>

ግንቦት ሰባት ወዴት እየሄደ ነው!? (አቻምየለህ ታምሩ)

ብአዴን የሚባለው የወያኔ ነውረኛ ድርጅት ከቀናት በፊት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫው ሰሜን ወሎ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ሕዝቡ እየወሰደው ባለው ራስ የመከላከል እርምጃ ትግሬዎች በዘራቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ መናገሩን ተከትሎ ሃቁ ምን እንደሚመስል መሬት ላይ እየሆነ ያለውን ማስረጃ በማሰባሰብ እዚህ ፌስቡክ ላይ በማተም ብአዴን ባማራ ሕዝብ ላይ ያካሄደው ውግዘትና የፈጠራ ክስ መሰረት የሌለው እንደሆነ አስረግጠን ነበር።

ሰሜን ወሎ ወያኔ ያካሄደውን ጭፍጨፋ ተከትሎ ሕዝቡ በወሰደው ራስን የመከላከል እርምጃ ጥቃት የደረሰባቸው ሕዝቡን የሚያስገድሉ ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ ባንዳ አማራዎች ጭምር ናቸው። ይህንን ለመረዳት ከሁለት ቀን በፊት ያተምነውን ይህንን ትር በመጫን መመልከት ይቻላል፤ https://www.facebook.com/achamyeleh.tamiru.3/posts/1720331221322153

ንጉሱ ጥላሁን የሚባለው የብአዴን ቃል አቀባይ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ቀርቦ ትግሬዎች [በአማራ] ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ተናግሮ ነበር። ሆኖም ስለደረሰው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠን፣ አይነትና ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥር እንዲገልጽ ሲጠየቅ ግን መረጃው በእጁ እንደሌለና ገና እየተጠናቀረ እንደሆነ ተናግሯል። ይታያችሁ! ደረሰ ስለሚለው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠንና አይነት እንዲሁም ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥርና ዝርዝር እንዲገልጽ ሲጠየቅ በእጁ መረጃ የሌለ ሰው እንዴት ብሎ ነው ትግሬዎች በትግሬነታቸው ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ማወቅ የሚችለውና ትግሬዎች [በአማራ] ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ሊናገር የሚችለው?

በዚህም የተነሳ ነው ደረሰ ስለሚለው ጥቃት፣ተጎዳ ስለሚባለው ንብረት መጠንና አይነት እንዲሁም ስለተጎዱ ሰዎች ቁጥርና ዝርዝር እንዲገልጽ ሲጠየቅ በእጁ መረጃ እንደሌለ የተናገረው ንጉሱ ጥላሁን «ትግሬዎች [በአማራ] ቃት እየተፈጸመባቸው ነው» ሲል የሰጠው መግለጫ አይን ያወጣ ውሸት፣ ነውረኛነትና አለቃውን ወያኔን ለማስደሰት ሲል በትዕዛዝ የሰጠው የሕወሓት መግለጫ ነው ያልነው።

እንግዲህ! በፈጠራ ውሸት መግለጫ አቅራቢነቱ ያወገዝነው ነውረኛው ብአዴን የሰጠውን አይነት መግለጫ በማውጣት ሕዝባችን እያደረገ ባለው ትግል ላይ ተመሳሳይ በደል የሚፈጥሩትን ማንኛውንም አካላት ዝም አንልም።

ግንቦት ሰባት ዛሬ [ከደምሕት ጋር በመሆን] በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ከሕወሓት ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጧል። ይህ ግንቦት ሰባት ያወጣው የነውረኛው ብአዴንና የፋሽስት ወያኔ አይነት የውሸት መግለጫ በውሸትነቱና የሕዝብ ትግልን ጥላሸት በመቀባቱ ልክ እንደ ብአዴንና ሕወሓት መግለጫ ሁሉ በጥብቅ የሚወገዝ የክፋት ተግባር ነው።

በጣም ገራሚው ነገር ግንቦት ሰባት ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ በሚባለው ጸረ ወያኔ ተጋድሎ ሁሉ እኔ አለሁበት እያለ ኃላፊነት ሲወስድ ከርሞ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች እየተጠቁ ነው የሚል ራሱን የሚያወግዝ መግለጫ ይዞ መምጣቱ ነው። ጤና ይስጥልኝ ግንቦት ሰባቶች! ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ የተባለን ጸረ ወያኔ ተግባር ሁሉ የኛ ነው ስትሉ ከርማችሁ ዛሬ
ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ስትሉ የምትከሱት ማንን ነው? ራሳችሁን ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ ተደረገ የተባለን ጸረ ወያኔ ጥቃት ሁሉ እናንተ ስትፈጽሙ ከከረማችሁ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎችም ያጠቃችኋቸው እናንተ ናችሁ ማለት ነው።

ይህ ከሆነ ደግሞ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ተጠቁ ካላችሁ እየተካሄደ ባለው ትግል ጀርባ ሁሉ እናንተ አለን ስለምትሉ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ከተጠቁ ያጠቃችኋቸው እናንተ ናችሁና ተፈጠመ ያላችሁትን ጥቃት የማውገዝ ሞራሉ የላችሁም። ተፈጠመ ያላችሁትን ጥቃት የማውገዝ ሞራሉ የሌላችሁ እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ሁሉ እናንተ እንደነገራችሁን ከጀርባ ስላላችሁ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ትግሬዎች ማጥቃት አልነበረባችሁምና ነው። በሌላ በኩል ግንቦት ሰባት ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች እየተጠቁ ነው ካለና እኔ ጥቃት አላደረስኩባቸውም ካለ ግንቦት ሰባት ሕዝቡ እያደረገ ካለው ትግል ጀርባ ሁሉ እኔ አለሁበት ሲለን የከረመው ውሸት ነው ማለት ነው።

እንግዲህ! ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ከተጠቁ ጥቃት አድራሹ ሕዝቡ እያደረገ ካለው ትግል ጀርባ ሁሉ እኔ አለሁበት የሚለው ግንቦት ሰባት ነውና ራሱ እየፈጸመ ያለውን ጥቃት የማውገዝ ሞራል የሌውም፤ በሌላ በኩ ደግሞ ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ተጠቅተዋል የሚለው ግንቦት ሰባት ጥቃቱን እኔ አልፈጸምኩም ካለ ከሕዝባዊ ትግሉ ሁሉ ጀርባ አለሁበት ሲለን የከረመው ውሸት ነው ማለት ነው። ባጭሩ መግለጫው ራሱን ግንቦት ሰባትን ተጠያቂና ውሸታም የሚያደርግ ነው፤ እንድም ከወያኔ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ትግሬዎች ከተጠቁ ያጠቃቸው ከሕዝባዊ ትግሉ ሁሉ ጀርባ አለሁበት የሚለው ግንቦት ሰባት ነው፤ ከሕዝባዊ ትግሉ ጀርባ ሁሉ አለሁበት ሲለን የከረመው ግንቦት ትግሬዎቹን አላጠቃሁም ካለ ደግሞ ግንቦት ሰባት ከሕዝባዊ ትግሉ ሁሉ ጀርባ አለሁበት ሲለን የከረመው የውሸት ነው ማለት ናውና በሌለበት አለሁበት እያለ ሲዋሸን በከረመው ተጠያቂ መሆን አለበት።

የሆነው ሆኖ ይህ የግንቦት ሰባ የውሸት መግለጫ ፍጹም የተሳሳተ፣ አንዳችም ማስረጃ የማይቀርብበትና ሕዝባች የማይተካ መስዕዋትነት እየከፈለ እያደረገ ያለውን ትግል የሚኮንን በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ተግባር ነው።

እስቲ የመግለጫው ባለቤቶች የሆናችሁ ግንቦት ሰባቶች የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ?

1. የትኛውና መቼ ነው ከሕወሓት ጋር ግንኙነት የሌለው ትግሬ ነው በሕዝባዊ ትግሉ ጥቃት የደረሰበት?

2. ጥቃት ደረሰበት ያላችሁት ትግሬው ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ይዉረው አይኑረው እንዴት አረጋገጣችሁ?

3. ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎችስ ቁጥር ስንት ነው?

4. ከሕወሓት ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ተጠቁ ያላችኋቸው ትግሬዎች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ሁሉ ትግሬዎች በትግሬነታቸው ብቻ ጥቃት እየደረሰባቸው ከሆነ ለምን ሁሉም ትግሬዎች አልተጠቁም ትላላችሁ?

5. በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በሚማሩ ተማሪዎች ዘንድ ታየ ባላችሁት «መጨካከን» ማን በማን ላይ ነው የጨከነው? በጨካኑ ወያኔና ጭካኔ በሚፈጽምባቸው ንጹሐን ተጨፍጫፊዎች መካከል ያለውን የበይና የተበይ ግንኙነት ሁለቱንም እንደ በይ ቆጥሮ «መጨካከን» በሚል መግለጹ ከሕዝብ ወገንተኛነት መራቅ አይደለምን?

እስቲ መልሱልን?!

Filed in: Amharic