን ፍላጎት እራሱን አርቆ በጥንቃቄ መራመድ አለበት።
6 ለትላንትናው የሞቀ የዶሮ መረራ አቀባበል መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ባለድርሻ ነው።የኦሮሞ ህዝብ ለረጅም ጊዜ በደረገው ትግል ውስጥ ብዙሃኑ ህዝብ ስችል ድጋፍ በመስጠት ካልቻለም እንቅፋት ባለ መሆን ተባብሯል።እውቅናም በመስጠት ትግሉ የደረሰበት እንዲደርስ የራሱን ድርሻ ተወጥቷል።ለዚህ ምስጋና ይገበዋል።አሁንም ኦሮሚያ ውስጥ የታየው መጠነኛ ዲሞክራሲ እና መደማመጥ በሁሉም የሀገራችን ክፍል በፍጥነት እንድስፍፋ ሁላችንም መረባረብ አለብን።

Filed in: Amharic