>

የትግሬ የበላይነት አለ? ወይንስ የለም?የማይረባ ጥያቄ!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የፋሽስት ወያኔ «አዲሱ» ሊቀመንበር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል ባለፈስ ሰሞን «የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር የለም!» ሲል አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ አይነት ያቀረበውን ንግግር ተከትሎ በኢትዮጵያውያን መካከል የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆን ያልነበረበት ግን ቀዳሚ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው የትግራይ የበላይነት አለ? ወይንስ የለም? የሚለው ወያኔ የሰጠን አጀንዳ ነው። በዚህ ጽሁፍ የትግሬ የበላይነት አለ? ወይንስ የለም? የሚለውን ጥያቄ ከጽንሰ ሐሳባዊ ዳራ ጋር ጠጥረው የሚታዩ አስረጅዎችን እናቀርባለን።

የወያኔው ሊቀመንበር ደብረ ጺዮን ገብረ ሚካኤል ኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይ የበላይነት የለም ሲል የተናገረውን ብልጣብልጥነት ለማስረገጥ ሁለት ነገሮችን አቅርቧል። አንደኛው የወያኔው «የዘር» ፌዴራሊዝም የአንድ ብሔርን የበላይነት አያስተናግድም የሚል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሕወሓት አባላት በኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ ውስጥ የስልጣን የበላይነት የላቸውም የሚለውን የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚ አባላት የሚባሉት ሁሉ የተስማሙበት መሆኑን ነው።

ደብረ ጺዮን በአንደኛ ደረጃ ያነሳውን ድንቁርና ለመመርመር ሩቅ ሳንሄድ «ዘረጋነው» ያለው ፌድራሊዝም በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ ማየቱ በቂ ነው። የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም መሰረቱ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባለው የወያኔ ርዕዮተ አለም ነው። የዚህ የወያኔ ርዕዮተ አለም ማዕከል ደግሞ የዐማራ ጥላቻ ነው። በርግጥ በዐማራ ጥላቻ ላይ የተመሰረተ አገዛዝ ሌላ ሕዝብን ያማከለ ሊሆን አይችል። ባለፉት ሀያ ስድስት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ አመታት ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል ባጋጣሚ የተከሰተ፤ የአይናቸው ቀለም ስላላማረ የተፈጸመ አይደለም። ባለፉት ሀያ ስድስት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ አመታት በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመው ግፍና በደል ታሪካዊ መነሻ ያለው፤ ተቋማዊ ቅርጽ የተሰጠውና በርዕዮት አለም የታገዘ ግፍና በደል ነው። የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም መሰረት የሆነው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባለው የነሌሊኒን ፍልስፍና በባህሪው ያዳላል።

ሳይማር የዶክተርነት ማዕረግ የጠመጠመው ደብረ ጺዮን «ፌዴራሊዝሙ የአንድ ብሔርን የበላይነት አያስተናግድም» እንዳለው ሳይሆን በአብዮታዊ ዲሞክራሲ የተወለደው የዘር ፌዴራሊዝም በባህሪው ዲሞክራሲያዊ አይደለም። አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚነሳው በማዳላት እና ዲሞክራሲ የሚገባቸውና የማይገባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ ብሎ በማሰብ ነው። ዲሞክራሲ የሚገባቸውና የማይገባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ የሚለው የ «ያ ትውልድ» የፖለቲካ ማጠንጠኛ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ፣ የወያኔ ሕገ አራዊትና የዘር ፌድራሊዝማቸው ማዕከል ነው። የሐሳቡ አዳባሪዎች እነ ሌኒን በአብዮታዊ ዲሞክራሲያቸው ዲሞክራሲ አይገባቸውም የሚባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች «በመደብ» የተለዩ ነበሩ። በቤተ ወያኔ ግን ዲሞክራሲ አይገባውም ወይንም በይፋ የማጥፋት ዘመቻ እንዲካሄድበት ሕግ ያወጣበት የሕብረተሰብ ክፍል የተለየው በዘር ሲሆን ያ ዘር ደግሞ ወያኔ ከምስረታው ጀምሮ በየጎራው ያሉ የግራ ኃይሉች ሁሉ እንዲፋለሙት የተዘመተበት የዐማራው ዘር ነው።

የወያኔ ሕገ መንግሥትና «የዘር» ፌዴራሊዝሙ መሰረት የሆነው ወያኔ ዐማራን ለማጥፋት የታገለበት የ1968ቱ የተሓሕት ፕሮግራም ወይንም የኋላው የሕወሓት ማኒፌስቶ ነው። ይህ ፕሮግራም የዘረኛነት አዋጅ ነው። የተለያዩ ዘሮች ባሉበት አገር ውስጥ ፖለቲካው የዘር ሆኖ ለስልጣን የበቃ የዘር ቡድን ባለበት አገር መቼም ቢሆን ፍትሐዊነት ወይንም አለማዳላት ሊኖር አይችልም። የወያኔ ሕገ መንግሥት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን ፈጥሯል። ዛሬ ክልሎች የሚባሉት መስተዳድሮች የክልሉ ባለቤቶች የተደረጉ የጎሳ ባለቤቶቹ ንብረት እንጂ የኗሪዎቹ ሁሉ የጋራ ክፍለ ሀገር አለመሆናቸውን ክልሎች የተባሉቱ የተፈጠሩበትን የክልል ሕገ መንግሥት ማየት ይቻላል። ለዚህ አንድ አስረጂ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚል የተፈጠረውን ክልል ሕገ መንግሥት ማየት እንችላለን።

«ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል» የሚባለው የወያኔ ፍጡር ወያኔ ከጎጃምና ከወለጋ መሬት ወስዶ የፈጠረው አዲስ ቅናት ነው። በዚህ የወያኔ መፈንጫ የሆነ ክልል ውስጥ ዛሬም ድረስ አብዛኛው ባላገር ዐማራና ኦሮሞ ነው። እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ወያኔ ባካሄደው የቤትና የሕዝብ ቆጠራ ቤንሻንጉል ክልል የሚባለው ክልል ውስጥ 784,345 ኗሪዎች ነበሩ። ከነዚህ ውስጥ 170,132 የሚሆነው ዐማራ ሲሆን 106,275 የሚሆነው ደግሞ ኦሮሞ ነው። ክፍሌ ወዳጆ የሚባለው የወያኔ አገልጋይ፤ ከወያኔ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በጻፈው የክልሉ ሕገ አራዊት ግን የክልሉ ሕገ መንግሥት በተባለው ሰነድ ውስጥ ጠቅላላ ድንጋጌዎች በቀረቡበት ምዕራፍ አንቀጽ 2 ስር ስለክልሉ ባለቤቶች እንዲህ ይላል፤

«በክልሉ [በቤንሻንጉል ክልል ለማለት ነው] ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ሕዝቦች የሚታወቁ ቢሆንም፤ የክልሉ ባለቤት ብሄር፣ ብሄረሰቦች ግን በርታ፣ ጉሙዝ፣ ሽናሻ፣ ማኦና ኮሞ ናቸው።

ልብ በሉ! የክልሉ ባለቤቶች የተባሉት ብሄርና ብሄረሰቦች ለምሳሌ ጉምዝ እ.ኤ.አ. በ2007 ዓ.ም. ወያኔ ባካሄደው የቤትና የሕዝብ ቆጠራ መሰረት ብዛቱ 163, 781፤ ሺናሻ 60,687፤ ማኦ 15,384 ሲሆን ኮሞ ደግሞ 7, 773 ነው። ከነዚህ የክልሉ ባለቤቶች ከተባሉት ብሄር፣ ብሄረሰቦች ቁጥር የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ትናንትና ጎጃምና ወለጋ የተወለዱ ዐማራና ኦሮሞዎች ግን ዛሬ ከጎጃምና ወለጋ ተወስዶ በተፈጠረው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ እትብታቸው በተቀበረበት ምድር ባለቤቶች አይደሉም። ለዚህም ነው ደብረ ጺዮን «ፌዴራሊዝሙ የአንድ ብሔርን የበላይነት አያስተናግድም» በማለት አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ አይነት የድንቁርና ድፍረቱን ፍንትው አድርገን እንድናሳይ የወደድነው።

የወያኔ ሕገ መንግሥት የሚባለውና የዘር ፌዴራሊዝሙ በትክክል ይተግበር ቢባል እንኳ አግላይና የሚያዳላ የአፓርታይድ ፕሮግራም ነው። ይህንን የምንለው ከመሬት ተነስተን አይደለም። የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም ክልሎች በተባሉት ውስጥ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን በሙሉ በእኩል አይን አያይም። እንደሚታወቀው ከግማሽ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዛሬ እየኖረ ያለው «ያንተ አይደለም» በተባለ የወያኔ የአገዛዝ ክልል ውስጥ ነው። ይህ ማለት ግማሽ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመምረጥ፣ ንብረት ከማፍራት፣ በራሱ ቋንቋ ከመዳኘት የተገለለና መብት የሌለው ነው ማለት ነው። በወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም መሰረት ጅማ የሚኖር ጉራጌ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት በላቲን ፊደል በቁቤ መጻፍ ይኖርበታል። ሻሸመኔ የሚኖር ወላይታ ፍርድ ቤት የሚቀርበው በትርጁ ማን ነው። ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ የሚኖሩ በርካታ ሚሊዮን ዐማሮች ግብር እየከፈሉ አንድም ወኪል ግን የላቸውም። ናዝሬት የሚኖር የጋሞ ሰው ለናዝሬት አይመረጥም። ሻሸመኔ የሚኖር ሲዳማ ለሻሸመኔ አይመረጥም። ሐረር የሚኖር ዐማራ በሐረሬ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የመመረጥ፣ ራስን የማስተዳደር መብት የለውም።

ባጭሩ የወያኔ ፕሮግራም የወለደው የዘር ፌዴራሊዝም ክልሎች በተባሉት ውስጥ «እኛና ሌሎች» የሚል አስተሳሰብን ፈጥሯል። እኛና ሌሎች የሚለው አስተሳሰብና ተግባር ያለፉት የወያኔ የሀያ ስድስት የአገዛዝ አመታት መገለጫዎች ናቸው። ይህንን የሕይወታችን አካል የሆነውንና የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም ያመጣብንን ግፍና መከርራ ነው እንግዲህ ደብረ ጺዮን የፌዴራሊዝሙ የአንድ ብሔርን የበላይነት አያስተናግድም ሲል በደረቁ ሊላጨን የሚሞክረው። እንዴውም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ቀዳሚ ችግር ሁለተኛ ዜግነትን የፈጠረው የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝም ነው። «እኛና ሌሎች» የሚለውን የወያኔ የዘር ፌዴራሊዝሙ ማጠንጠና ተሽሮ፤ ዛሬ «ዘርህ ከሌላ ነው» በሚል ሰበብ ሁለተኛ ዜጋ የሆነውን በርካታ ሕዝብ የአገሩ ባለቤት የሚያደርግና ሁሉንም በእኩል የሚያስተናግድ አስተዳደር እስካልተፈጠረ ድረስ ዛሬ ባለው የወያኔ ሕገ መንግሥት የአፓርታይድ አገዛዝ ሕጋዊ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሰፈነው አገዛዝ የፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ነው። ይህንን ግልጽ መሆን ይኖርበታል። የፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ የክልል ስርዓት ከደቡብ አፍሪካው የአፓርታይድ የፖለቲካ አቋም የተወሰደ ነው። አፓርታይድ በቋንቋችን በአማርኛ ክልል ማለት ነው። ይሁን እንጂ የወያኔ ዋናው የአመራር ስርዓት ከፋሽስት ጥሊያን የአመራር ስርዓት የተወሰደ ነው። በርግጥ የኢሕአፓም ሆነ የኦነግ የፖለቲካ ፍልስፍና የፋሽስት ጥሊያን ቅጂ ነው። ወያኔ እስከ ዛሬ ድረስ የገዛን ኢትዮጵያውያንን በፋሽስት ጥሊያን የፖለቲካ ቅጂ የውሸት ታሪክ በመፍጠር እየከፋፈለ ነው። ፋሽስታዊና የአፓርታይድ አገዛዝ ደግሞ እንደ ፌዴራሊዝም ተቆጥሮ የአንድ ብሔርን የበላይነት አያስተናግድም ሊባልለት አይችልም። In fact Weyyanes apartheid regime is even more, more, more perfect than South Africa’s apartheid system and that of George’s Orwells 1984.

ደብረ ጺዮን የትግራይ የበላይነት አለመኖሩን ለማሳየት በሁለተኛነት ያቀረበው ሌላኛው ማስተባበያ የሕወሓት አባላት በኢሕአዴግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም ሆነ በካቢኔ ውስጥ የስልጣን የበላይነት የላቸውም የሚል ነው። ይህ ቀልድ ለኛ ሁሉን ነገር ለምናውቀው ለኢትዮጵያውያን ቀርቶ ኢትዮጵያን ለማያውቋት እንኳ የትግራይ የበላይነት እንደሌለ ማሳያ ተደርጎ ሊቀርብ የሚችል አመክንዮ አይደለም። ሲጀምር በአንድ አገዛዝ ውስጥ የአንድ ነገድ ወይንም ቡድን የበላይነት መኖር አለመኖር የሚለካው በተዘረጋው የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ ባሉ የባለስልጣናት ብዛት ብቻ አይደለም። የአንድ ነገድ ወይንም ቡድን የበላይነት መኖር አለመኖር የሚረጋገጠው በዘፈቀደ አይደለም። የአንድ ነገድ ወይንም ቡድን የበላይነት መኖር አለመኖር ራሱን የቻለ የፖለቲካ ፍንሰ ሐሳብና የራሱ መለኪያ ያለው ኅልዮት ነው።

የትግራይ የበላይነት ወይንም በእንግሊዝኛው [Tigrian Domination] ሲባል የትግሬ ዘርን የበላይነት [Tigrian Supremacy] የሚገልጥ ሳይሆን የወያኔ ትግሬዎችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የፖለቲካ የበላይነት የሚያሳይ ነው። ይህ ማለት ግን የትግሬ ዘርን የበላይነት ወይንም Tigrian Supremacyን እነ መለስ ዜናዊ «በእሳት ተፈትነው ወርቅ በሆኑት ትግሬዎች» እና ወርቅ ባልሆነው በሌሎቻችን መካከል ንጽጽር አቅርበው የትግሬ ዘርን የበላይነት ያቀነቀነበትን፣ የአስተሳሰቡም ተከታዮች እንዳሉትና ዛሬም ድረስ ይህን የሚያራምዱ መኖራቸውን በመዘንጋት አይደለም። ሆኖ ግን እኛ በዚህ ጽሁፍ የትግሬ የበላይነት ስንል ወያኔ በፕሮግራም የፈጠረውን የትግሬዎች የፖለቲካ የበላይነትና ልክ የሌለው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማለታችን ነው።

ልዊዝ ጋሪዴ ቨርጋራ [Luis Garrido Vergara] የሚባል በቡድን የበላይነት [domination] ዙሪያ ጥናት ያደረገ ምሁር በአንድ ፖለቲካ ስርዓት ውስጥ ሊኖር የሚችልን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ሲገልጽ «በአንድ ስርዓት ውስጥ የጥቂቶች የበላይነት አለ ማለት የጥቂቶች ሁሉን ነገር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻል ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ቡድኖች የሚሰሩበትን ሕግ ማውጣት፣ መወሰንና ሊሰሩበት የሚገባን ሕግ መበየን መቻል ጭምር ነው» ሲል «Elites, political elites and social change in modern societies» በሚል እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. ባሳተመው የጥፋት ውጤት ላይ አስፍሯል።

ይህን ጽንሰ ሐሳባዊ ዳራ ወደ ኢትዮጵያ አውርደን ስንፈትሸው ወያኔ ባለፉት አስርት ዓመታት የበላይነቱን ለማስጠበቅ የሰራቸውን እልቆቢስ ነውሮች እናገኛለን። ፋሽስት ወያኔ በኢትዮጵያ ምድር የትግራይን የበላይነት ለማንበር ከሰራቸው ነውሮች ቀዳሚዎቹ የዐማራና የኦሮሞ ነገዶችን ጨምሮ ሌሎችንም የኢትዮጵያ ነገዶች ለመግዛት የሚያስችሉትን ድርጅቶችና የሚተዳደሩበትን ሕግ መፍጠር ነበር። በዚህ መሰረት የአገዛዙ ባላባት ፋሽስቱ መለስ ዜናዊ የትግራይን የበላይነት በኢትዮጵያውያን መከራና ፍዳ ላይ ለማደላደል በፈጠራቸው ክልሎች ልክ ስም ብቻ በመለወጥ ድርጅቶችንና የሚተዳደሩበትን ሕግ ፈጥሯል። መለስ ዜናዊ ከድርጅት ማቀነባበሪያ ፋብሪካው የፈጠራቸውን ክልሎች የሚገዙለት ድርጅቶች ሲፈጥር ከክልሎች ስም በስተቀር የሁሉም ድርጅቶች ስሞች አንድ አይነት በማድረግ የድርጅቶችን ስያሜ በCopy and Paste ፈጥሯቸዋል።

ባጭሩ መለስ ዜናዊ የድርጅቶችን ስም ሲያበጅ ያደረገው ነገር ቢኖር የክልሎችን ስም ብቻ ቀይሮ ድርጅቶችን ግን አንድ አይነት አድርጎ ፈጥሯቸዋል። መለስ ዜናዊ በአንድ ስም ከፈጠራቸው የክልል ፓርቲዎች መካከል ወያኔ የፈጠራቸውን የስድስቱን ክልሎች ገዢ ድርጅቶች የተባሉት ፓርቲዎች ስሞች እነሆ፤

1. የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፤
2. የደቡብ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት/ንቅናቄ፤
3. የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ፓርቲ፤
4. የቤንሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት፤
5. የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ፓርቲ፤
6. የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ንቅናቄ፤

ከዚህ በተጨማሪ ወያኔ ዐማራ ክልል ሲል የፈጠረውን አካባቢ ለመግዛት ኤርትራዊውን በረከት ሰምዖን እንደራሴ አድርጎ «ብሔረ ኣማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» ሲል ለዐማራ ሕዝብ ለማስተዳደር የትግርኛ ስም ያለው ድርጅት አቋቋመ። ልብ በሉ! ዐማራ የተባለውን ክልል በእንደራሴነት እየገዛ ያለው ድርጅት መለስ ዜናዊ ብሔረ ኣማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሲል ስሙን ትግረኛ ያደረገው ድርጅት ነው። እስከ ዛሬ ግን «ብሔረ ኣማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» የሚባለው የመለስ ዜናዊው ፍጡር ብአዴን ስያሜ ትግረኛ እንደሆነ ብዙ ሰው ልብ ያለው አይመስል።

ወያኔ የትግራይን የበላይነት ለማስጠበቅ የፈጠረው ክልሎችን፣ በእንደራሴነት የሚያስተዳድሩለትን ድርጅቶችና የሚገዙበትን ሕግ መንግሥትና መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሳይሆን የየድርጅቶቹ የበላይ ጠባቂም የራሱን ሰዎች አስቀምጧል። ዐማራ ለሚባለው ክልል ኤርትራዊውን በረከተ ሰምኦን፣ ትግሬዎችን እነ ሕላዬ ዮሴፍን፣ ካሳ ተክለ ብርሃንን፣ ታደሰ ጥንቅሹን፣ ጫኔ ከበደን፣ ወዘተ ሲፈጥር፤ ኦሮምያ ለሚባለው ክልል ሰለሞን ጢሞን፤ ደቡብ የሚባለውን ክልል ለመቆጣጠር ደግሞ ቢተው በላይ የሚባሉ ትግሬዎች አሰማርቶ ሁለቱ ትግሬዎች ሁለቱን ክልሎች በኦሕዴድና በደሕዴን ዋና ጽህፈት ቤቶች ውስጥ ቢሮ ከፍተው ክልሎቹን ያስተዳድሩና እንደራሴዎችን ያዝዙ ነበር።

ወያኔ የፈጠራቸውን ክልሎች ከፍ ሲል በቀረበው መልኩ ከጠረነፈ በኋላ የተቀረው የሕብረተሰብ ክልፍ ደግሞ እንዳይተነፍስ፤ አይን ያወጣውን የአገዛዙን ነውረኛነት ነጻ ሜዲያዎች እንዳይተቹ የፀረ ሽብር ሕግ፣ የብዙኃን መገናኛና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና የሲቪክ ማኅበራት ማቋቋሚያ አዋጅ፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና ታክስ አዋጆችና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት የታገለለትን የትግራይ የበላይነት በኢትዮጵያውያን ስቃይ ላይ ያደላድላል። በነዚህ አዋጆች ከ2002– 2006 ዓ.ም ባሉት አራት አመታት ብቻ «ሂውማን ራይትስ ዋች» የሚባለው ለሰው ልጆች መብት የቆመው ድርጅት እንደዘገበው ከ19 በላይ ጋዜጠኞች ለእስር ሲዳረጉ፤ ከ60 በላይ ጋዜጠኞች ደግሞ አገር ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል። ከእነዚህ ታሳሪዎችና ተሰዳጆች መካከል አንድም የትግራይ ተወላጅ የለም። ፋሽስት ወያኔ ከፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥም የወያኔን ቅጥ ያጣ ዘረፋና ግፍ የሚቃወሙ አንዳንድ ግለሰቦች ብቅ የሚሉት ከሆነ ኦሮሞዎችን በጠባብነት፤ ዐማራ የሆኑትን ደግሞ በትምክህተኛነት እየከሰሰ በማሸማቀቅ አንገታቸው አስደፍቶ እንደ ሸንኮራ አገዳ ተጠቅሞ ይጥላቸውና በራባቸውና ሁሉ ብርቁ በሆኑ አዲስ ሆዳሞች ይተካቸዋል።

እንግዲህ! ኦሮምያ፣ ዐማራና ደቡብ የሚባሉትን ክልሎች ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የፈጠራቸውን ክልሎች ወያኔ የሚገዛው ተጋድሎ ሓርነት ሕዝብ ትግራይ ወይንም ተሓሕት በ1968 ዓ.ም. ያወጣውን ፕሮግራም በ1983 ዓ.ም. ስልጣን ከያዘ በኋላ ወደ ሕገ መንግሥት በመቀየር፣ የየ አካባቢውን እንደራሴዎች በመፍጠር፣ ከጽንሰ ሐሳብ እስከ ትግበራ ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ ሁሉ ፊት አውራሪ በመሆን ነው። ይህ ባለፉት ሀያ ስድስት አመታት በኢትዮጵያ ምድር ሰፍኖ የቆየው አሰራር ልዊዝ ጋሪዴ ቨርጋራ «በአንድ ስርዓት ውስጥ የጥቂቶች የበላይነት አለ ማለት የጥቂቶች ሁሉን ነገር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻል ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ቡድኖች የሚሰሩበትን ሕግ ማውጣት፣ መወሰንና ሊሰሩበት የሚገባን ሕግ መበየን መቻል ጭምር ነው» ሲል ካስቀመጠው ጽንሰ ሐሳባዊ መሰረት ጋር የሚገጥምና ኅልዮት ለሚፈልጉ የትግሬን የበላይነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሳይንሳዊ መለኪያ ነው።

ደብረ ጺዮን ያደረገውን አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ አይነት ንግግር ተከትሎ በማህበራዊ ሜዲያዎቻችን ተቃዋሚ ነን በሚሉ ግለሰቦች ዘንድ ሳይቀር የሕወሓት እንጂ የትግራይ የበላይነት የለም ሲባል አስተውለናል። እነዚህ ግለሰቦች እንዲህ አይነት ድማዳሜ ላይ እየደረሱ ያለፉት ባለፉት ስርዓቶች የዐማራ የበላይነት የለም ካልን እንዴት ዛሬ የትግራይ የበላይነት አለ እንላለን የሚልና ሕወሓትና የትግራይን ሕዝብ መለየት አለብን ከሙሉ የተሳሳቱ መነሻዎች የሚመነጭ ነው። ከሁሉ በፊት የዐማራ መንግሥት አልነበረምና ባለፉት የኢትዮጵያ መንግሥታት የዐማራ የበላይነት ብሎ ነገር ሊኖር ይቅርና ሊታሰብም አይችልም። የኢትዮጵያ መንግሥታት ብሔራዊ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ የኢትዮጵያን መንግሥታት የዐማራ መንግሥታት ሊያደርጋቸው አይችልም። አንድ መንግሥት አማርኛ ቋንቋን በመንግሥትነት ተሰይሞ መገልገሉ የዐማራ መንግሥት የሚያሰኘው ከሆነ የአገዛዙ የስራ ቋንቋ አማርኛ የሆነው ወያኔም የዐማራ መንግሥት ነው ማለት ነው። ስለዚህ ያለፉትን የኢትዮጵያ መንግሥታት የኢትዮጵያ መንግሥታት እንጂ የትኛውም የዘውግ ውክልና ስለሌላቸው ከዐማራ የበላይነት ጋር የሚያገናኛቸው አንዳችን ነገር የለም። ስለዚህ ዛሬ ትግሬን ወክሎ በመንግሥትነት የተሰየመው የወያኔ መንግሥት ያሰፈነውን የትግሬ የበላይነት ባልነበረ የዐማራ መንግሥትና በልታየ የዐማራ የበላይነት ልናጣፋው አንችልም። ስለዚህ ይህ መከራከሪያ ከመነሻው ውሃ የማይቋጥርና ከቁምነገር የሚገባ አይደለም።

ሁለተኛውና ሕወሓትንና የትግራይን ሕዝብ መለየት አለብን የሚለው የትግራይን የበላይነት አለመኖር ለማሳየት የሚቀርበው መከራከሪያም በወያኔ አገዛዝ ውስጥ የትግራይ የበላይነት ላለመኖሩ እንደ አስረጂ ተደርጎ ሊቀርብ የሚችል አይደለም። ሕወሓት መንግሥት ሆኖ ያለው የትግራይን ሕዝብ ወክሎ ነው። ይህ የትግራይን ሕዝብ የወከለው ድርጅት ለትግራይ የበላይነት ሌተ ተቀን የሚሰራ ድርጅት ነው። የወያኔ አገዛዝ የዘረጋው የዘረፋና የመድሎ መዋቅር ትግሬ ለሆነ ሁሉ ክፍት ነው። አገዛዙ ለትግሬ የሚያደላው የሕወሓት የአባልነት መታወቂያ በመጠየቅ አይደለም። በየትኛውም መንግሥታዊም ይሁን አስተዳደራዊ መዋቅር ውስጥ የሕወሓት አባል ባልሆነ ትግሬና ትግሬ ባልሆነ ሌላ ኢትዮያዊ መካከል መድሎ ይደረጋል።ይህ ለማየት ወደ የትኛውም በአገዛዙ ስር ወዳሉ መስሪያ ቤቶች መሄድና ማየት ይቻላል። በየትኛውም መስሪያ ቤት ውስጥ አንድ ሰው ትግሬ መሆኑ እንጂ የሕወሓት አባል መሆን አለመሆኑ የሚጠየቅ ጉዳይ አይደለም። ይህን ለማስረገጥ ላይ ሩቅ ሳንሄድ የአረና ፓርቲ አባል የነበረው የተምቤኑ አስራት አብርሓም ከአራት አመት በፊት ለፍትህ ጋዜጣ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ማውሳት ይቻላል። አስራት አብርሓም በፍትሕ ጋዜጣ፤

«መጽሀፍክ ላይ ሕወሓት በደቡብ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች ክልሎች የራሱን ሰዎች ያስቀምጥ ነበር ስትል የገለፅከውን አብራራው እስቲ?» ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልስ እንዲህ ብሏል፤ . . .

«ይሄ አዲስ ነገር አይደለም። በኦሮምያ እነ ሰለሞን ጢሞ፤ በደቡብ እነ ቢተው በላይ ነበሩ። እንዲያውም አንድ አጋጣሚ ልንገርህ ። አንድ ትግርኛ የሚናገር የአዲስ አበባ ልጅ በአቶ ኪሾ ጊዜ አዋሳ ሄዶ ከደህንነት መ/ቤት እንደመጣ ሆኖ በመቅረቡ መኪና ተመድቦለት አስተዳደሩን ሲያሽከረክር የነበረበት ነገር ነበር። እንግዲህ አንድ ሰው ያለአንድ ማስረጃ እንዲህ ማድረግ ሲችል ምን ትላለለህ።»

ልብ በሉ! አስራት እየነገረን ያለው ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳ የሄደ አንድ ተራ ትግሬ ልጅ የደቡብ ክልልን ርዕሰ መስተዳደር አባተ ኪሾን አሹሮታል። ለይስሙላ ያልህ ሕወሓት ይሁን አይሁን መያወቂያ እንኳ ሳይጠየቅ ትግሬነቱ መታወቂያ ሆኖት አንድ ተራ ትግሬ ሀምሳ ስድስት ብሔረሰብን ወክሎ የክልል ርዕሰ መስተዳደር የሆነን ሰው ሊዘውር የቻለው ትግሬነቱን መከታ አድርጎ ነው። የትግሬ የበላይነት የለም የሚሉን ሰዎች መታወቂያ ወረቀት እንኳ ሳይጠየቅ ትግሬነቱን ብቻ መከታ አድርጎ የአንድን ክልል መስተዳድር ያሽከረከረውን አስራት አብርሃም በቃለ መጠይቁ ያነሳውን ተራ ትግሬ ድርጊት ሕወሓት የትግሬ የበላይነት እንዲኖር ሳይሰራ የመጣ ነው እንዳማይሉን መቼም ተስፋ አለን። ባጭሩ የሕወሓት መዋቅር የተዘረጋው የወያኔን አባላት ብቻ ሳይሆን ትግሬ የሆነን ሁሉ ትግሬነቱን መከታ አድርጎ እንዲጠቀም ነው። ለዚህም ነው አንድ ተራ ትግሬ በኢትዮጵያ ምድር ምንም የማድረግ መብት ያለው።

የወያኔ አገዛዝ የሕወሓት ብቻ ሳይሆን ትግሬ የሆነን ሁሉ ለመጥቀም የተዘረጋ ስርዓት መሆን አለመሆኑን ለማየት ወልቃይት፣ ጠገዴና ሑመራ መሄድ ብቻ ይበቃል። ትናንትና የወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በነበሩት በኮርም፣ በወለዛይ፣ በዋጃ፣ በዞብል፣ በአላማጣ፣ ወዘተ ይኖሩ የነበሩ የአገሩ ባለቤቶች ዐማሮች ጠፍተውና ማንነታቸውን ቀይረው መሬቱን ግን ከትግሬዎች በሰፈራ የመጡ ገበሬዎች ሰፍረውበት ታገኙታላችሁ። ትናንትና ጎንደር የነበረውና ከዚያ ቀደም ብሎ ስሜን ጠቅላይ ግዛት ተብሎ ይታወቅ በነበረው በወልቃይት፣ በጠገዴና በሑመራ ዐማራ ከእርስቱ እየተነቀለና እየጠፋ የሰፈረበት ወያኔ ከተከዘ ማዶ ከመሐል ትግራይ በሰፈራ ያሰፈራቸው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ትግሬዎች ናቸው። የወያኔ አገዛዝ ትግሬን ብቻ ለመጥቀም የተዘረጋ መሆኑን ለማሳየት ከዚህ በላይ አስረጅ ሊኖር አይችልም።

ቀደም ብለን ባቀረብነውና ወያኔ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ሲል በፈጠው ክልል ውስጥ እየተደረገ ያለውን ቅጥ ያጣ የትግሬ የበላይነት ማሳያም ማንሳት እንችላለን። በዚህ የወያኔ ክልል ውስጥ ከጎጃም የተወሰደው መተከል አውራጃ በቤንሻንጉል ክልል ውስጥ ሰፊው ዞን ነው። ይህ አውራጃ ርስታቸው የሆኑት ዐማሮች ላለፉት በርካታ አመታት የክልሉ ባለቤት አይደለህም ተብሎ እየተጨፈጨፈ «ወደ አገርህ ሂድ» ሲባል የከረመው የጋምቤላ ክልል መሬት ተወደድብን ላሉ የትግራይ ባለሃብቶች ሰፋፊ መሬቶችን ለመስጠት ሲባል ነው። ክልሉን እንዲያስተዳደር በወያኔ የተሰየመው ምስለኔው አሻድሊ ሀሰን «ዐማራዎችን ከአገራችሁ አስወጡ» ተብሎ ትዕዛዝ እንደተላለፈለት ተናግሯል። የማፈናቀሉ ስራም በአንድ ዙር እንዳይካሄድ በጥብቅ ታዝዟል። እቅዳቸው ተራ በተራ በማፈናቀል ያን ለም መሬት ለትግራይ ባለሃብቶች ጨርሶ ለመስጠት ነው። ትናንትም ሆነ ዛሬ እየሆነ ያለው ይህ ነው። ትናንት የተጨፈጨፉትን ዐማሮች ቦታ ለማረስ ተጨማሪ የትግራይ ባለሀብቶች ከሰሞኑ ከአውሮፓና ከአሜሪካ እየተጠሩ ከልማት ባንክ ያሻቸውን ገንዘብ በመዛቅ ትራክተር ከኤፌርት ገዝተው መተከል እየገቡ እያረሱ ነው። በዐማራ መቃብር ትግራይን ይገነቧል ማለት ይህ ነው።

ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉ አንድ ነገር በተነሳ ቁጥር ከትግሬ ውጭ ያሉት ተማሪዎች በቆመጥና በጥይት እየተደበደቡ የትግራይ ተማሪዎች ግን ልዩ ጥበቃ የሚደረግላቸውን አላየንም አልሰማንም ማለት መቼም አይቻልም። በሕዝብ ቁጥር ድርሻ አኳያ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር በፌዴራል መንግሥቱ በትምህርት ሚኒስትር ስር ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ከሚደረጉት በኢትዮጵያ ተማሪዎች መካከል የትግራይ ድርሻ ከሁሉ የላቀ ነው። ይህ ሁሉን ትግሬ የሚጠቅም ፕሮግራም እየተሰራ ያለው ሕወሓትን ብቻ ለመጥቀም አይደለም። በደርግ የተወረሰው የትግሬዎች ንብረት በወያኔ ዘመን ሲመለስ የተቀሩት ኢትዮጵያውያን ንብረት ግን እንደተወረሰ የቀረው የወያኔ አገዛዝ የቆመው ለትግሬዎች ብቻ ስለሆነ ነው።
ኢትዮጵያ ውስጥ ሶስት ሺህ ዶላር ሚሊዮነሮች ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ ዶላር ሚሊዮነሮቹ ትግሬዎች ናቸው። ኤፌርት የሚባለው የንግድ ኮርፖሬሽን ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የታወጀ ካፒታል [declard capital] እንዳለው ይታወቃል። ይህ ኮርፖሬሽን በይፋ የትግራይ ሕዝብ ሀብት እንደሆነና ይህንንም ወያኔ የነገረን መሆኑ አለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የአምስት ቢሊዮን ዶላር ኮርፖሬሽን ባለቤት የሆነ ሕዝብ ቢኖር የትግራይ ሕዝብ ብቻ ነው። የአምስት ቢሊዮን ዶላር ባለቤት የሆነን ሕዝብ በተለየ መልኩ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ አልተደረገም ማለት አይቻልም።

በፖለቲካው ዘርፍ ያለውን የትግሬ የበላይነት ለማየት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አመራሮች እንደ ማን እንደሆኑ ማየት ይበቃል። ወረድ ብለን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከላይ እስከ ታች በነማን እንደተያዘ የሚያሳየንን ማስረጃ እንደሚከተለው እናቀርባለን፤
1. የመከላከያ ኢታማጆር ሹም — ሜ/ጀ ሳሞራ የኑስ (ትግሬ)

2. የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር — ብ/ጀ ገ/ኪዳን ገ /ማሪያም(ትግሬ)

3. የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)

4. የመከላከያ በጀትና ፕሮገራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ምቡዝ አብርሃ(ትግሬ)

5. የመከላከያ የኪነ-ጥበባት ስራወች ኃላፊ —ኮ/ል ክብሮም ገ/ እግዚአብሄር (ትግሬ)

6. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን የግንኙነት መምሪያ ኃላፊ—ኮ/ል ነጋሲ ትኩ (ትግሬ)

7. የመከላከያ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ገ/ትንሳይ ሓጎስ (ትግሬ)

8. የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ — ሌ/ጀ ሳህረ መኮንን (ትግሬ)

9. የመከላከያ ሎጅስቲክ መምሪያ ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ኢብራሂም አብደል ጀሊድ (ትግሬ)

10. የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኃላፊ —ሜ/ጀ ክንፈ ዳኛዉ(ትግሬ)

11. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንደንት —ብ/ጀ ሃለፎም እጅጉ (ትግሬ)

12. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ኃላፊ— ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ (ትግሬ)

13. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ገ/እግዚአብሄር በየነ (ትግሬ)

14. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ —ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ (ትግሬ)

15. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዱክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ —ኮ/ል ጌታሁን ካህሳይ (ትግሬ)

16. የብላቴ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ (ትግሬ)

17. በልዩ ሀይል ማሰልጠኛ ማእከል የልዩ ኃይልና ጸረ ሽብር ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ —ሻለቃ ተክላይ ወ/ገብርኤል (ትግሬ)

18. የሜ/ጀ ሀየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ— ኮ/ል ጎይቶም ፋሮስ (ትግሬ)

19. የጦር ላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል አደም ምትኩ (ትግሬ)

20. የሜ/ጀ ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ (ትግሬ)

21. የሆሚት አሙኒሽን ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ዋና ኃላፊ —ኮ/ል ሃድጉ ገ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)

22. የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ — ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ (ትግሬ)

23. የመከላከያ ኮንስትራክሽንና ኢንጅነሪንግ ማሽነሪ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ— ሻለቃ ካህሳይ ክህሸን (ትግሬ)

24. የመከላከያ መሰረታዊ ልማትና ግንባታ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ— አቶ ወልዳይ በርሄ (ትግሬ)

25. የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ኢንዱስትሪ ም/ስራ አስኪያጅ —ሻለቃ አማኑኤል አብርሃ (ትግሬ)

26. የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ ኃላፊ — ሌ/ኮ ለተብርሃን ደመወዝ (ትግሬ)

27. የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ሃጎስ አስመላሽ (ትግሬ)

28. የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ጸጋዬ ግርማይ (ትግሬ)

29. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግኑኝነትና ስርአት ደህንነት መምሪያ ኃላፊ — ኮ/ል በርሄ አረጋይ (ትግሬ)

30. የመከላከያ ፋዉንዴሽን ኃላፊ — ብ/ጀ ያይኔ ስዩም (ትግሬ)

31. የሽሬ ከተማ ኮሪደር ሜንተናንስ ኃላፊ — ኮ/ል አብርሀ ገ/ መድህን (ትግሬ)

32. የብሔራዊ ተጠባባቂ የሃይል ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ማሞ ግርማይ (ትግሬ)

33. የኢንሳ ዳይሬክተር —ሜ/ጀ ተክለብርሃን/ካህሳይ (ትግሬ)

34. የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተርና የጅኦስፓሻል ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ታዚር ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)

35. የሰሜን እዝ አዛዥ —ጄ/ል ገብራት አየለ (ትግሬ)

36. የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክ ኃላፊ — ብ/ጄ አብርሃ አረጋዊ (ትግሬ)

37. የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ብ/ጀ ማዕሾ በየነ (ትግሬ)

38. የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ነጋሲ ተስፋዬ (ትግሬ)

39. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ — ሌ/ኮ ሙሉ አብርሃ (ትግሬ)

40. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ስላሴ በላይ (ትግሬ)

41. የሰሜን እዝ የሰሜን ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ላዕከ አረጋዊ (ትግሬ)

42. የሰሜን እዝ መሃንዲስ አዛዥ —ኮ/ል ተሰስፋየ ብርሃኔ (ትግሬ)

43. የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ጽ/ቤት ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ዮሃንስ ተክሌ (ትግሬ)

44. የሰሜን እዝ አጠቃላይ የትምህርት አገልግሎት ኃላፊ —ኮ/ል ግደይ ሃይሌ (ትግሬ)

45. የሰሜን እዝ የመድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሀላፊ ኮ/ል ሰገደ/ ገ/መስቀል (ትግሬ)

46. የሰሜን እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ —ኪሮስ ወ/ስላሴ (ትግሬ)

47. የሰሜን እዝ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ታደለ ገ/ህይወት (ትግሬ)

48. የሰሜን እዝ የሰዉ ኃይል አመራር መምሪያ ኃላፊ — ኮ/ል መሃሪ አሰፋ (ትግሬ)

49. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ — ኮ/ል ጀማል መሃመድ (ትግሬ)

50. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ሆስፒታል ጤና ኃላፊ — ሌ/ኮ ተክላይ ገ/መድህን (ትግሬ)

51. የሰሜን እዝ የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬክተር — ሻለቃ ነጋሲ ሃጎስ (ትግሬ)

52. የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ — ሜ/ጀ ዮሃንስ ወ/ዮሃንስ (ትግሬ)

53. የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ብ/ጀ አብርሀ ተስፋይ (ትግሬ)

54. የማዕከላዊ ዕዝ የትምህርት ክትትል ኃላፊ —ሌ/ኮ ሀጎስ ሀይሌ (ትግሬ)

55. የማዕከላዊ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አዛዥ ኮ/ል ገ/ሚካኤል ኪ/ማርያም (ትግሬ)

56. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ ምክትል አዛዝና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማ (ትግሬ)

57. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪና ማመላለሻ ዲፓርትምንት ኃላፊ — ሻለቃ ተክላይ ካህሳይ (ትግሬ)

58. የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ፍስሀ ኪዳኑ(ትግሬ)

59. የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ ኃላፊ —ብ/ጀ አብድራሃማን ኢስማኤል (ትግሬ)

60. የምዕራብ ዕዝ ኢንሰፔክሽን ኃላፊ — ኮ/ል ዮሃንስ ገ/ሊባኖስ (ትግሬ)

61. የምዕራብ ዕዝ ሲግናል ሬጅመንት አዛዥ — ኮ/ል ተክላይ ገ/ጻድቃን (ትግሬ)

62. የምዕራብ ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ገ/ኪዳን ቸኮል (ትግሬ)

63. የምዕራብ ዕዝ የስልጠና ኃላፊ — ኮ/ል በርሄ ኪዳነ (ትግሬ)

64. የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ — ኮ/ል ንጉሴ ሐይሌ (ትግሬ)

65. የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ — ሌ/ጀ አብርሀ ወ/ማሪያም (ትግሬ)

66. የደ/ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ብ/ጀ የማነ ሙሉ (ትግሬ)

67. የደ/ምስራቅ ዕዝ የትራንስፖርት ኃላፊ —ኮ/ል ቀለህ ገ/ስላሴ (ትግሬ)

68. የደ/ምስራቅ ዕዝ የህግ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ገ/ሚካኤል ገብራት (ትግሬ)

69. የደ/ምስራቅ ዕዝ ጤና ት/ቤት ዳሬክተር — ሻ/ል ሀፍቱ ሰብለዉ (ትግሬ)

70. የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ሃጎስ [ህቁት] (ትግሬ)

71. የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥና የአስተዳደር ፋይናንስ ኃላፊ — ኮ/ል ተ/ብርሃን አለማየሁ (ትግሬ)

72. የ7ኛ ሜካናይዝድ ከ/ጦር የወንጀል ምርመራ ኃላፊ — አምሳ አለቃ ሀይለአብ ፍስሀ (ትግሬ)

73. የ8ኛ ሜካናይዝድ ከ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ዘሚካኤል (ትግሬ)

74. የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ኢንዶክትሬሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ —ሌ/ኮሎኔል ሓጎስ ታረቀኝ (ትግሬ)

75. የ12ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ኮ/ል ምሳሁ ገ/ተክሌ (ትግሬ)

76. የ20ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ሰመረ ተክሉ (ትግሬ)

77. የ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ወ/ጊዮርጊስ ተክላይ (ትግሬ)

78. የ23ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ በላይ ስዩም (ትግሬ)

79. የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ፍስሀ ወርቅነህ (ትግሬ)

80. የ24ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ — ሎ/ኮ ዘሚካኤል ብርሀኔ (ትግሬ)

81. የ25ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ አሰፋ ቸኮል (ትግሬ)

82. የ25ኛ ክ/ጦርምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ሊባኖስ ገ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)

83. የ32ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)

84. የ32ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የፋይናንስ ኃላፊ — ኮ/ል መሃሪ በየነ (ትግሬ)

85. የ32ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ — ሌ/ኮ ተክሊት ገ/ህይወት (ትግሬ)

86. የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ጋይም መሸሻይ (ትግሬ)

87. የ33ኛ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ — ሻ/ል መብርሀቶም አብርሀ (ትግሬ)

88. የተዋጊ መሀንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ሙሉ ግርማይ (ትግሬ)

89. የተዋጊ መሀንዲስ ምክትል አዛዥ — ኮ/ል ሰመረ ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)

90. የተዋጊ መሀንዲስ ክ/ጦር ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል አደም ትኩ (ትግሬ)

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሚባለውንና የሰላም አስከባሪ ኃይል የሚባለውንም እንደሚከተለው በትግሬዎች ብቻ የተያዘ ነው፤

91. የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ —ብ/ጀ መአሾ ሀጎስ (ትግሬ)

92. የአየር ኃይል የዘመቻ እቅድ መምሪያ ኃላፊ—ኮ/ል ደሳለኝ አበበ (ትግሬ)

93. የማዕከላዊ የአየር ምድብ ዋና አዛዥ — (ኮ/ል ሰለዎን ገ/ስላሴ ትግሬ)

94. የማዕከላዊ የአየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ጸጋየ አረፈአይኔ (ትግሬ)

95. የምዕራብ አየር ምድብ 3ኛሚሳይል ክንፍ አዛዥ — ሻ/ል ገ/እግሂአብሄር ኅ/ስላሴ (ትግሬ)

96. የምዕራብ አየር ምድብ የ301ኛ አየር መቃወሚያ አዛዥ— ሻ/ል ዝናቡ አብራሃ (ትግሬ)

97. የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ—ኮ/ል ኪዱ አሰፋ (ትግሬ)

98. የምዕራብ አየር ምድብ አዛዥ እና የኦሎጅስቲክ ኃላፊ — ሌ/ኮ ክብሮም መሀመድ (ትግሬ)

99. የሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ኃይሌ ለምልም (ትግሬ)

100. የሰሜን አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የአስተዳደርና ፈይናንስ ኃላፊ—ኮ/ል ጸጋየ ካህሳይ (ትግሬ)

101. የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ—ኮ/ል አበበ ተካ (ትግሬ)

102. የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ሙሉ ገብሌ (ትግሬ)

103. ካሳ የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ — ሻ/ቃ ጸጋ ዘአብ (ትግሬ)

104. የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ምክትል ኃላፊ — ሻ/ቃ ሀፍቶም ዘነበ (ትግሬ)

105. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር የ8ኛ ታንከኛ ሻምበል አዛዥ— ሻ/ቃ ወልደ ገሪማ (ትግሬ)

106. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር ምክትል የሃይል አዛዥ —ብ/ጀ ህንጻ ወ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)

107. በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 9ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ —ኮ/ል ጽጋቡ ተወልደ (ትግሬ)

108. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር 10ኛ ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል ገ/ህይወት አደራ (ትግሬ)

109. በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል መለሰ ብርሀን (ትግሬ)

110. በዳርፉር ሰላም ማስከበር ድጋፍ ሰጭ ቡድን አስተባባሪ — ኮ/ል ዮሴፍ አሮን (ትግሬ)

111. በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል ተክላይ ወ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)

112. በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ የዘመቻ አዛዥ —ሻ/ቃ ሀጎስ ነጋሽ (ትግሬ)

እንግዲህ! ከፍ ሲል ከቀረበው ዝርዝር ማስረጃ ማየት እንደሚቻለው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ በአየር ኃይል፣ በአጋዚ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በሚባለው ውስጥ በየ ንዑስ ክፍሉ ካሉ አስር የአዛዥነት መደቦች መካከል ቢያንስ ዘጠኙ በትግሬዎች የተያዙ ናቸው። ልብ በሉ! በሕጉ መሰረት የአገር መከላከያ ሰራዊት የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ውግንና/አባል አይሆንም። በዚህ መሰረት ከፍ ብለው እስከ 112 ድረስ የዘረዘርናቸው የመከላከያ አዛዦች ሁሉ ትግሬዎች እንጂ የሕወሓት አባላት አይደሉም ማለት እንችላለን። ይህ ማለት በመከላከያው ያለው የበላይነት የትግሬ እንጂ የሕወሓት አይደለም ማለት ነው።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ላለፉት 26 ዓመታት ግፍና ጭፍጨፋ እየፈፀመብን ያለው ቅልብ ጦር ከተከዘ ማዶ ከአንድ መንደር በመጡት ነውረኞች ሙሉ በሙሉ የተያዘ ነዉ። ወደድንም ጠላንም እውነታው ይህ ነው። ቅኝ ግዛት ማለት 95% የሚሆነው ሕዝብ ተረስቶና ተረግጦ ሀብቱና ስልጣኑ በሙሉ 5%ቱን ሕዝብ እንወክላለ በሚሉ የአንድ ዘር ሰዎች ቁጥጥር ሲወድቅ ነው። ከፍ ሲል ከቀረበው ማስረጃ እንዳየነው የፋሽስት ወያኔ የትግራይ የአፓርታይድ አገዛዝ ስላልታወጀ ነው እንጂ ቅኝ ግዛት ከዚህ የከፋ ሊሆን አይችልም።

እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ሊሰመርበት ይገባል። ከፍ ብለው እንዳነሳነው «የትግሬ የበላይነት አለ» የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ነው። ይህ ማለት ግን እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ሚሊዮነር ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን የፋሽስት ወያኔ አገዛዝ በዘረፋ የከፈታቸው ፋብሪካዎች፣ በገፈፋ ያቋቋማቸው ታላላቅ የንግ ኩባንያዎች፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እሱን የሚያህል ኩባንያ የለም የተባለለት ኤፌርት የሚቀጥራቸው ሰዎች የትግራይ ተወላጆች ብቻ ናቸው። ይህ ደግሞ ባጋጣሚ የመጣ ሳይሆን ታስቦበት፣ በእቅድና በፕሮግራም የሆነ ነው።

ባጠቃላይ የትግሬ የበላይነት አለ? ወይንስ የለም? የሚለውን ጉዳይ በመሰለኝና በደሳለኝ የምናቀርበው ጉዳይ አይደለምና ያፈጠጠውን እውነታ በስርዓት ማጤን ያስፈልጋል! የትግሬ የበላይነት ለፖለቲካዊ ተአርሞ ሲሉ የተወሰኑ ግለሰቦች የለም ስላሉ የማይኖር፤ እንዲኖር የሚፈልጉ ጎትተው የሚያመጡትም ጉዳይ አይደለም። የትግሬ የበላይነት የሚለው የሚለካና ንድፈ ሐሳባዊ መሰረት ያለው ተጨባጭ ነገር ነው። የትግሬ የበላይነት የለም ብሎ መከራከር እውነታን የመካድ ድንቁርና ብቻ ሳይሆን በድሎት ጥንቡን የጣለውን አልተመቸህም ብሎ ማሸርገድ ነው። እንዴውም ለፖለቲካ ተአርሞ ሲባል የአገሪቱን ፖለቲካ የተቆጣጠሩት ትግሬወች ናቸው…. ግን የትግሬ የበላይነት የለም፤ የአገሪቱን የደህንነት ተቋም የተቆጣጠሩት ትግሬወች ናቸው…. ግን የትግሬ የበላይነት የለም፤ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነት የተቆጣጠሩት ትግሬወች ናቸው…. ግን የትግሬ የበላይነት የለም. . .ወዘተ አይነት እውነታውን የመካድ ድንቁርና የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ መንስኤ የሆነውን የተንሰራፋውን የትግራ የበላይነት የበለጠ በማጀገን የአፋኝና ገዳይ አገዛዙን እድሜ እንደማራዘም ይቆጠራል።

ከፍ ሲል በንድፈ ሐሳብ ተደግፎ በተጨባጭ ሞልተው በተረፉ በቀረቡ ማሳያዎች ታጅቦ የቀረበው ሀተታ እንደሚያሳየው የትግራይ የበላይነት ከመኖር አልፎ ወደ ብዝበዛና ምዝበራ ደረጃ የተሸጋገረ መሆኑን ማየት እንችላለን። ያለ ጥርጥር በወያኔዋ ኢትዮጵያ የትግሬ የበላይነት አለ ብቻ ሳይሆን ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር ሁሉ ዋነኛ የቀውስ መንስኤ ነው። አጥልቀን ካሰብንበት እውነታው ይሄ ነው!

Filed in: Amharic