>

እዉነትም፣ መምጣት ያለበት ቀን፣ ፈጽሞ ላይመጣ አይችልም!! (ሃራ አብዲ)

ምነዉ እንደወፍ በርሬ፣ እንደ ዉቅያኖስ ምድርን ሸፍኜ፣ ዛሬ ኢትዮጵያ በተገኘሁ።
እዉነትም፣ መምጣት ያለበት ቀን፣ ፈጽሞ ላይመጣ አይችልም!! (ሃራ አብዲ)

እንደ ዛሬ ወፍ መሆን የተመኘሁበት ፣ እንደዉቅያኖስ ምድርን መሸፈን የፈለኩበት፣ ቀን ያለ አይመስለኝም። ዛሬ፣ እንደወፍ በርሬ ከሀገሬ ሰማይ ላይ ቁልቁል እየተመለከትኩ «ስማ በለዉ ፣የዜማ ጊዜ ደረሰ » ማለት ብችል ምንኛ በታደልኩ። ዛሬ፣ እንደ ዉቅያኖስ ፤ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በለሆሳስ ፍስስስ……እያልኩ፤ የወገኖቼን የደስታ ሲቃ ከምድር ልብ ዉስጥ ሆኜ በሰማሁት።

«ሞልቶ ከሚተርፈዉ እድሜህ አትንፈገኝ» ይሉ ነበር ሴት አያቴ። እዉነትም እድሜ ጠግበዉ አለፉ። ኢትዮጵያም ፣ይህን የምጥ፣ ጣር መጀመሪያ፣ ለማየት ፣እድሜ፣ አገኝታለች። እኛም እንደዚሁ።

የማያልፍ፣ የሚመስለዉ፣ ሲያልፍ፤ የሚመጣ ፣የማይመስለዉ፣ ሲመጣ፣ የሚሆን፣ የማይመስለዉ፣ ሲሆን፣
በአይናችን በብረቱ እያየን ነዉ። በመከታተል ፣ ከህወሃት አፓርታይድ የእስር ማነቆ እየተላቀቁ ከቤተሰቦቻቸዉና ከሚወዳቸዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚቀላቀሉት የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ጉዳይ የኔንም ልብ በታላቅ ደስታ አስዘልሎታል። ብርቅ የኢትዮጵያ ልጆች፣እነ እስክንድር ነጋ፣ አንዱአለም አራጌ፤ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ጫልቱ፣ ማሙሸት አማረ እና ሌሎቻችሁም፤ በእግር ብረት ሲያስራችሁ፣ ሲገርፋችሁ፣ ቁልቁል ሲሰቅላችሁና በጣእራችሁ ሲሳለቅ የነበረዉ የትግራይ አፓርታይድ አገዛዝ፣ እነሆ አፍንጫዉን ተሰንጎ፤ እናንተን ከመንጋጋዉ ዉስጥ ፈልቅቆ መትፋት ግድ ሆኖበታል!!! በአረመኔዎች፣ በባለጌዎች፣ በፋሽስቶች፣ በምቀኞች፣ በቀናተኞች፣በስግብግቦች እና በአልጠግብ ባዮች የተሞላዉ የትግራይ ማፍያ ቡድን፣ የተፈጠረበትን ቀን እየተራገመ የግዱን ምርኮዉን በመመለስ ላይ ይገኛል። የወጣ ሁሉ መዉረዱ፣ የተፈጥሮ የስበት ህግ ነዉና፣ «ጉምበት 20, 1983 አ.ም የቶቆጣጠረዉን» የማይገባዉን ስልጣን በአሰገራሚ ፍጥነት እያጣዉ መምጣቱን፣ የትግራይ ነፃ አዉጭ ድርጅት ዛሬም አልሰማ ይሆናል። በዩናይትድ እስቴትስ፣ ሊጸድቅ ሁለት ሳምንት ብቻ የቀረዉ H.R 128 የሚያመጣበትን መዘዝ ለመሸሽ፣ የእዉር ድንብሩን ብጥቅ፣ ብጥቅ እያደረገ፣ ዉዶቻችንን በቁጠባ መልቀቁ ሲገርመኝ፣ ይባስ ብሎ፣ ከእስር የተፈቱትን ለመቀበል የታደሙ በመቶ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ማሰር እብደት ካልሆነ በቀር ምን ይባላል? ለመሆኑ፣ ገለልተኛዉ አጣሪ ቡድን እስክ መጨረሻዉ ድረስ ያለዉን
የህወሀት ወንጀል በሙሉ የማያጣራ ይመስለዋልን? መቼ ነዉ እነዚህ አንጎል ፋቶዎች ሰብአዊ ህሊናቸዉን
መጠቀም የሚጀምሩት?
‘ለአቶ በቀለ አቀባበል በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በፌደራል ፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል’‘በሌላ በኩልም ዛሬ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጭምሮ የተፈቱትን የሕሊና እስረኞች ለመቀበል ከወጡት ወጣቶች መካከል ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወገኖች ታስረዋል::
ከነዚህም መካከል ጋሻነህ ላቀዉ፤ ይድነቃቸው አዲስ; አዲሱ ጌታነህ; ባየልኝ ብርቁና ሲለሽ ደቻሳ
ይገኙበታል:: አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ይዛችኋል እንዲሁም እስረኞችን አጅባችኋል በሚል ነው
የታሰሩት’(ዘ-ሃበሻ, Feb, 14,2018) ጉድ እኮ ነዉ! ደግሞ የነሱን ስራ ባቃለሉላቸዉ ያስሩአቸዋል?
ጎፈሬያቸዉን በማበጠርያ ነቅሰዉ፣ ጅብ አይበላሽ ጫማቸዉን አፅድተዉ፣ ሻንጣዎቻቸዉን ተቀብለዉ በጭንቅላታቸዉ ላይ ፣ተሸክመዉ ( እንደ ድሮ ቆርቆሮ ያለሽ ዘመናቸዉ) ከነ በቀለ ገርባ…. ሁዋላ ሁዋላ፣ ሱክ፣ ሱክ እያሉ እያንዳንዱን ጀግና እቤቱ አስገብተዉ፣ ለኩሊነት አገልግሎታቸዉ፣ አራትም፣ አምስትም ብር ተቀብለዉ፣« እግዚሃር ይስጥልኝ» «ያቅነይለይ» ብለዉ ከዉጭ በር መመለስ የነበረባቸዉ እኮ ወያኔዎቹ ነበሩ !! ገና አንድ ትዉልድ ሳያልፍ ማንነታቸዉን ረሱት አነዚህ እታች ቤት ያደጉ ለማኞች!! እነሱ ቢረሱ የኢትዮጵያ ህዝብ አይረሳላቸዉም። የበሉበትን እጅ ነካሾች።
«ሞልቶ ከሚተርፈዉ እድሜህ አትንፈገኝ» እንዳሉት ሴት አያቴ፣ በኢትዮጵያ ነጻነት ፤ -እኩልነት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን በማንኛዉም መንገድ ለሚታገሉት ወገኖቻችን ሞልቶ ከሚተርፈዉ እድሜዉ  አይንፈግብን።
-አሁን በእስር ላይ ለሚገኙት ወገኖቻችን፤ የነጻነት ጎህ ፈጥና ትቅደድ!
– የትግራይ አፓርታይድ እሳት እንደ ገባ ጎማ ተጨማዶ ሳለ፣የሁላችንም በትር ይረፍበት።

– አሁንም አጥብቆ የጨበጠዉን ብረት ከእጁ ላይ በማስረገፍ፣ህዝባችንንና ሀገራችንን ነጻ ለማድረግ
ሁላችን በመክሊታችን እንነግድ።
ዛሬ ወፍ ለመሆን እንደተመኘሁ፣ ዉቅያኖስ ለመሆን እንዳሰብኩ፣ ያን ጊዜ በምኞት አልቀርም። በርሬ
ሀገሬ እገባለሁ። ያን ጊዜ፣ ህልቆ መሳፍርት የሌላቸዉ ወፎች (አዉሮፕላኖች) ኢትዮጵያዉያኖችን እያበረሩ
ወደ አዲስ አበባ ይጎርፋሉ። የአዲስ አበባዉ፣ የባህር ዳሩ፣ የጂማዉና ሌሎቹም አዉሮፕላን ማረፊያዎች
የአየር ትራፊኩን ለማስተናገድ ስለሚጨናነቁ፣ አራቱ የመቀሌ፣ ኢንተርናሽናል አዉሮፓላን ማረፊያዎች፣
ባለቤቶቹን የኢትዮጵያን ልጆች ያስተናግዳሉ።( ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ ዘርፈዉ ለሃጫቸዉ
እየተዝረከረከ፣ በጉጉት ያሰሩዋቸዉ ፣ የመቀሌ አዉሮፓላን ማረፊያዎች ከየት አባታቸዉ ኢንተርናሽናል
ኮሚዩኒቲ ጋር ሊገናኙበት ነዉ?)
Anyhow, ያን ጊዜ ምድራችን በደስታ ዉቅያኖስ ትጥለቀለቃለች! መምጣት ያለበት ቀን፣ ፈጽሞ ላይመጣ አይችልም። ከምጥ የሚቀጥለዉ መወለድ ብቻ ነዉ።

Filed in: Amharic