>
5:13 pm - Thursday April 19, 7032

ሠራዊቱ የገዛ ወገኑን ለምን ይጨፈጭፋል?

ጉዱ ካሳ

የአንድ አገር የምድር የአየር እና የባህር ኃይል የሚቋቋመው የአገሪቱን ዳር ድንበር ከውጭ ወራሪ ኃይል ለመጠበቅ እና ሊከሰቱ የሚችሉ የተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎችን ለመቋቋም እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያም በቅርብ ጊዜ ታሪኳ የገጠሟትን ሶማሊያ እና ሻዕብያ የውጭ ወራሪዎች ጥቃት በብቃት መክታ የመለሰችው በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ በተካኑ እና ህዝባዊነት በተላበሱ የጦር ኃይል አባላቷ ነበር፡፡ ሀገራችን በእስራኤል፣ በአሜሪካና አውሮፓ ስመጥር ከሆኑ ወታደራዊ ተቋማት የተመረቁ መኮንኖች የነበሯት ሲሆን በሀገር ውስጥም እነደ ሀረር ጦር አካዳሚ ዓይነት ብቃት ያላቸው መኮንንችን አሰልጥኖ የሚያወጣ ወታደራዊ አካዳሚ ነበራት፡፡

ህወሀት እና ሻዕብያ አስመራን እና አዲስ አበባን በህዝብ ድጋፍ ከተቆጣጠሩ በኋላ ልዩ ትኩረት ሰጥተው የሠሩት ሥራ ወታደራዊ አካዳሚዎችን ማፍረስ እና እውቅ ጄኔራሎችን እና ሌሎች መኮንኖችን ማጥፋት ነበር፡፡ የአየር ኃይልን ሙሉ በሙሉ አጠፉ፡፡ የሽምቅ ውግያ ውስጥ የነበሩ የአንድኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቅጡ ያላጠናቀቁ የህወሀት ተዋጊዎችንም በመደበኛ መኮንንኖች ምትክ በጦር አዛዥነት አስቀመጡ፡፡

በዚህ መሀል ግን የ1990 ዓ.ም የሻዕብያ ወረራ እየሞተ ለነበረው የአገሪቱ ወታደራዊ ተቋም ትንሳኤ እንዲያገኝ ከመርዳቱም ሌላ በወታደራዊ አካዳሚዎች ሰልጥነው ሚሊታሪ ሳይንስን የተካኑ ወታደራዊ መኮንኖችን ህወሀት መልሶ እንዲጠቀምባቸው የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡በዚህም የተነሳ የደርግ ወታደር እየተባሉ ተባረው የነበሩ መኮንኖች ተቋርጦ የነበረው የሰባት ዓመት ደመወዛቸው እየተከፈለ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ተደረገ፡፡ የባድመ እና የዛል አንበሳ ጦርነትም በኢትዮጵያ የበላይነት እና በሻዕብያ የከፋ ውድቀት እንዲጠናቀቅ የቀድሞው መንግሥት መኮንኖች ከፍተኛ ሚና ተወጡ፡፡

በተፈጥሮው ቂም በቀል እና የሴራ ፖለቲካ አስተሳሰብ የተጠናወተው ህወሀት ሻዕብያ ድል ከተመታ በኋላ አብዛኛዎችን የቀድሞ ጦር መኮንኖች መልሶ ከመበተኑም ሌላ “በጦርነቱ የተሳተፉት የቀድሞ ሠራዊት አባላት ከ1500 አይበልጡም “ በማለት የቀድሞ ሠራዊትን ተጋድሎ እና ወሳኝ ሚና በማንኳሰስ በወቅቱ የመከላከያ ሚንስትር የነበረው የጄኔራል አባዱላ ገመዳ (የቀድሞ የደርግ አስር አለቃ ምርኮኛ) ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገልጽ አደረገ፡፡ ለአገር የከፈሉትን መሰዕዋትነትም ተላላኪው “ጄኔራል” ዝቅ አድርጓል፡፡ ህወሀት በሚከተለው የሴራ ፖለቲካ አማካኝነት የአንደኛ ደራጃ ትምህርት ያላጠናቀቁትን ሽምቅ ተዋጊዎቹን ቀስ በቀስ ወደ ሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ እያሳደገ መጣ፡፡

ጄኔራሎቹ ለህወሀት ውለታ ሲሉ ያላደረጉት ነገር የለም፡፡ የጦር አዛዦቹ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን በኃይል ለመጨፍለቅ ሲባል በትግራይ ወጣቶች የተሞላ አጋዚ የሚባል ፓራሚሊታሪ ኃይል አቋቁመው ከ2008 ዓ.ም ወዲህ በቢቢሲ ዘገባ መሠረት ከ670 በላይ ሲቪሎች እንዲገደሉ አድርገዋል፡፡ ይህ አህዝ የ2010 ዓ.ም የሲቪሎች ግድያን አያካትትም፡፡ ለመሆኑ ሠራዊቱ ህዝቡን ለምን ይጨፈጭፋል? ለዚህ የሚከተሉትን መላምቶች ማስቀመጥ ይቻላል፡-

1/ ጄኔራሎችን ጨምሮ ብዙዎቹ የሠራዊቱ አዛዦች ወታደራዊ ሳይንስ፣ ስትራቴጂ እና ታክቲክ ምን እንደሆነ የማያውቁ፣ከወታደራዊ አካዳሚ ያልተመረቁ እና በዘር ፖለቲካ ብቻ የተጠመቁ መሆናቸው አንዱ የጸረ ህዝብነታቸው ምክንያት ነው፡፡ የተማሩ ጄኔራሎች ሀገራቸውን ለአደጋ አያጋልጡም ፤ ህዝብንም በምንም መስፈርት አያስገድሉም፤

2/ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት ጄኔራል መኮንንኖች የህወሀት ሽምቅ ተዋጊ የነበሩ ሆነው ህገ መንግሥቱ ከሚደነግገው ውጭ የፖለቲካ ወገንተኛ ስለሆኑ እና ለትግራይ መገንጠል ከመጀመሪያው ጀምሮ የተሰበኩ እና የታገሉ ስለሆኑ የጄኔራል አብርሀ ወ/ማርምን ከ1 ሚሊዮን በላይ ኦሮሞ ከሶማሊያ ክልል እንዲፈናቀል ማድረጉ ዋና መስረጃ ሊሆን ይችላል ፣

3/ ብዙዎቹ ጄኔራሎች እና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የበርካታ ሚሊዮን ብር ካምፓኒ ባለቤት እና ባለሀብት ስለሆኑ እንዲሁም በኮንትሮባንድ ሥራ የተሠማሩ ስለሆኑ ከህዝባዊ ኃላፊነት ቅንጣት ስሜት ወደ ጎደለው የማፍያ ባህርይ ወደመላበስ ወርደዋል፣

4/ የሀገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ወይም ጠቅላይ ሚንስትሩ በቂ ፖለቲካዊ ዕውቀት እንደሌላቸው “ጄኔራል መኮንኖች” ስለሚያውቁ እና በሚፈጽሙት ወንጀል ምንም ዓይነት እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደማይችሉ ስለሚገነዘቡ ኅዝብን በማፈን ተግባር ተሰማርተዋል፡፡

ስለሆነም ሠራዊቱ ከድንበር ወደ መንደር ወርዶ ንጹሀን ዜጎችን በተለይም ህጻናትን ጨምሮ የአማራ እና የኦሮሞን ዘር በስናይፐር እያጨደ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገራችን በከፋ ችግር ውስጥ ወድቃለች፡፡ ሊታደጋት የሚችለውም የአምላክ ጥበብ ብቻ ነው፡፡

Filed in: Amharic