>

የሕውሀቱ ንጉስ ጦና (ከሚሊዮን አየለች)

የፖለቲካን ህይወትን በአጋጣሚ እንደጀመረ የሚነገርለት ሀይለማሪያም ደሳለኝ ቦሼ የመጀመሪያ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና ያገኘ ሲሆን የማስተርስ ትምህርቱን በሳኒቴሽን ኢንጅነሪንግ የትምህርት አይነት እንዳገኘም ይነገርለታል፡፡ ለተከታታይ 13 አመታት በዩኒቨርስቲ ፖሊቲክኒክ መምህርነትና በአስተዳደር ዘርፍ በመስራት የቆየ ሲሆን የፖለቲካ ህይወቱን የጀመረው የዱቡቲ ከተማ አስተዳደር በመሆን ነበር ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ የEPRDF አባል በመሆንና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ፕሬዘዳንት በመሆን ለተከታታይ 5 አመታት አስተዳድሯል፡፡ ከዚህ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ኃላፊነት ቦታ ላይ በመሆን የህውሃት የደቡብ ህዝቦች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ ለመሆን በቅቷል፡፡
ተናግሮ ማሳመን እና በእርሱ አስተሳሰብና ማንነት መምራት እንደማይችል በተደጋጋሚ ያረጋገጠልን አቶ ሀይለማርያም የሁለተኛ የማስተርስ ድግሪውን organizational Leadership” ካልፎርኒያ ከሚገኘው Azusa pacific university መውሰዱን ይነገርለታል፡፡
በዚህፅሁፍ ዋነኛ ትኩረት ኃይለማርያምን ና በአፂምኒሊክ ዘመን የነበረውን የወላይታውን ከኦ ጦና ማመሳሰል አይደለም ደግሞ ሁለቱ በምንም መስፈርት ሊመሳሰሉ አይችሉም በዘመን እጅግ በጣም ረጅም ርቀት ያላቸው በስብዕናም በኩል ከቶ የማይገናኝ የሩቅ አለም ሰዎች ናቸው፡፡

• ‹‹የምኒሊኩ ንጉስ ጦና››
ንጉስ ጦና ማን ነው?
ንጉስ ጦና የወላይታ ባለባት የነበረ በደቡብ ኢትዮጵያ በዘመነ መሳፍንት ጊዜያት ሰፊ ግዛት ይዞ ያስተዳደረ ባላባት ነው፡፡ በአፄ ቴዎድሮስ የተጀመረው ዳግም ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ ዓላማና ተግባር ከቴዎድሮስ በኋላም የመጡት ነገስታት ይህንን ህልም ለማሳካት ደፋ ቀና የሚሉበት ጊዜ ነበር በዘመነ መሳፍንት ወቅት ኢትዮጵያ ለ700 አመታት ያኸል ማእከላዊ አስተዳደር የሌላትና በሁሉም አቅጣጫዎች በጎበዝ አለቃ በባላባቶች ትመራ የነበረችበት ጊዜ ነበር ይህ ጊዜ ለኢትዮጵያ የጨለማው ጊዜ ተብሎ ሊጠራ ይችላል ምክንያቱም ከአለም ቀድማ ገናና የነበረች ሀገር በዚህ ረጅም አመት እርሷም አለምን እርስታ አለምም እርሷን እረስተው የኖረችበት ዘመን ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንዲህ መሆኗ እና በተለያዩ ባላባቶች መያዟ ና የህዝቡ ሰቆቃ ከእለት እለት መጨመሩን የተመለከተው አፄ ቴዎድሮስ ዳግሞ ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ መጣር ጀመረ ይሄም ተሳክቶለት የዳግም የኢትዮጵያ አንድነት አባት ለመሆን በቃ በቴዎድሮስ የተጀመረው ሀገር ግዛትን በማስፋፋት ማዕከላዊ መንግስትን ዳግሞ መፍጠር አፄ ዩሀንስም ዘልቀውበት ነበር ነገር ግን በአፄ ዩሀንስ ዘመን ከዚህ የከፋው የደርቡሾች ኢትዮጵያን ዘልቆ መግባት ነበርና የኢትዮጵያን ድንበር ለማስከበር ተነቀሳቅሰው ለድንበር ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈዋል፡፡ እነሱን ተክተው የመጡት ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ (በህዝቡ አጠራር እምዬ ምኒሊክ) የታላላቅ ነገስታቶችን ህልም ከዳር ማድረስና ኢትዮጵያን ቀድማ ወደነበረችበት ቦታ ለመመለስ በየአቅጣጫው ተንቀሳቅሰዋል በዚህም የአፄምኒሊክ አላማና ሀሳቡ ጠንቅቅው ከታረዱት መካከል መስፍኑ ምስራቅ ሸዋን ጨምሮ ሰፊውን ኦሮሞን ያስተዳድር የነበሩት ራስ ጎበና ዳጨው ነበሩ ራስ ጎበና ቀድሞም ቢሆን የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቀው ስላወቁት የምኒሊክን ሀሳቡ መጋፋት አላስፈለጋቸውም ከዛ ይልቅ ከምኒሊክ ጎን በመሆን ታላቋን ኢትዮጵያ ዳግም ለመፍጠር ተንቀሳቀሱ እንዲህ እንዲህ እያለ በየአቅጣጫው የምኒሊክ ማዕከላዊ መንግስት የመፍጠር ተግባር ሀሳቡን ደግፈው ያለምንም ኮሽታ የገበሩ እንዳሉ ሁሉ እንዲሁ ግዛቴን አልሰጥም እኔም ወንድነኝና አልገብርም በማለት ከአንድነታቸው ይልቅ ወንድነታቸው ይበለጠባቸው አንድ አንድ መሳፍንት አልጠፉም ከእነዚህ መስፍኖች መካከል የወላይታው ካኦ ጦና ይገኝበታል ካኦ ጦና ለምኔልክ እንዲገብር ለማድረግ አያሌ ኢትዮጵያውያን ተዋድቀዋል፡፡ ደማቸውን አፍስሰዋል ቆስለዋል እንዲህ ባለመልኩ ንጉስ ጦና ቆስለው ለምኒልክ እጅ ሰጡ ምኒልክ መልካምና አስተዋይ መሪ መሆናቸው እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነው የሚታየው የቆሰሉትን ንጉስ ጦና ወደ አዲስ አበባ ቤተ መንግስታቸው ይዘው ሄደው እስኪ ሻላቸው ከተንከባከቧቸው በኋላ እንደሚገብሩላቸው አረጋግጠው የንጉስ ማዕረጋቸውን ሳይገፏቸው ዳግም ደግሞ ወላይታን እንዲያስተዳድሩ ና በልዩም ግዛት ተመርቆላቸው ተሸኙ ምንም እንኳ በንግስና ማዕረግ ወላይታን ቢያስተዳድሩም ዋናውና ውሳኔን የሚሰጡት ንጉስ ነገስቱ ነበሩ፡፡
• የህዋቱስ ንጉስ ጦና /ኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሺ/
ሀይለ ማርያም ደሳለኝ ቦሽ በ2004 የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በህዋት ውስጥ ታላቅ ፍጥጫ በነገሰበት ሰዓት ህውሀቶች እንደሚፈልጉት የሚያደርጉትን ከፊት አድርገው ከጀርባ መሰሪ ስራቸውን ለመሰረት የወሰኑበት ጊዜ ነበር በዚህ ም በወቅቱ የም/ጠቅላይሚኒስተር ቦታን ይዞ የነበረው ኃ/ማርያም ከመለስ ሞት በኋላ ባለሙሉ ማዕረግ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኖ እነ አቦይ ስብሃት እና መሰሎቹ በርቀት መቆጣጠሪያ /Remote Control/ የሚያንቀሳቅሱትና ወደ ፈለጉበት አቅጣጫ የሚመሩት artificial person ሆነላቸው
በአጠቃላይ ለይስሙላ የተቀመጠ የተቀመጠበት ቦታ ዘወትር የሚቆረቁረው እንደ አንድ የሀገር ጠቅላይ ሚኒስትርነት ደህንነቱን ማዘዝ የማይችል መከላከያው በእሱ ቁጥጥር ውስጥ ያይደለ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆኖ በእንደዚህ አይነት እንዝላልነት ህዝብን እያስጨረሰ ይገኛል እንደመደርተኛ አሉባልታ ነጋሪ በመግለጫዎቹ ላይ እንደ አንድ ፖለቲከኛ የሚያስደነግጥ እንደ አንድ የዋህ ሰው ሆኖ ለሚሰማው ባለማወቁ የሚታዘንለት አይነት ንግግሮችን በማድረግ እያስገረመንም እያናደደነም ዘልቋል ታዲያ ለዚህ አይነቱ የታላቋ ኢትዮጵያ ሀገር በአጋጣሚ የመሪነቱ ቦታ ለተደፋበት ዥዋዥዊ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቢሰማንም ባይሰማንም ይህቺን ምክር ልንለግሰው ወደድን
1. በህውሃት ቁጥጥር ስር ያለው ስልጣንህን ሙሉ በሙሉ ወደ ራስህ በመውሰድ በኢትዮጵያ ላይ ወንጀል የሰሩትን ጉምቱ የህውሃትና አጋር ድርጅቶችን ባለ ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ ለፍርድ እንድታቀርብ ታላቅ ምክሬ ነች ይህንን ለማድረግ ም በህወሃት እጆች የተቀማው የደህንነቱና የመከላከያውን ቦታ በንፁህ ኢትዮጵያውያን እንዲመራ ግልፅ የሆነ ትዕዛዝማ ስተላለፍ አሁን ያሉት ደህንነቶች ላንተ እንደማይታዘዙልህ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የቃል ስለዚህ እነዚህ በህዝቡ እንባ የታጠቡ የመከላከያን የደህንነት ሰዎችንና የህውሀት ባለስልጣኖችን አሳልፎ ለህዝቡ በመስጠት ከህዝቡ ጋር የሚያቀላቅልህን መንገድ ጥረግ፡፡
2. ሁለተኛ ና ቀጣይ ተግባርኸን ማድረግ ይገባኸል ብዬ የምለው እነዚኸን 26አመት ሙሉ ፈላጭ ቆራጭ ሆነው የኢትዮጵያን ህዝብ ደም ያስለቀሱትን ለህዝቡ አሳለፈህ ከሰጠህ በኋላ በእነሱ እግር ስር የተተኩትን የህውሃት ኢህአዲግ ቡችሎች ን ከድርጅታዊ አሰራር እንዲርቁ ማድረግና አሁን እየመራኸ ያለውን ካቡኔ ሙሉ በሙሉ መበተን በመቀጠልም በኢትዮጵያ የተቋቋሙት የፖለቲካ ድርጅቶችን ሰብስበህ ብሔራዊ አንድነትና እርቅ መፍጠር ይሄ ውሳኔህ ኢትዮጵያውያን አንተን ከሚያስቡህ በላ ይ አንተን በሌለኛው ገፅታ የሚያስቡበትን እድል ትከፍታለህ ኢትዮጵያውያን ጥፋቱን አውቆ ተፀፅቶ ለተመለሰ ሰው ሁሌም ቢሆን በራቸው ክፋት ነው፡፡ ስለዚህ ሁለተኛው ተግባርህ ይሄ እንዲሆን ምክሬን ጣል አደርግልሃለሁ፡፡
3. ሶስተኛው የመጨረሻው ተግባርሽ እነዚኸን ሁለት ታላላቅ ተግባር ከፈፀምክ በኋላ አትጠራጠር የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ውስጥ መግባት ትችላለህ ስለዚህ ከእነዚኸ ተግባራት በኋላ ማለትም የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያስቸግሩትን የኢህአዲግ ግምቱ ባለስልጣናትን እጃቸው በሙስና የተጨማለቁት የኢህአዲግ ቡችሎችን መከላከያውን የአንድብሔር መፈንጫያ ደረጉትን ደህንነቶችን እና በአጠቃላይ በስራቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት የሆኑትን ሁሉ አሳልፋ ከሰጠኸ በላዩም ካቢኔውን በትነህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ እርቅ እንዲኖር ካደረግህ ሌላ ምን ቀረህ እኔ ልንገርህ የቀረውን የቀረው ኃ/ማርያም ደሳለኝ ቦሺ ብቻ ነው ያኔ የምታቀረው አንተ ብቻ ትሆናለህ ስለዚህ አንተም በገዛ ፍቃድህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣንህን አንድታስረክቡ ታላቅ ምክሬነች፡፡
መቼም ከአህዲግ ጋር ያጠጋህ ጋኔል ምክር እንድትሰማ አያደርግህም፡፡ እስከ ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝቡ የመከረህን ምክር ብትሰማ እስከአሁንም ስልጣንህ ላይ ባለኖርክ ነበር፡ ፡ መቼም የእንቁራሪቷን ታሪክ ታውቃታለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ካስፈለገህ እዚሁ ብደግመው ደስይለኛል ፡፡
በአንድ አካባቢ ኩሬ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት እንቁራሪቶች ከሩቅ አንድቤት ሲቃጠል ይመለከታሉ እናአንደኛው እንቁራሪት ከዚህ እናምልጥ እሳቱ አጠገባችን ከመድረሱ በፊት እንሄድ በማለት ይጠይቀዋል አንደኛው እንቁራሪት ግን የሚቃጠለው ቤት ከዚህ በጣም ይርቃል እኔ የትም አልሔድም በማለት የእሳቱን ነበልባል እየተመለከተ ወደ ውስጥ ሆኖ መጫወት ይጀምራል፡፡ ይህንን የፈረው ጓደኛው እንቁራሪት በጊዜ እግሬ አውጭኝ ብሎ ይሸሻል እናልህ ቤታቸው እየተቃጠለባቸው ያሉት ወጣቶች ውሃ ለመቅዳት ወደ ኩሬው ይወርዳሉ፡፡ በዚም በያዙት ባልዲ ከእነእንቁራሪቱ ጨልፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩታል፡፡
ምሳሌውን መተንተን አያስፈልግም ህዝቡ እሳት ነው ሲነድ በመንገድ ያገኘውን ሁሉ ያቃጥላል በተለይ የተገፋና የታፈነ ህዝብ መታፈኑ መሮት ሰልችቶ ት የወጣ ጊዜ ያኔ የህዝቡን ቁጣ መመለስ የሚያስችላችሁ ቅንጣት ሀይል እንኳን አይኖራችሁም ትግሉ እንደ ሰደድ እሳት በየቦታው እየተያያዘ ነው ብዙ ሰው ሳያልቅ ሰላማዊት ኢትዮጵያ ዳግም እንድትፈጠር እላይ ማማው ላይ ያለችሁ ወሳኝ ሚና መጫወት አለባችሁ አልያ ግን ማማውን መናድ የሚችል ህዝብ ከጎናችሁ አለ ይሄ ህዝብ የባብሎንን ግንብ ከናዱት ከነናውያን በላይ ጩኸቱ ሀያል ነው!!!!

Filed in: Amharic