>

አሁን እኛ አንገብጋቢ ጉዳያችን ይሄ አይደለም ! (ሰላም መሃመድ)

አንድ እንድታውቁ የምፈልገው ነገር ከዚህ በፊት ኩማ ደመቅሳ ይሁን ጁኔይድን ሳዶ የኦሮምያ ፕሬዘዳንት በነበሩ ወቅት የአማርኛ ጽሑፍ ከኦሮምኛ በይዘቱ አንሶ በማስታወቂያ ቦርዶች ላይ ሲጻፍ ነበር :: ይህ በክልሉ ሕገ ረቂቅ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ዘመናት ያስቆጠረ ጉዳይ ነው !

አሁን ሁኔታውን አዲስ እንደተፈጠረ አድርጎ ማራገብ ለምን አስፈለገ? 
አስታውሳለሁ በዘመቻ መልክ ነበር በየማስታወቂያ ታፔላዎች ላይ የተጻፉትን ስእልና ፊደሎች ሲያጠፉና ሲያቀልሙ የነበረው ማለት ይቻላል !
በመሠረቱ ህዝቡ ምንም የዘረኝነት መንፈስ በውስጡ ባለመኖሩ ኦሮምኛ የኔ ነው ብሎ ; በሚሊየኖች የሚቆጠር አማርኛ ተናጋሪ ማኅበረስብ ነገሩን ተግባራዊ ሲያደርግ ኖሮአል !!!

ምኑ ነው አዲስ ነገር ? ምንም አዲስ ነገር የለም !!!
አማርኛ ትምህርት ካንደኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጥ የነበረው ቀርቶ ከአምስተኛ ክፍል መሰጠት ከጀመረ ሃያ ዓመት አለፈው እኮ !
አማርኛ ተናጋሪው ሁሉ የቁቤ ተማሪ ከሆነ ቆየ አይደል እንዴ ? ኦሮምኛን ማን ይጠላል ? አማርኛንስ ልጥላ የሚል ኦሮሞ የት ድረስ ያስኬደዋል? የትም !!!

በመላው ሀገራችን አማርኛ ብቻ በነበረበት ዘመን አማራ የበላይ ስለሆነ ሳይሆን ሀገር በቀል ፊደል ያለው ልሣን አማርኛ በመሆኑ ከዚያ ጋር ተያይዞ የሁሉ ነገር መጠቀሚያ ሆኗል ! ያንን ስንል እንደ ቻይና ወይም እንደ ኮርያ የራሳችን ፊደል ካለሆነ የሚል ፈልጥ አልነበረንም ! የነጮቹ የመማሪያ መጽሐፍት በየዘርፉ በሰፊው ተሰራጭተው ስንማርባቸው ቆይተናል !

በሀገራችን ብዙ ጎሳዎች አሉን ሁሉም የራሱን ሳይተው ሌላም በመጨመር የመግባቢያውን አንደበት ከፍ ሊያደርገው ይገባል ! ቁዋንቁዋ ማወቅ አይጎዳምና ! ሁሉም ሰው በስደት ዓለም አዳዲስ ልሣን በመማር ከሰዎች ጋር ይግባባበታል !
በሀገራችን በተለያየ ክልል ተመሳሳይ ነው ምናልባት ከደቡብ በቀር ! ትግራይም በራሱ አፍ መፍቻው ነው ፊደል የሚቆጥረው ይሄው ነው ነባራዊ ሁኔታችን !

ባለፈው ባህርዳር አማራ ሚዲያ ላይ ዶ/ር ዓብይ አሕመድ ቀርቦ ቃለመጠይቅ ላይ ከተናገራቸው አንዱ በህዝቦች መካከል ያለውን ተቀራራቢነት ለማጠናከርና ለዘመናት አብሮ የነበረውን ማንነት ይባስ ለማቆራኘት በአማራ ክልል ኦሮምኛ ት/ት እንዲጀምር ንግግር እንዳለ ; በኦሮምያም ክልል እንደፊቱ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ አማርኛ እንዲሰጥ ሁኔታውን እያዩት እንደሆነ ሲናገሩ ሰምተናል !

በወቅቱ ይሄን የሰማ የተቃወመ ነበር ? አልነበርም !!!
አማርኛን አቀላጥፎ የሚናገር የኦሮሞ ልጅ እንዳለ ሁሉ ኦሮምኛንም አሳምሮ የሚናገር የአማራ ልጅ ወይም የሌላ ጎሳ ተወላጅ መኖሩን መገንዘብ ተገቢ ነው ! እርግጥ ነው ሀገሪቱ አንድ ብሔራዊ መግባቢያ ቁዋንቁዋ አላት ወደፊት ሁለት ሦስት ይኖረናል ተብሎ ይገመታል ! አሁን እኛ አንገብጋቢ ጉዳያችን ይሄ አይደለም !

ዋናው ጉዳይ ይህ ነው !
፩/ ሽፍታው ቡድን በሕዝባችን ደም እየቀለደ መኖር የለበትም !
፪/ ዘራፊው ወያኔ ከዚህ በላይ ዘርፎ በኛ ሀብት ትግራይን የኢንዱስትሪ ዞን ማድረግ የለበትም !
፫/ ኢትዮጵያን ትውልድ ከፍሎ በማይጨርሰው ብድር ማስያዝ የለበትም !
፬/ በሕዝብ መካከል ከፍተኛ ቀውስና ትርምስ እየፈጠረ የራሱን ጥቅም እያስከበረ በጊዜያዊ መደለያ በማጭበረበር መቀጠል የለበትም !
፭/ በየቦታው የተነሳው የህዝብ ተቃውሞ በግርግር ፈጣሪዎች መደናቀፍ የለበትም !!!

ድል በህውሓት ቅኝ ግዛት ውስጥ ለወደቀው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን !

Filed in: Amharic