>

የማለዳው የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ ...(ነብዩ ሲራክ)

ስጋቱ ሲገፈፍ …

ከቀናት በፊት እናቴ የእስረኞችን የመፈታት ዜና ስትሰማ ደስታዋ ወሰን አጣ ፣ እናት ነትና ” ያስሩህና ትጎዳብኛለህ ፣ አትምጣብኝ !” በሚል ለመጠየቅ ወደ ሀገር እንዳልገባ ትከላክለኝ የነበረው ሀሳቧ ተቀይሮ አገኘኋት … የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምህረት ትለቀቃሉ የሚለው መረጃ ሲናኝ የሰማችው ከልታማ እናት እንደገና የተወለደችውን ያህል ደስታዋ ወሰን አጣ ! ከልጅነት እስከ እውቀት በጉያዋ ስር ሆኘ የማውቀውን በእውነተኛው ደስታና ሀሴት ተሞልታ ድምጸኝ ሰማሁት …ያችን ምሽት የተሰማኝን ስሜት መግለጽ አይቻለኝም ! ከአመታት በኋላ እናቴ በደስታ ተውጣ ያነጋገረችኝ ቀን ቢኖር ያችን ቀን ነበር … በእርግጥን በአይኗ የሚንከራተት ልጇን በአይነ ስጋ ለማየት የመሻቷ ህልም የመቅረቡ እውነት ለእናቴ ከምንም በላይ ሆኗል … ተመስገን !

እኔና እነሱ …

የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት እንደሚውተረተር ዜጋ ወጥቸ የወረድኩ በተሌ ጎልማሳ አባወራና ነኝ እንጅ ኤጀንሲ ከፍቸ በእድሜ ያልበሰሉ እህቶቸ አሻግሬ የሸጥኩ ክፉ ደላላ አይደለሁም። ከሀገር ቤት እስከ የመንና ሳውዲ በተዘረጋ የድለላ ሰንሰለት ወገኖቸን እየሰደድኩ በግፍ እጀ ደም የተጨመለ በድለላ የናጠጥኩ ባለሀብት አይደለሁም ። ወገኖቸን አግቸ ፣ ዘግቸና አፍኘ በወገኖቸ ደም አልነገድኩም ። ስጋየን አዋድጄ ፣ ወንድም እህቴን አዋርጀ ሰብዕናቸውን አልተጋፋሁ አንቱ የተበልኩ የዘመንኩ ወሮበላ አይደለሁም! እኔና እነሱ እንለያያለን ፣ እነሱ አሳዳጆቸ እንዲህ ናቸው ፣ እኔ ነፍሴ ድህነትን የምታከብር ሰብዕናን የምታነግስ ዘር ሐይማኖትን የማትለይ ከወንጀልና ጸጸት የጸዳች ናት ነፍሴ !

እኔ በሳውዲው ስደት ህይዎቴ የሳውዲን ህግ አክብሬ ኖሬያለሁ ፣ ለወገኖቸ ድምጽ ለመሆን ተፍጨርጭሬያለሁ ፣ ከዚህ ውጭ የፈጸምኩት አንዳችም ወንጀል የለም ! ከግል የኩናንያ ስራየ ጋር በተጓዳኝ ጊዜየን መስዋዕት አድርጌ ወቅታዊ መረጃን የማቀበሌ የድልድይነት ስራዬ ብቻ ያስመሰግነኝ እንደሁ እንጅ ያሳድደኛል ብየ አላምንም። እውነቱ ይህ በመሆኑ ለእኔ ስጋቱ አስግቶኝ አያውቅም ። ዳሩ ግን እውነትና ፍትህ በጎደለበት ሰማይ ስር ስለ እውነት መስዋዕት እከፍል ዘንድ የእናት አንጀት ፍቅሯ በስጋት ነትቦ እናትና ልጅ የባጀነው በመለያየት ስቃይ ነው …

ያ የመለያየት ስጋት ስቃይ ከእናቴ ርቆ ” እፈልግሃለሁ ናልኝ ልጄ ! ” ብላኝ ደስ ብሎኛል። ስጋቷ ከላዩዋ በመከላቱ ደስ ብሎኛል። ያ ማለት የማይፈልጉኝ አሁንም አያጠቁኝም ማለት አይደለም። ዳሩ ግን ያሻቸውን ያህል ፈርጣማ ጉልበታም ቢሆኑ የያዝኩትን እውነት በሚዛኑ የሚለካ በፈጠሪዬ ነውና የምጠነቀው ዝንቤን እሽ አይሏትም !

ከምንም በላይ የእናቴ ” ናልኝ ! “ድምጽ ምንም ሊያስደርገኝ አቅም አለውና የመመለስ ውሳኔየን በደስታ ለእናንተ ሳሳውቃችሁ ስለጎረፋችሁልኝ የድጋፍና የመልካም ምኞት መልዕክት የተሰማኝን ወሰን የሌለው ደስታ የከበረ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ ! አመሰግናለሁ !!!

ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 4 ቀን 2010 ዓም

የማለዳው የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ …============================ ስጋቱ ሲገፈፍ …=============== ከቀናት በፊት እናቴ የእስረኞችን የመፈታት ዜና ስትሰማ ደስታዋ ወሰን አጣ ፣ እናት ነትና " ያስሩህና ትጎዳብኛለህ ፣ አትምጣብኝ !" በሚል ለመጠየቅ ወደ ሀገር እንዳልገባ ትከላክለኝ የነበረው ሀሳቧ ተቀይሮ አገኘኋት … የእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በምህረት ትለቀቃሉ የሚለው መረጃ ሲናኝ የሰማችው ከልታማ እናት እንደገና የተወለደችውን ያህል ደስታዋ ወሰን አጣ ! ከልጅነት እስከ እውቀት በጉያዋ ስር ሆኘ የማውቀውን በእውነተኛው ደስታና ሀሴት ተሞልታ ድምጸኝ ሰማሁት …ያችን ምሽት የተሰማኝን ስሜት መግለጽ አይቻለኝም ! ከአመታት በኋላ እናቴ በደስታ ተውጣ ያነጋገረችኝ ቀን ቢኖር ያችን ቀን ነበር … በእርግጥን በአይኗ የሚንከራተት ልጇን በአይነ ስጋ ለማየት የመሻቷ ህልም የመቅረቡ እውነት ለእናቴ ከምንም በላይ ሆኗል … ተመስገን !እኔና እነሱ …======== የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት እንደሚውተረተር ዜጋ ወጥቸ የወረድኩ በተሌ ጎልማሳ አባወራና ነኝ እንጅ ኤጀንሲ ከፍቸ በእድሜ ያልበሰሉ እህቶቸ አሻግሬ የሸጥኩ ክፉ ደላላ አይደለሁም። ከሀገር ቤት እስከ የመንና ሳውዲ በተዘረጋ የድለላ ሰንሰለት ወገኖቸን እየሰደድኩ በግፍ እጀ ደም የተጨመለ በድለላ የናጠጥኩ ባለሀብት አይደለሁም ። ወገኖቸን አግቸ ፣ ዘግቸና አፍኘ በወገኖቸ ደም አልነገድኩም ። ስጋየን አዋድጄ ፣ ወንድም እህቴን አዋርጀ ሰብዕናቸውን አልተጋፋሁ አንቱ የተበልኩ የዘመንኩ ወሮበላ አይደለሁም! እኔና እነሱ እንለያያለን ፣ እነሱ አሳዳጆቸ እንዲህ ናቸው ፣ እኔ ነፍሴ ድህነትን የምታከብር ሰብዕናን የምታነግስ ዘር ሐይማኖትን የማትለይ ከወንጀልና ጸጸት የጸዳች ናት ነፍሴ ! እኔ በሳውዲው ስደት ህይዎቴ የሳውዲን ህግ አክብሬ ኖሬያለሁ ፣ ለወገኖቸ ድምጽ ለመሆን ተፍጨርጭሬያለሁ ፣ ከዚህ ውጭ የፈጸምኩት አንዳችም ወንጀል የለም ! ከግል የኩናንያ ስራየ ጋር በተጓዳኝ ጊዜየን መስዋዕት አድርጌ ወቅታዊ መረጃን የማቀበሌ የድልድይነት ስራዬ ብቻ ያስመሰግነኝ እንደሁ እንጅ ያሳድደኛል ብየ አላምንም። እውነቱ ይህ በመሆኑ ለእኔ ስጋቱ አስግቶኝ አያውቅም ። ዳሩ ግን እውነትና ፍትህ በጎደለበት ሰማይ ስር ስለ እውነት መስዋዕት እከፍል ዘንድ የእናት አንጀት ፍቅሯ በስጋት ነትቦ እናትና ልጅ የባጀነው በመለያየት ስቃይ ነው … ያ የመለያየት ስጋት ስቃይ ከእናቴ ርቆ " እፈልግሃለሁ ናልኝ ልጄ ! " ብላኝ ደስ ብሎኛል። ስጋቷ ከላዩዋ በመከላቱ ደስ ብሎኛል። ያ ማለት የማይፈልጉኝ አሁንም አያጠቁኝም ማለት አይደለም። ዳሩ ግን ያሻቸውን ያህል ፈርጣማ ጉልበታም ቢሆኑ የያዝኩትን እውነት በሚዛኑ የሚለካ በፈጠሪዬ ነውና የምጠነቀው ዝንቤን እሽ አይሏትም ! ከምንም በላይ የእናቴ " ናልኝ ! "ድምጽ ምንም ሊያስደርገኝ አቅም አለውና የመመለስ ውሳኔየን በደስታ ለእናንተ ሳሳውቃችሁ ስለጎረፋችሁልኝ የድጋፍና የመልካም ምኞት መልዕክት የተሰማኝን ወሰን የሌለው ደስታ የከበረ ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ ! አመሰግናለሁ !!!ቸር ያሰማን ነቢዩ ሲራክ የካቲት 4 ቀን 2010 ዓም

Posted by Nebiyu Sirak on Saturday, February 10, 2018

Filed in: Amharic