>

«እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም!» (ኤቫ አደም)

ታማኝ በየነ ባለፈው ሰሞን ባሳየን ድንቅ ስራው ፋሽስት ወያኔን «እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም!» ሲል ገልጾት ነበር። ፋሽስት ወያኔ ትናንትና በመሪ ዜናው HR128 ከፊት ያስቀመጣቸውን እስክንድር ነጋንና አንዷለም አራጌን እፈታለሁ ብሎ ዜና ሲያሰራጭና ለአለም ሲናገር ውሎ ዛሬ ግን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን የግንቦት ሰባት አባል ነበርሁ ብለህ ካልፈረምህ «አትፈታም» ብለውት ያልነበርሁትን አልፈርምም ስላለ እንደማይፈታ ሲፒጄ ነግሮናል። «እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝም!» ይሏል ይሄ ነው። እባብ እባብነቱን አይረሳም፤ ወያኔም ተቀጥቅጦ እስካልተወገደ ድረስ እባብነቱን አይተውም፤ መቸም ቢሆን አይተኛም፤ ሳያመቸው አድብቶ፤ ሲያመቸው ደግሞ በመንግሥትነት በተሰየመበት ወንበር ላይ ሆኖ ያይናቸው ቀለም ያላማረውን ይናደፋል፣ ይበቀላል፤ ቂሙን ይወጣል፤ ያጠፋቸውማል።

ጋዜጠኛ እስክንድር ጋዜጠኛ እንጂ የግንቦት ሰባት አባል አለመሆኑን ለፋሽስት ወያኔ ፍርድ ቤት በመግለፅ ተከራክሮ ቢያሸንፍም ነውረኛው የግፍ ቤት ግን ያላንዳች ማስረጃ የ18 ዓመት የበቀል እስር በይኖበታል።

የግንቦት ሰባት አባል ስለመሆንህ ፈርምና ትፈታለህ ያለው አገዛዝ እስክንድርን የግንቦት ሰባት አባል ነው ብሎ 18 ዓመታት በእስር እንዲቀጣ የፈረደበት ነውረኛ ቡድን ነው። ይህ በግልጽ የሚያሳየው የትግራዩ የአፓርታይድ አገዛዝ እስክንድርን በ18 ዓመታት የበቀል እስር የቀጣው ያላንዳች ማስረጃ ነው ማለት ነው። እስክንድር 18 ዓመታት በእስር እንዲቀጣ ፍርድ ቤት ተብዮው የበየነበት የግንቦት ሰባት አባል መሆኑን በማስረጃ ስላረጋገጠ ቢሆን ኖሮ ዛሬ የግንቦት ሰባት አባል ስለመሆንህ አምነህ ፈርምና ተፈታ ባልተባለ ነበር።

ፋሽስቶቹ ዛሬ የግንቦት ሰባት አባል ስለመሆንህ ፈርምና ተፈታ ያሉት እስክንድር የወያኔ ፍርድ ቤት የበየነበትን የአስራ ስምንት ዓመታት የእስር ቅጣት በመቃወም «ሰበር ሰሚ» እስከሚባለው ችሎት ድረስ ቀርቦ የተከራከረውን ብርቱ ሰው ነው። ፋሽስት ወያኔ ሰው ለማዋረድ የሚሄደው እስከዚህ ድረስ ነው። እኒህ አረመኔዎች የግንቦት ሰባት አባል ነበርሁ ብለህ ካልፈረምህ «አትፈታም» ያሉት እስከ ሰበር ሰሚ ደርሶ የተከራከረውን እስክንድርን ራሱን እንዲያዋርድና በራሱ ላይ እንዲፈርድ ነበር። እባቡ ፋሽስት ወያኔ እንዲህ ነው፤ እስካልተወገደ ድረስ እባብ ለመደ ተብሎ በኪስ አይያዝምና እስክንድርንም ሆነ ኢትዮጵያን ከእስር ለማስፈታት የተጠመጠመብንን እባብ አናቱን ቀጥቅጦ ማስወገድ ግድ ነው።

Filed in: Amharic